ቃል ኪዳን.. ምልክት.. ምሥጢረ ጥምቀት
እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ሁሉ ጋር እርሱ እንደሰጣቸው ትዕዛዝ እና መንገድ እስከሄዱ ድረስ መልካም ነገርን እንደሚሰጣቸው ቃል ኪዳንን እንደሰጣቸው የብሉይም የሐዲስም መጽሐፍት ያስረዱናል፤ ቃል ኪዳን ባለበት ሁሉ ደግሞ የቃል ኪዳን ምልክት የሆነ ነገር ምንጊዜም አብሮ አለ፤
እግዚአብሔር ኖኅን በመርከብ እንዲድን ካደረገው በኋላ "ከዚህ በኋላ ምድርን ዳግመኛ በንፍር ውሃ አላጠፋትም" አለ፤ ለዚህ ምልክትም አድርጎ ቀስተ ደመናን በሰማይ ላይ አሳየው፤
አብርሃምን ከቤተሰቦችህ ተለይተህ ውጣ እኔም ወየማሳይህ ምድር ሂድ ካለው በኋላ፤ ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ምድር አሸዋም አበዛዋለሁ አለው፤ በእኔ እና በአንተ መሀል ምልክት ይሁነንም ብሎ ግዝረትን ምልክት አድርጎ ሰጠው፤ ... ሌሎቹም እንዲህ
በሐዲስ ኪዳን ላለን ክርስቲያኖች ደግሞ ዘላለማዊ ደስታ ወደምናገኝባት ርስታችን መንግስተ ሰማያት እንደሚያስገባን “በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤" — ዮሐንስ 3፥36 እያለ ይህን ቃል ኪዳን ሰጥቶናል፤ ለዚህ ቃል ኪዳን መፈጸምም ምልክት ተደርገው ብዙ ነገሮች ተሰጥተውናል፤ እነርሱን ስናይ እነርሱን ስናስብ ይህን የዘላለም ሕይወት ተስፋ ቃል ኪዳን ልብ የምንልባቸው ማለት ነው፤
ከእነዚህ ምልክቶች ሁሉ የመጀመሪያዋ የነቢያት ሁሉ የትንቢታቸው መፈጸሚያ፤ ከውድቀታችን ለመዳን ምክንያት የሆነችን፤ የጨለማው ዘመን ማብቂያ ምልክት የሆነችው እመቤታችን ናት፤
ሌሎቹ ምልክቶች ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ብላ ቅድስት ቤተክርስቲያን የምትፈጽማቸው የዘውትር የአገልግሎት አካሎቿ ናቸው፤ ዛሬ ይህን ሐሳብ በዋናነት ለማንሳት ምክንያት የሆነን ደግም ከእነዚህ ምሥጢራት አንዱ የሆነው ምሥጢረ ጥምቀት ነው፤
ቅዱስ ኤፍሬም በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ያሉ ንባባትን በሚደንቅ አተረጓጎም እያስቀመጠ ይተረጉማል፤ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ደግሞ በቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ውስጥ የሚገኘውን ጥቅስ የተረጎመበት መንገድ ነው፣
‘ከጭፍሮች አንዱ የኢየሱስን ጎን በጦር ወጋው ወዲያውም ደምና ውኃ ወጡ።” (ዮሐ. 19፡34)
'ጎኑ' እና 'ጦር' ለቅዱስ ኤፍሬም ወደ ኦሪት ዘፍጥረት የመክፈቻ ምዕራፎች፣ የአዳም 'ጎን' በተአምር ሔዋንን የወለደችውን እና 'ጦር' የወደቁትን አዳምንና ሔዋንን የገነትን መግቢያ የከለከለውን 'ሰይፍ' ይጠቁማሉ። በሌላ በኩል፣ ‘ደሙና ውኃው’፣ ወደ ምሥጢራት ይጠቀማሉ፣ እነዚህም ምስጢረ ጥምቀትና ምስጢረ ቁርባን ናቸው፤
ስለዚህም የአዳም ጎን፡ ሔዋንን እንዳስገኘ ፡ የክርስቶስ ጎን ፡ ቤተ ክርስቲያን አስገኝቷል።
የአዳም ጎን ካስገኘችው ሔዋን ጋር የእባቡን ክፉ ምክር በመስማት የመጀመሪያዎቹ ጥንዶች ከመጀመሪያው ‘የክብር ልብሳቸው’ ተገፈው ከገነት ተባረሩ፣ በምትሽከረከረው በምትገለባበጥ የእሳት ሰይፍም ተጠብቀዋል።
ሁለተኛው መሳሪያ ይህንን ጉዳት የሚያስተካክለው ሌላኛውን ጎን በመውጋት ነው ፣ ከዚያም 'የሚፈሰው' (ኤፍሬም አንዳንድ ጊዜ ሆን ብሎ 'ከዮሐንስ 7፡38 የተወሰደ ፍሰት የሚለውን ቃል ይጠቀማል) [“በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈሳል ብሎ ጮኸ።” — ዮሐንስ 7፥38 ]
ኃጢአትን የሚያጥቡ እና ዳግም የመግባት እድልን የሚፈጥሩ ሁለቱ ምሥጢራት ፤ የተጠመቁት ሁሉ ወደ ገነት ገብተው ክርስቶስ የሕይወትን ዛፍ እንዲመገቡ አስችሏቸዋል፣ አዳምና ሔዋን በውድቀት ያጡትን ያን 'የክብር ልብስ' ለብሶ ጥምቀት ዳግመኛ አልብሷቸዋል።
ቅዱስ ኤፍሬም መዝሙር በእንተ ልደት በተባለ ድርሳኑ ላይም እንዲህ ይላል
« ከገነት አጠገብ ሰይፍ የሕይወትን ዛፍ ሲዘጋ ያየ መሐሪ የተባረከ ነው; መጥቶ የቆሰለውን ሥጋ ለራሱ ወሰደ፥ ስለዚህም በተወጋው ጎኑ ወደ ገነት የሚያስገባውን መንገድ ከፈተ። »
ይህ ጥቅስ ለቅዱስ ኤፍሬም ምን ማለቱ እንደሆነ በሚከተለው ውብ ቃላት ሊጠቃለል ይችላል።
“ ወደ እጅና እግርህ ሁሉ ሮጬአለሁ፣ እናም ከነሱ ሁሉንም አይነት ስጦታ ተቀብያለሁ። በሰይፍ በተወጋው ጎንህ በሰይፍ ወደታጠረው የደስታ ቦታ ወደ ገነት ገባሁ። በተነቀለው የጎድን አጥንት ምክር(በሔዋን ምክር) ተገፍተናልና በተለወጠው በኩል እንግባ። በአዳም ላይ የተቃጠለ እሳት በዚያ የጎድን አጥንት አቃጥሎታልና; ስለዚህም የሁለተኛው አዳም ጎኑ ተወጋ ከእርሱም የቀዳማዊ አዳምን እሳት ሊያጠፋ የሚፈስ ውሃ ወጣ። ”
ስለእኛ ሲል ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ አቅርቦ ከጎኑ በፈሰሰ ደም የንጽሕና የቅድስና ጥማችንን ላረካ ለሚያረካልን፤ ከጎኑ በፈሰሰ ውሃ የራሱ፡ የአብ ፡ የመንፈስ ቅዱስም ልጅ አድርጎ ላከበረን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይሁን!!!
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ፤
መልካም በዓል
ጥር ፲ ፳፻፲፯ ዓ.ም
፭ ኪሎ
አ/አ
✍🏾 ሐቢብ ጊዮርጊስ
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo