የካቲት ፯ /7/
በዚችም ዕለት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት ቴዎድሮስ አረፈ።
እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ አምስተኛ ነው። ይህም አባት መርዩጥ በሚባል አገር በአንድ ገዳም ውስጥ መነኰሰ የዚያም ገዳም ስም ነው። ለአንድ ፍጹም ጻድቅ የሆነ ሽማግሌ ሰው ደቀ መዝሙሩ ሆነ። እርሱም ልጁ ቴዎድሮስ በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና እንደሚሾም በመንፈስ ቅዱስ አይቶ ይህንን ለመነኰሳቱ ነገራቸው።
ይህም አባት ቴዎድሮስ በገድል የተጠመደ ሆነ መልኩም የሚያምር ነው በሰውነቱም ላይ ከውስጥ ማቅ በመልበስ በላዩ የብረት ልብስ መንቈር ይለብስ ነበር በቅንነቱና በትሕትናው ፍጹም ሆነ። በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ተመርጦ በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ። የክርስቶስንም መንጋዎች በበጎ አጠባበቅ ጠበቀ ሁልጊዜ መጻሕፍትን በማንበብ ያስተምራቸው ነበር ይልቁንም በሰንበትና በበዓላት ቀን።
የሹመቱም ዘመን ጸጥታና ሰላም ነበረ ቤተ ክርስቲያንም በሰላም ኖረች በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበርም ላይ ዐሥራ አንድ ዓመት ተኩል ከኖረ በኋላ በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑርለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️