ስለኔና አንቺ ለታዳሚው ሁሉ
በግጥሞችሽ መሃል
ግጥሞች ነን እያልሽ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ ግጥሞች ነን
ማንም የሚገጥመን
ማንም የሚደርሰን
ሲፈልግ ሚክበን ሲፈልግ ሚያፈርሰን
የገጣሚ..ግጥም
የደራሲ..ድርሰት
የወገኛ..ወግ ነን
(እኔ እና አንቺ እኮ እናሳዝናለን)
በዝብርቅርቅ ህይወት የተሞነጨርን
ሙንጭር ሙንጭርጫሪ
ልክ ነሽ ግጥሞች ነን
ሌላ ቃል አይሆንም ቃል እንዳትቀይሪ
አወደስኩኝ ብለሽ ነገርሽኝ ብሶቴን
ያንቺንም ምንነት የኔን ማንነቴን
በአንድ ፀንተን ማናውቅ
በሰው ምንዋደድ
በሰው ምንጣላ
ልክ ነሸ ግጥሞች ነን
በራሳቸው ዲስኩር
ሚመሩን በሌላ።
https://t.me/selafeker
በግጥሞችሽ መሃል
ግጥሞች ነን እያልሽ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ ግጥሞች ነን
ማንም የሚገጥመን
ማንም የሚደርሰን
ሲፈልግ ሚክበን ሲፈልግ ሚያፈርሰን
የገጣሚ..ግጥም
የደራሲ..ድርሰት
የወገኛ..ወግ ነን
(እኔ እና አንቺ እኮ እናሳዝናለን)
በዝብርቅርቅ ህይወት የተሞነጨርን
ሙንጭር ሙንጭርጫሪ
ልክ ነሽ ግጥሞች ነን
ሌላ ቃል አይሆንም ቃል እንዳትቀይሪ
አወደስኩኝ ብለሽ ነገርሽኝ ብሶቴን
ያንቺንም ምንነት የኔን ማንነቴን
በአንድ ፀንተን ማናውቅ
በሰው ምንዋደድ
በሰው ምንጣላ
ልክ ነሸ ግጥሞች ነን
በራሳቸው ዲስኩር
ሚመሩን በሌላ።
https://t.me/selafeker