💥 ዛሬ የእመቤታችን የወላዲተ አምላክ ወርኃዊ በዓሏ ነውና የፍቅር ልጆቿ በረከቷን እንሳተፍ ዘንድ በምትወዱት የሊቃወንት የምስጋና ቃል ወይም መዝሙር በአስተያየት መስጫው ላይ በጽሑፍ ትውልድ ኹሉ ብጽዕት የሚላትን አወድሷት። በረከቷ አንዲበዛለኝ በመመኘት እኔ በሊቁ በፕሮክልዩስ ዘቁስጥንጥንያ ቃል አወደስኳት፦
❖ “ሰው ሆይ፥ ኹሉንም ፍጥረት በሐሳብኽ ቃኝና ከአምላክ እናት ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የሚነጻጸር አልያም ከርሷ የሚልቅ ነገር ይኖር እንደኹ ተመልከት። ዓለምን ኹሉ ዙር፣ ውቅያኖሶችን ኹሉ አስስ፣ አየሩን ቃኝ፣ ሰማያቱን ጠይቅ፣ ኹሉንም የማይታዩ ኃይላት ዐስብ እናም በመላው ፍጥረት ውስጥ ማንኛውም ሌላ ተመሳሳይ ድንቅ ነገር ይኖር እንደኹ ተመልከት፡፡ ወደፊት የሚኾኑትን ኹሉ ዐስብና በድንግል ልዕልና ተደነቅ። ርሷ ብቻ፥ ከቃላት በላይ በኾነ መንገድ ኹሉም ፍጥረት በፍርሃትና በመራድ ከፊቱ የሚንበረከኩለትን የርሱ የመርዐዊ ሰማያዊ ማደሪያ በሚኾን ማሕፀኗ ይዛዋለች።” (Proclus of Constantinople, Homily 5, 2)
(መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
https://youtu.be/OtCUpVTF-4M?si=W7gSvvz3foiARSoe
ሼር..............