ፈልጌህ ነበረ...
ፈልጌህ ነበረ..
ብዬ እንዳላወራ..
የታማሁለት ፍቅር እንዲ ሆኖ ቀረ
ልቡን ባገኝ ብዬ ስደክም ስለፋ
አንተን አገኝ ብዬ ከራሴ እስክጠፋ
ባልዋልኩበት ውዬ ያልሆንኩትን ሆኜ
መውደድክን ፍለጋ ለፍቼ ኳትኜ
ይወደኛል በሚል የቁም ቅዠት ሞቼ
ላለመገኘትህ ተስፋዬን ሰውቼ
ባንተ ክህደት ሰበብ ማፍቀር እርም እስከምል
አልደግመውም ብዬ በ እመቤቴ እስክምል
ይሄ ሁሉ ሳይሆን ልቤ ሳይሰበር
ያልሆንኩትን ሆኜ ስፈልግህ ነበር...
✍️ ኤልሳ[FB]
ለተጨማሪ ግጥሞች 👉👉👉 @Fkerofficial
@yegetemkalat
@poem_merry
ፈልጌህ ነበረ..
ብዬ እንዳላወራ..
የታማሁለት ፍቅር እንዲ ሆኖ ቀረ
ልቡን ባገኝ ብዬ ስደክም ስለፋ
አንተን አገኝ ብዬ ከራሴ እስክጠፋ
ባልዋልኩበት ውዬ ያልሆንኩትን ሆኜ
መውደድክን ፍለጋ ለፍቼ ኳትኜ
ይወደኛል በሚል የቁም ቅዠት ሞቼ
ላለመገኘትህ ተስፋዬን ሰውቼ
ባንተ ክህደት ሰበብ ማፍቀር እርም እስከምል
አልደግመውም ብዬ በ እመቤቴ እስክምል
ይሄ ሁሉ ሳይሆን ልቤ ሳይሰበር
ያልሆንኩትን ሆኜ ስፈልግህ ነበር...
✍️ ኤልሳ[FB]
ለተጨማሪ ግጥሞች 👉👉👉 @Fkerofficial
@yegetemkalat
@poem_merry