የግጥም ቃላቶች


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ጥበብ እንደ ጥጥ ነው ለጉድ ተፈልቃቂ
ሰው ጥሩ ፈታይ ነው ድር ማግ ግን አላቂ

ስለ ግጥም ብላቹ @buchula36 ላይ አዋዩኝ
የናንተ ድምፅ ነው ለኔ እውቀት የሆነኝ
.
.
.
@buchula36
@yegetemkalat
@ortodox_fkr

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


የዘመኑ ይሁዳ

ከዘመናት በፊት ሞተ የተባለው
እያቀፈ ስሞ አምላኩን የሸጠው
ያ ለሰላሳ ዲናር ነብሱን የዘነጋ
ይሁዳ አልሞተም አለ ይኸው እኛ ጋ

የሞተ ቢመስለን እንዲያው ያበቃለት
ተቀቶ የሚኖር ሲኦል ባለው እሳት
የሞተው እሱ ነው ሀሳቡ ተላልፏል
የዘመኑ ይሁዳም ስራውን ጀምሯል

ተዋህዶ ማለት የሀገር ምሰሶ ናት
በሀገር ያለው ሁሉ ህዝቡ የሚያከብራት
ብሎ በአንደበቱ ሲደሰኩር ኖሮ
ወንበሩ ሲመቸው ፈጠረ አምባጓሮ

ይከፋፈል አለ ሀይማኖት እንደ ቅርጫ
በብሄር በጎሳ ይሁን መጫወቻ
አንደበቱ አራምባ ተግባሩ ቆቦ ነው
በቅቤ ምላሱ ህዝቡን አታለለው
ተደመር እያለ አካፍሎ ገደለው

ማህተብ አልፈታ ያለውን በሙሉ
በጥይት በክላሽ ሲያበቃ ዘመኑ
ድምፁን ሰቶ ሁሉ እሱ ይምራን ባለው
ልምራህ እኔ ብሎ ከአፈር ደባለቀው

ይለያል መንገዱ አያስጠረጥርም
ጉንጭኮ አደለም ይኸኛው ይሁዳ እግር ነው የሚስም
አጎንብሶ ሲስም መስሎን ያከበረ
ሲተበትብ ቆየ መጥለፊያ እያሰረ

ሁሉንም ለመናድ ከስር መሰረቱ
ቢገፋ ቢገድል ቢሆንብን ብርቱ
ማህተብ አንበጥስ ለአህዛብ አንገዛ
ሲገፋን ሲገሉን ነንኮ የምንበዛ

ንገሩት ለዛ ሰው ለዘመኑ ይሁዳ
ፈገግ ብሎ ስሞ ሀገሩን ለከዳ
እንደው ላይቻለው ተዋህዶን ሊያጠፋ
ሰራዊት በመላክ በመግደል አይልፋ
ፀንታ የምትኖር ነች ዘላለም በእምነት
በምድራዊ ሀይል የማትፈርስ አለት

                 ✍ቤዛዊትድሪባ
                      (የተክልዬዋ)

@yegetemkalat
@poem_merry


እንዲቀልህ 2

🔥ከጓደኞችህ ጋር ያለህ መስተጋብር ምን ይመስላል?
ስላንተ ምን ያህል ቦታ አላቸው???? ንግግርህን ምን ያክል ይሰሙሀል???? ስሜትህን የቱን ያክል ይረዱታል???? ፍላጎትህን ምን ያክል ያስቀድሙልሀል??? ቁጣህን እስከየት ይታገሱሀል????
🪄 በነዚህ ውስጥ የምታገኘው መልስ ሁሉ ትክክል ካልሆነ ራስህን ከዚህ ግንኙነት አርቅ። ኖሮ ያልጠቀመ ሄዶ አይጎዳምና አዳዲስ ሰዎችን ልመድ ለራስህ ባለህ ክብር ልክ ግንኙነቶችን መስርት ....መስመርህን ለሚያልፍ ምህረት አይኑርህ !!!!...ጠንካራነት ስምህ ብቻ አይሁን ማንነትህም  አድርገው ሰው ባይኖርህ እንኳን ብቻህን ታምራለህ ከሚንቁህ ጋር አትወዳጅ።


©ማኪ

✎semir ami


ፈልጌህ ነበረ...

 ፈልጌህ ነበረ..
ብዬ እንዳላወራ..
የታማሁለት ፍቅር እንዲ ሆኖ ቀረ
ልቡን ባገኝ ብዬ ስደክም ስለፋ
አንተን አገኝ ብዬ ከራሴ እስክጠፋ
ባልዋልኩበት ውዬ ያልሆንኩትን ሆኜ
መውደድክን ፍለጋ ለፍቼ ኳትኜ
ይወደኛል በሚል የቁም ቅዠት ሞቼ
ላለመገኘትህ ተስፋዬን ሰውቼ
ባንተ ክህደት ሰበብ ማፍቀር እርም እስከምል
አልደግመውም ብዬ በ እመቤቴ እስክምል
ይሄ ሁሉ ሳይሆን ልቤ ሳይሰበር
ያልሆንኩትን ሆኜ ስፈልግህ ነበር...

                                                    ✍️  ኤልሳ[FB]

ለተጨማሪ ግጥሞች 👉👉👉 @Fkerofficial


@yegetemkalat
@poem_merry


በውሸተኛ ፎቶ ላይ የተመሰረተ እውነተኛ ታሪክ ክፍል #2(semir ami)😍

ቀጥሬም አልቀረው መርጠን አንዱን ስፍራ
         ተቀምጠን አወራን
አወራን አወራን ግማሽ ኪሎ ሀሚት ግማሽ
             ፖለቲካ
    ደስ ሲለን ታሪክ ሲያሸን ሰበካ
እንደው ሳናስበው ሰአቱ ነጉደ...
አይን አይንዋን እያየው አይን አይኔን አየችኝ
  በፍቅርዋ ከንፍ መውደድዋን ሰጠችኝ
በርዱን ይሆን ሳናቀው ብቻ ተቃቀፍን
የመፍራትን መንገድ አንድ እርምጃ አለፍን
እሷ ልሆን እኔ ማን እንደቀደመ
         ባላስታውሰውም
ብዙ እንደሳምኳት ብዙ እንደሳመችኝ ፍፁም
             አረሳውም
መጠጥም ቀመስን አንድ ሁለት አልን
  ብዙም ሳንቆይ ስካር አሸነፈን
አብረንም አደርን አንሶላ ተጋፈን
በጣሙን   ተገረምኩ በአብረን ማደራችን
የሰው ተፈጥሩ ግን እጅጉን ይገርማል
ካልጠበቀው ስፋራ ሳያስብ ይውላል
ከአይምሮ በላይ ስሚቱን ይሰማል
የሰውነቱ መለክያ ባዳሩ ይለካል
ብቻ አስታውሳለው ለኔ ያላት መውደድ ለኔ
             ያላት ክብር
ለኔ ያላት መሳሳት ያላት ግዙፍ ፍቅር
ባይኔ ውልብ ይላል....
ምን ነካት ሳልላት ዞራ ተቀየረች
እኔን የሚባል ሰው አይንህ ላፈር አለች
ምትወደኝ ያህል አግዝፍ ጠላችኝ
ከረሱኝ እንደምረሳ እሷም ዘነጋችኝ
እኔ ግን ያው ሆኜ ግራ ስትሰጠኝ ቀኝ
         እየ ሰጠዋት
የኩራትዋን ያህል እኔም ተማፅንኳት
ከሷ ልብ አባራኝ ከኔ ልብ አኖርኳት
ከአሁን መቀየርዋ ድርዋን አመንኳት።


ይቀጥል ባትሉም ይቀጥላል.....




😂"ነገረኛ" ብለሽ እኔን ስትሰድቢ
ሐበሻ መሆኔን ምናል ብታስቢ።

"በነገነራችን ላይ"

በሚል መንደርደሪያ
ዲስኩር ማሳመሪያ
የንግግሩን ውል በሚቀምር ሀገር
እንደምን ይቻላል መኖር ያለነገር።

              semu ami😍😍


በውሸት ፎቶ ላይ የተመሰረተ እውነተኛ ታሪክ
(Semir ami) ክፍል #1

ከለታት አንድ ቀን...
በቆንጅናዬ እጅጉን ተገርማ
በፀባዬ ማማር የኔ መሆን አልማ
ከጕደኞቺ መሀል አንዱን ትግባባለች
እንዴትም ለምናው ቁጥሪን ወሰደች
ደወለች እኔ ጋር አመሻሽ ጠብቃ
ደዋይ ለሌለው ስልክ ሆናለት ጠበቃ
ሂለው አልኩኝ እኔም የማላውቀው ቁጥር ማን  
                ይሆናል ብዬ
በለሰለሰ ድምፅ አፍን አባብዬ
ወሪውን ቀጠልን እጅግ የከረመ ወዳጆች
               መሰልን
ብዙ ሰአት አወራን ከድምፅዋ ውጭ     ምንዋንም  አላውቀው
አትጥፍ አለችኝ ቻው ተባብለን ስልኩንም
              ዘጋነው.
     ከለታት ሁለት ቀን......
ቲክስት ላከችልኝ ልዩ ሰው ነህ ብላ ባወራን
                   ማግስት
ልዩ ሰው አያደለውም አንድ ሰው ነኝ ብዬ
         እኔም መለስኩላት
ቀልዴን አልነበረም እሷን ግን አሳቅኳት
ባህሪህ ስርአት ሳትስቅ ምታስቅ
የድብርት መፍትሄ ደስታን ምታፈልቅ
ብላ አሙገሰችኝ ቃላቶች ደርድራ
እሷ ላወራችው አልነገርኳትም ግን
          የኔ ፊትም በራ
ከለታት ሶስት ቀን.......
ማውራታችን ዳብሩው ሙገሳው ደልቦ
ድንገት በመሀል  ላይ እንገናኝ አለች
በስልክ ያወራነውን በተግባር ፍለገች
እኔ ደሙ ኩራው ማግኘት ብፈልግም
እስከዚ ነው ብዬ የተፈላጊ አቅም
እሷም አኩረፈች በኔ እንቤ ባይነት
   መደወል አቁመች
እኔም በዛው ጠፍው
አውቁ የተደበቀ አይገኝም ብዬ
እሷን ምትባል ሴት ከአይምሮዬ ጥዬ
ድንገት ስልኬ ጠራ ሳነሳው እሷ ናት
አወራች በፍቅር ንዲትዋ በርዱላት
ለምን እንዲ ጠፍ ብላ ጠየቀችኝ
ከረሱኝ እንደምረሳ እሷም አወቀችኝ
ደግማ ጠየቀችኝ እንገናኝ ብላ
       በፍቅር አባብላ
ቃልም አስገባችኝ በናቲ አስምላ
     እኔም እሺ አልኩት
ዝም ካለ ስፍራ መርጭ ቀጠርኳት።

ይቀጥል ካላቹ ይቀጥላል .......inbox ንገሩኝ @semirami




ረፍዷል

ፈልጌህ ፈልጌህ አንተነትክን ሳጣ
ከፍቅርህ እብደት ጥግ ቆርጬ ስወጣ
አድቀህ ሰባብረህ እንደቀልድ አይተኸው
የገፋኸው  ልቤን በመርሳት ሳክመው..
ዳግም አትመለስ ያንተ ፍቅር ሄዷል
አትልፋ አትድከም ብትመጣም ረፍዷል
       
                                              ✍ኤልሳ[FB]
👉👉👉 @fkerofficial


@yegetemkalat
@poem_merry


🖤😞

የሆነ የማታውቁት ቦታ ላይ ተገኝታችሁ የእንግድነት ስሜት ተሰምቷችሁ አያውቅም????? ለቦታው የምታንሱ አይነትስ???? አላፊ አግዳሚው ሁሉ አዲስ መሆናችሁን የሚያውቅ መስሏችሁስ አያውቅም???? ከዛ ቦታ የምትወጡበት ሰአትዝ አልረዘመባችሁም???   ሰአቱ መቁጠሩን ያቆመ ይመስል ቀጥ አላለባችሁም????   እንደዚ ያለ ነገር ገጥሟችሁ አያውቅም????

ለኔ ግን ተሰምቶኝ ፣ገጥሞኝ  ያውቃል??

© maki

✎semir


ስም አውጪ ወዛዝርት
ገና ስትወለጅ አበባ ያሉሽ 'ለት
ይህ ነው ኮቴ ማድመቅ
ይህ ነው ቅጥፈት ማለት

ዮኒ-ኣታን @Yonny_Athan

@yegetemkalat
@poem_merry


ሚስቴ ፒዛ በጣም ትወዳለች፡፡ (ፈረንጅ አይደለችም...እነሆ ፒዛ የሚወዱና የሚከተክቱ ሃበሻ ሚስቶች በከፍተኛ ሁኔታ ቁጥራቸዉ ጨምሯል!) አንድ ጊዜ ቤት ፒዛ ይዛ መጣች🍕🍕

እኔም እሷም በላን፣ አንድ ዘለላ እስኪቀረዉ ድረስ በላን፡፡ ጠግቤ ስለነበር ሄጄ ተኛሁ፡ እሷም እንደዚሁ ጠግባ ነበር፡፡ የሚቀጥለዉ ቀን ወደስራ ልሄድ ስል ዉሃ መጠጣት እንዳለብኝ ስለተሰማኝ ፍሪጁን ከፍቼ ሳይ ፒዛ ሆዬ ዱቅ ብሏል፡፡ ምንም ሳላደርግ ዉሃዬን ጠጥቼ ዉልቅ፡፡

ማታ ከስራ ስገባ ሚስቴ ቤት አልነበረችም፡፡ ስለራበኝ የሚበላ 😏 መሶቡን ብከፍት ድስቱን ብከፍት ወፍ የለም! ኤጭ አሁንስ!😏😏

ያቺ ፒዛ ትዝ አለችኛ! አዉጥቼ እየከተከትኩ ሚስት ከች! እንደራባት ታስታዉቃለች፡፡ ልክ የመጨረሻዉን ጉርሻ ስጎርስ ከለመችኝ! አቤት ፊቷ ፍም መሰለ! በቃ እሳት ፊቷ ላይ ነደደ ብል ይቀላል፡፡😡😡😡

  • እሷ፡ “አንተ ለምን በላኸዉ?”

  • እኔ፡ “ምኑን?”🤔

  • እሷ፡ “ምኑን ይላል እንዴ!”😡

  • እኔ፡ “አልገባኝማ?”

  • እሷ፡ “ሰምተሃል! ፒዛዉን ለማን በላኸዉ??”😡

  • እኔ፡ “መልእክት ደርሶኝ ነዉ”

  • እሷ፡ “የምን መልእክት?”🤔

  • እኔ ፡ “ከሆዴ! ፒዛዉን ወደታች ቤት እንድልከዉ አስቸኳይ ጥሪ ቀርቦልኝ ነዉ፡፡ ያንቺም ሆድ ጥሪ አቀረበ አይደል...ትሪውን ሰቅዬዋለሁ በዪዉ”😂😂

  • እሷ፡ 'ሆዳም ቀልደህ ሞተሃል!😡 እኔ ልበላዉ መስሎህ ነዉ? ባክህ ልነግርህ የፈለኩት ጠዋት ፍሪጁን ሳልዘጋዉ ከፍቼዉ ጓዳ ሄጄ ድመቱ እየላሰዉ ነበር'😔😔

  • እኔ ፡'እእእ... ወይኔ ጉድ...ጉድ!!” አቅለሸለሸኝ!😝😭😭

  • እሷ፡ “ባክህ አዉቄ ነዉ! ጮማ ራስ!”😂😂😜😜

  •እኔ ፡ “አንቺ !!!!”😡😡
...
...
✎semir ami 😍😁


Forward from: ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚
44,000member ያለው የቴሌግራም ቻናል መግዛት የምትፈልጉ በውስጥ መስመር @asrategabriel ላይ አናግሩኝ እውነተኛ ገዢ ብቻ owner በታማኝነት እናስተላልፋለን!


የሬዲዮ ስራ - ፈጠራ፣ ጥልቅ ንባብ፣ ጄነራል ኦብዘርቬሽን፣ ተመስጦ፣ አድማጭ አዕምሮ ውስጥ ምስል የመፍጠር ብቃት ምናምን ምናምን ይጠይቃል።

በዘመድ አዝማድ ተሰባስቦ የጉጎል ታሪክ መተርጎም፣ የቲዊተር አጀንዳ ማራገብ፣ የቴሌግራም እና ፌስቡክ ስነ ፅሁፍ ማንበብ፣ ድምፅ አወፍሮ የዘይት ማስታወቂያ ማነብነብ፣ ማንም ሰው ኢንተርኔት ላይ የሚያገኘውን የአውሮፖ ሊግ እንደ ቁራ እየጮኹ ማስተጋባት አይደለም።

¤

ሬዲዮ ኢትዮጵያ ውስጥ ዳዴ ብሎ የሞተ ሞያ ነው። ቢደብርህም ሐቁ ይሔ ነው።


Semir ami✍✍✍


አዲስ ግጥም
ግጥሙን ለማግኘት ይላቀሉን 👇
@fkerofficial


ጠባቂሽ. . .


ደህና ነች
ዛሬም እንደፊቱ ደምቃለች ፈክታለች!
የውበት አምባ ጥግ የሄዋን ተምሳሌት
የመዋደድ ጣዖት የፍቅር አማልክት
አንቺ...
አንቺ በመውደድ ጥምዝምዝ አስረሽ የማትፈቺ
የአይኖቼ ጥም ሀሩር የማትሰለቺ
እስቲ እንደው ገምቺ...
እስቲ እንደው ገምቺ ...
እንዴት ባለ ምትሀት እንዴት ባለ ታምር
የሰው ቀልብ አርፎብኝ እንደዛ የማምር
የእውቀቶች ባለቤት ባለብዙ ተስፋ
አይሽ እንደሁ ብዬ ሰርክ የምለፋ
ዛሬ እንዴት እንደሆንኩ የሸርፍ ተራ ሰው.
ሌላ ምንም አይደል
ውለሽ ስትገቢ ባይኔ እንድታልፊ ነው
ከሸርፍ ተራው ጥግ እጠብሻለሁ
የሰው ብትሆኚም ዛሬም አይሻለሁ
ዛሬም ደህና ነሽ.. ዛሬም አምሮብሻል
ህይወት ቀንታሻለች  ወልደሻል ከብደሻል

ጊዜ አልለወጠሽ እድሜ አልወጠነሽ
ማሻላህ ደህናነሽ
የዘመን ባዘቶ መች ይቀይርሻል
ወላሂ አምሮብሻል
ሳታውቂው ማፍቀሬን እስከመፈጠሬም
አልሃምዱሊላህ ትስቂያለሽ ዛሬም
ገርጅፎ ያልጃጀ በፍቅር ያሳደገሽ
በልጅነት ልቡ ወዶ የፈለገሽ
መስዋዕት ሳያሻው ራሱን የከፈለሽ
ተርቦ ማይጠግብ ድብቅ ፍቅር እንዳለሽ
እንኳን ስሜን መልኬን   አንቺ መች ታውቂያለሽ..
ብቻ... ምንም ቢሆን
ህመሜ ተሰምቶሽ ልምጣ ያልሽ እንደሆን
እንደጠዋት ጀምበር ዘወትር ናፋቂሽ
የማታውቂው እውነት የፍቅር ደባቂሽ
ካስቀመጥሺኝ ቦታ አለሁኝ ጠባቂሽ


                                                     ✍ኤልሳ[FB]

JOIN 👉👉👉 @Fkerofficial

@yegetemkalat
@poem_merry


Forward from: Unknown
የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ለምንዘገየ እና  ተያያዥ ዜናዎችን አሁንኑ ከንቁ የተዋሕዶ ድምፅ ቻናል ያግኙ
ሙሉ መረጃ ለማግኘት
👇🏾👇🏾👇🏾
https://t.me/+ULytP9NXh6o2ZDdk
https://t.me/+ULytP9NXh6o2ZDdk
https://t.me/+ULytP9NXh6o2ZDdk


አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?


እንደትላንት ተወልደን ዛሬ ላይ እድሜያችን ስንት ደረሰ? ወጣትነታችን ወደ ፊት የሚያራምደን መስሎን ተሞኘን። ዕቃቃችንን ስንጥል፥ ጨዋታችንን አልጠገብንም ነበር። ድክ፥ ድክ ያልነው በወጉ ዳዴ ሳንል ነው። ልባችን ላይ የሚነደው የጉርምስና እሳት ደረታችንን ሲፋጅ ሰፊ መንገድ ያለ መስሎን ነበር።


አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?


ከአባታችን ወገብ የተከፈለው ዘር፥ በእናታችን ማኅጸን እንቁላል ሳይመታ፤ ፅንስ ሳንሆን፥ ሥጋችን ሳይቦካ፥  አጥንታችን ሥር ሳይሰድ፥ ጅማታችን ሳይዘረጋ፥ ሽል ሳንሆን በፊት. . . ክፉ ዕጣ ቀድሞናል። አንዳችን ለአንዳችን ጠላት ተደርገናል። ለሞትም ታጭተናል። ሳንመርጥ ወግነናል። ደርሰን ባልበደልነው፥ ባልሠራነው ታሪክ. . . አክ እንትፍ ተብለናል።


አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?


እኔና አንተ ምንም እንኳ ወደ ፊት መጓዝ ብንፈልግም፤ ይሄ ሀገር የሚሄደው ወደ ኋላ ነው። ዳገቱን ወጣን፥ አቀበቱን አሸነፍን፥ ተራራውን ረታን ስንል. . . እየተንሸራተተ መቀመቅ ይዞን ይወርዳል። በየቀኑ ትርጉም አልባነትን እንድናንከባልል ተፈርዶብናል።


አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?


አናምንም። ግን ዕውቀት የማይዘልቀው የድንቁርና እና የአረመኔነት ዘረመል ሥጋ ለብሶ ያለው እዚህ ሀገር ነው። ኅዘንተኞች ሳለን መጽናኛ የለንም። ፍርፋሪ እሴት ሳይቀር ነጠቁን። ረክሰው አረከሱን። የሤራ ፖለቲካው ጉንጉን ፈጣሪ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበብ በላይ ሳይረቅቅ አይቀርም። እግዚዖ!


አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?


ከተወለድን ጀምሮ አላስተኙንም። ታዲያ  ሕይወታችን ስለምን ቅዠት በቅዠት ሆነ? ማለት  መቼ አስተኝተውን? መቼስ ተደላድለን? እስከ መች እንደምንኖር አናውቅም። ሕይወት አጭር ናት፤ እዚህ ሀገር ደግሞ እጅግ በጣም አጭር ናት። ሕልውናችን ከእኛ ቁጥጥር ውጪ ነው። ብንነቃም፥ ብናንቀላፋም ሕይወት ጭራቅ መልኳን ለአፍታ አትቀይርም። የቸገረ ነገር!


አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?


እንዴት እንደሆነ ባናውቅም እንደ ትውልድ አምክነውናል። ሳንወለድ ገድለውናል። የእናት ጡት ሳንጠባ አስረጅተውናል። ቆምረውብናል። ቅያሜውን ሳናውቅ፥ ጦርም ሳንገጥማቸው፥ ያለ ወግ ድል አድርገውናል። ያረፈብን የጀግናም አይደለ፥ የፈሪ ዱላ ነው!


አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?


ዳሩ ምርጫ አልነበረን


"ስንት አግብተሽ ፈታሽ"
Semir ami✍

... ልትቋቋመዉ ከምትችለዉ በላይ ልቧ ወደሱ ሸፍቷል። አግብቷት እድሜ ልኳን ከሱ ጋር ብትኖር ምኞቷ ነዉ። አሁንም ወደፊትም አላማዋና ፍላጎቷ እሱ ብቻ ነዉ።

የሱ ስልክ ሲጠራ መታገስ አትችልም። በፍጥነት ታነሳዉና ድምጹን ለመስማት ወደ ጆሮዋ ታስጠጋለች። "ሄሎ የኔ ልዕልት" ሲላት አለምን በሷ ግዛት ስር አድርጋ ንግስት የሆነች ያክል ይሰማታል።

"የኔ ... ዛሬ ማታ እፈልግሻለሁ .. እንገናኝ!" አላት። በደስታ ልቧ ቦታዋን ለቃ ፈነጠዘች። ለዛሬ ማታ የምትለብሳቸዉን ለብሶች መምረጥ የጀመረችዉ ስልኩ ከተዘጋ ጀምሮ ነዉ። የቱ እንደሚያምርባት፤ ማንኛዉ ዉበቷን አጉልቶ እንደሚያሳይ በመሞከር .. ስታነሳ ስትጥል ዋለች።

ቀኑ የአመት ያክል ረዘመባት። "መቼ ነዉ ነዉ ማታ የሚደርሰዉ?" በእድሜዋ ብዙ ማታዎችን ብታሳልፍም። የዛሬዉ ማታ ግን የተለየ እንደሚሆን ልቦናዋ ሹክ ብሏታል። የምትለብሰዉን ልብስ መርጣ ጨርሳለች። ከንፈሯ በስተቀኝ በኩል በቀይ ቀለም፤ በስተግራ በኩል ያለዉን ደግሞ በጥቁር ቀለም አስዉባ የጥቁርና የነጭ እኩልነት መገለጫ አስመስላዋለች። ቅንድቧን በደንብ ተኩላ፤ ድንቡሽቡሽ ያሉ ጉንጮቿን ዱቄት አብዛታበት በጠይም መልኳ ላይ ለብቻዉ ጎላ ብሎ የከረመ ቲማቲም መስሏል። ... ምንም አይወጣላትም። በስሜቱ ለሚነዳ ወንድ ታማልላለች፤ አቅሉን ያልሳተ ደግሞ እንደ አሻንጉሊት ቁጥሮ ያልፋታል።

.

... የአመት ያክል የራቀባት፤ በጉጉት ስትጠብቀዉ የነበረዉ ምሽት ደርሷል። የቀጠረባት ቦታ ስትደርስ አከባቢዉ በተለያዩ ቀለማት ባሸበረቁ ማብራቶች ተሽቆጥቁጧል። ጨረቃዋ ከላይ ከላይ አዝቅዝቃ እየተመለከተች ከእኔና ካንቺ ዉበት ማን ይበልጣል የምትል ይመስል ከአንፖሎቹ ዉበት ጋር ተደምራ ምሽቱን የተለየ ድባብ ሰጥተዋለች።

የምታየዉን ማመን አልቻለችም። በደስታ ብዛት ነፍሷ በሀሴት ጮቤ ረግጣለች። ግራና ቀኝ እየተመለከተች በተጎዘጎዘዉ ቀይ አበባ ላይ እየተራመደች ወደሱ እየተጠጋች ነዉ። እሱም ቢሆን በጣም አምሮበታል። የእሷን ወደሱ መጠጋት እየተጠባበቀ ፊቱ የደስታ ነጸብራቅ ይረጫል።

አጠገቡ ስትደርስ በጉልበቱ በርከክ ብሎ "የኔ ቆንጆ ታገቢኛለሽ" ሲል ቀለበቱን በጣቷ ላይ ሊያጠልቅላት ዘረጋ። ደስታዋ ወደር አጣ። ይሄን አልጠበቀችም። የጋብቻ ጥያቄ ይጠይቀኛል ብላ በፍጹም አልጠረጠረችም። መናገር እስኪያቅታት ድረስ ስለተደሰተች እየተንተባተበች "አዎ ... አዎ አገባሀለሁ!" ብላ የዘረጋዉን ቀለበት እንዲያደርግላት እጇን ወደሱ ዘረጋች።

"አንቺ .. አንቺ ኢክራም ተነሺ ... ተነስተሽ ሱብሂ ስገጂ" ብለዉ እናቷ ሲቀሰቅሷት ብንን ብላ ስትነሳ በህልሟ ፈክቶ የነበረዉ ፊቷ በእዉኗ ሬት እንደቀመሰ ሰዉ ጭፍግግ አለ።

"እማዬ... ምናለ ህልሜን ብጨርስ"

"ጓደኞችሽ በእዉናቸዉ ያገባሉ አንቺ በህልምሽ እያገባሽ ትፈቻለሽ። ቆይ እስካሁን ስንት አግብተሽ ፈታሽ?"


ሊለቀቅ ነው❗️❗️❗️

ጠባቂሽ! [በፅሁፍ]
አዲስ ግጥም በ ኤልሳ[FB]
ዛሬ ምሽት በ @Fkerofficial ይጠብቁን!

20 last posts shown.

42 243

subscribers
Channel statistics