🕊 † የናግራን ሰማዕታት † 🕊
በ፮ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ናግራን [የአሁኗ የመን] የክርስቲያኖች ሃገር ነበረች:: የሳባ ግዛትን የእኛ ነገሥታት ሲተዋት የተተካው ፊንሐስ ደግሞ ጨካኝ አይሁዳዊ ነበርና ናግራንን ሊያጠፋት ተመኘ:: ቀጥሎም "ሃገራችሁን ልጐብኝ" ብሎ በማታለል ገባ::
ወዲያውም ሕዝቡንና ካህናትን ሰብስቦ "ክርስቶስን ካዱ" አላቸው:: ጽኑ ክርስቲያኖች ግን "አይደረግም" አሉት:: እርሱም ሊያስፈራራቸው አስቦ ፬ ሺህ ያህል ካህናት: ዲያቆናትና ምሑራንን ጨፈጨፋቸው::
ይሕንን አድርጐ "አሁንሳ?" አላቸው:: ሕዝቡ ግን አሁንም "ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን የለም" አሉት:: [ሮሜ.፰፥፭] ጨካኙ ፊንሐስም እንደ ገና ከሕዝቡ መካከል ከ፬ ሺህ ፩ መቶ በላይ የሚሆኑትን ጨፈጨፈ::
ታላቁን ቅዱስ ሒሩትንም [የሕዝቡ መሪ ነው] ብዙ አሰቃይቶ ሰየፈው:: ሚስቱን ቅድስት ድማሕንም ፪ ሴት ልጆቿን ሰይፈው የልጆቿን ደም አጠጧት:: ከዚያም ሰየፏት:: ይሕንን የተመለከቱ የናግራን ክርስቲያኖች ግን ስለ መፍራት ፈንታ በፈቃዳቸው እየተሯሯጡ ወደ እሳትና ሰይፍ ተሽቀዳደሙ::
ከተማዋም እየነደደችና ደም እየፈሰሰባት ለ፵ ቀናት ቆየች:: ይሕንን የሰማው ቅዱሱ አፄ ካሌብም ደርሶ የተረፉትን ሲታደግ ፊንሐስን ከነ ወታደሮቹ አጥፍቶታል::
አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::
🕊
[ † ኅዳር ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፪. አቡነ ሃብተ ማርያም ንጹሕ
፫. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
፬. ቅዱስ ሒሩት አረጋዊ
፭. ቅዱሳን ቢላርያኖስ: ኪልቅያና ታቱስብያ [ሰማዕታት]
፮. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘደሴተ ሰንሲላ
፯. ቅድስት ዮስቴና ቡርክት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፪. ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
" እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና:: ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም::" [መዝ.፴፮፥፳፰-፴፩]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo