⚡️በግብፅ ቀይ ባህር ዳርቻ የቱሪስት ሰርጓጅ መርከብ አደጋ አጋጥሞት ስድስት ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል
በግብፅ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ በባህር ሰርጓጅ የቱሪስት መርከብ ላይ ያሉ ቱሪስቶች በሙሉ ሩሲያውያን መሆናቸውን ተናግሯል።
ስለ አደጋው ተጨማሪ ዝርዝር መረጃን ለማግኘት አሁንም እየጠበኩ ነው የሚለው በግብፅ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ በመርከቡ ውስጥ የነበሩት ቱሪስቶች በሙሉ ሩሲያውያን መሆናቸውን ገልጻል፡፡
ኤምባሲው በፌስቡክ ገፁ ላይ በለጠፈው ጽሁፍ ህጻናትን ጨምሮ 45 ተሳፋሪዎች በመርከቧ ውስጥ እንደነበሩ ተናግሯል።
መግለጫው አክሎ አራት ሰዎች መሞታቸውን እና ሌሎች በርካታ ተሳፋሪዎችን በተመለከተ መረጃ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።
ቢቢሲ ከአከባቢው ሰዎች አገኘሁት ባለው መረጃ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን አስነብቧል ።
በሁርጋዳ የሚገኘው የአከባቢው ገዥ ፅህፈት ቤት ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደገለጸው በቀይ ባህር ሰርጓጅ መርከብ ላይ ዜግነታቸው ያልታወቁ ስድስት የውጭ ዜጎች መሞታቸውን ገልጻል፡፡
@seledadotio