ሚስቴ ፒዛ በጣም ትወዳለች፡፡ (ፈረንጅ አይደለችም...እነሆ ፒዛ የሚወዱና የሚከተክቱ ሃበሻ ሚስቶች በከፍተኛ ሁኔታ ቁጥራቸዉ ጨምሯል!) አንድ ጊዜ ቤት ፒዛ ይዛ መጣች🍕🍕
እኔም እሷም በላን፣ አንድ ዘለላ እስኪቀረዉ ድረስ በላን፡፡ ጠግቤ ስለነበር ሄጄ ተኛሁ፡ እሷም እንደዚሁ ጠግባ ነበር፡፡ የሚቀጥለዉ ቀን ወደስራ ልሄድ ስል ዉሃ መጠጣት እንዳለብኝ ስለተሰማኝ ፍሪጁን ከፍቼ ሳይ ፒዛ ሆዬ ዱቅ ብሏል፡፡ ምንም ሳላደርግ ዉሃዬን ጠጥቼ ዉልቅ፡፡
ማታ ከስራ ስገባ ሚስቴ ቤት አልነበረችም፡፡ ስለራበኝ የሚበላ 😏 መሶቡን ብከፍት ድስቱን ብከፍት ወፍ የለም! ኤጭ አሁንስ!😏😏
ያቺ ፒዛ ትዝ አለችኛ! አዉጥቼ እየከተከትኩ ሚስት ከች! እንደራባት ታስታዉቃለች፡፡ ልክ የመጨረሻዉን ጉርሻ ስጎርስ ከለመችኝ! አቤት ፊቷ ፍም መሰለ! በቃ እሳት ፊቷ ላይ ነደደ ብል ይቀላል፡፡😡😡😡
• እሷ፡ “አንተ ለምን በላኸዉ?”
• እኔ፡ “ምኑን?”🤔
• እሷ፡ “ምኑን ይላል እንዴ!”😡
• እኔ፡ “አልገባኝማ?”
• እሷ፡ “ሰምተሃል! ፒዛዉን ለማን በላኸዉ??”😡
• እኔ፡ “መልእክት ደርሶኝ ነዉ”
• እሷ፡ “የምን መልእክት?”🤔
• እኔ ፡ “ከሆዴ! ፒዛዉን ወደታች ቤት እንድልከዉ አስቸኳይ ጥሪ ቀርቦልኝ ነዉ፡፡ ያንቺም ሆድ ጥሪ አቀረበ አይደል...ትሪውን ሰቅዬዋለሁ በዪዉ”😂😂
• እሷ፡ 'ሆዳም ቀልደህ ሞተሃል!😡 እኔ ልበላዉ መስሎህ ነዉ? ባክህ ልነግርህ የፈለኩት ጠዋት ፍሪጁን ሳልዘጋዉ ከፍቼዉ ጓዳ ሄጄ ድመቱ እየላሰዉ ነበር'😔😔
• እኔ ፡'እእእ... ወይኔ ጉድ...ጉድ!!” አቅለሸለሸኝ!😝😭😭
• እሷ፡ “ባክህ አዉቄ ነዉ! ጮማ ራስ!”😂😂😜😜
•እኔ ፡ “አንቺ !!!!”😡😡
...
...
✎semir ami 😍😁