⚡️በወርቅ ማምረት ሥራ ላይ የተሠማሩ የ32 አምራቾች ፈቃድ መሰረዙ ተገለፀ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል፣ የማዕድን ዘርፉ አፈጻጸም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ አስታውቋል።
በክልሉ ከሚገኙ 58 ልዩ አነስተኛና 12 ባሕላዊ የወርቅ አምራቾች መካከል አፈጻጸማቸው ደካማ የሆኑት 32ቱ ፈቃዳቸው መሰረዙ ተገለጿል ።
የክልሉ የማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ሰጠኝ በስድስት ወራት ውስጥ ምንም ዓይነት ወርቅ ማምረት ያልቻሉ 12 ልዩ አነስተኛና ሁለት ባሕላዊ አምራቾች አሉ። አሳማኝ ምክንያት ካላቀረቡ በቀጣይ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቀዋል።
በድንጋይ ከሰል ማምረት ፍቃድ ከወሰዱ ከ20 በላይ ባለፍቃዶች መካከል፣ እስካሁን ወደ ማምረት የገቡት ስምንት ብቻ መሆናቸው ተጠቁሟል።
በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 150 ኪሎ ግራም ወርቅ ለማምረት ታቅዶ 75.525 ኪሎ ግራም፣ እንዲሁም 100 ሺህ ቶን ድንጋይ ከሰል ለማምረት ታቅዶ 50 ሺህ ቶን ብቻ ማምረት መቻሉ ተነገረ ሲሆን የምርት እጥረቱ ምክንያት ሕገወጥነት እና ወደ ሥራ ያልገቡ አምራቾች መኖራቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል ሲል ካፒታል ዘግቧል ።
@seledadotio