Forward from: Bahiru Teka
👉 ለሽርክና ቢዳዓ እውቅና ለተውሒድና ሱና ንፍግና
የመጅሊሱን ስልጣን እንያዝ ብቻ ከዛ በኋላ ሽርክና ቢዳዓን እናጠፋለን ተውሒድና ሱናን የበላይ እናደርጋለን የሚል ዲስኩር እየለፈፉ ወጣቱን ሲያደነቁሩ የነበሩ ኢኽዋኖች የመጅሊስ ወንበር ላይ ሲወጡ ተገለበጡ ። የቀድመዎቹ ኢኽዋኖችና አዲሶቹ ( ነሲሓዎች ) በአሁኑ ጊዜ ትልቁ ስራቸው የተውሒድና ሱናን ዳዕዋ ማጨናገፍ አድርገዋል ።
ለሽርክና ቢዳዓ እውቅና የሚሰጡት የመጅሊስ አመራሮች ለተውሒድና ሱና እንዴት ተደርጎ እያሉ ነው ። ወንድና ሴት ተደባልቆ የሽርክ አይነትና ቢዳዓ እንዲሁም የተለያዩ ወንጀሎች የሚሰሩበትን መውሊድ የፈለገ ያክብር ይላሉ ። ይህ የመጅሊሱ መርህ ነው ብለው እያወጁ ሰዎች ከተለያየ ክ/ሀገር ወደ ሚፈልገው ቀብር አምልኮ እየሄደ ሞቶ አፈር የሆነን የሙታን መንፈስ እያመለከ አፈር በጥብጦ የሚጠጣበትን ፣ በቀብሩ ዙሪያ ጠዋፍ የሚያደርግበትን ፣ ጭንቁን ለበሰበሰው ሰጋና አጥንት የሚነግርበትን ፣ ሴቷ ዘር ፍለጋ ብላ ሄዳ እርሶ ጋር መጥቼ ምን አጣሁ ብላ የምታለቅስበትን ፣ አብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ ጭንቁን ፣ መከራውን ፣ ማጣቱን ፣ መራብ መጠማቱን ተንበርክኮ እየተንሰቀሰቀ ለሙታኖች የሚነግርበትን የኩፍርና ሽርክ ተግባርን እያበረታቱ ተውሒድና ሱናን መዋጋቱ እንደ ድል እየቆጠሩት ነው ።
በተለያዩ ቦታዎች የሚዘጋጁ የተውሒድና ሱናን ዳዕዋ ለማስቆም አብዛኛዎች የመጅሊስ አመራሮች የሌላ እምነት ተከታይ ፖሊሶችን ይልካሉ ። ከሚላኩት ፖሊሶች እንደሰማነው በጣም ነው የሚሰማን ግን ምን እናድርግ ከናንተው የመጅሊስ አመራሮች ለሀላፊዮቻችን መመሪያ ተሰጥቶ ተልከን ነው ይላሉ ። ተመልከቱ ይህ የመጅሊስ አመራሮች ተግባር በሌላ እምነት ተከታይ የፀጥታ ሰዎች ዘንድ እንኳን ትዝብትን አትርፏል ።
ሄዳችሁ እንዲህ የሚባል ቦታ ላይ መስጂድ ውስጥ ተሰባስበው ቁርኣንና ሐዲስን የሚሰሙትን በትኑ አስተባባሪዮችን እሰሩ እያሉ መመሪያ ይሰጣሉ ። አብዛኞቻቸው መጀመሪያውኑ ጥላቻ ስለሚኖርባቸው አጋጣሚውን ቂማቸውን ለመወጣት ይጠቀሙበታል ። ጤነኛ አመለካከት ያላቸውና አካሄዱ ኢህገመንግስታዊ ነው ብለው የሚያምኑት ደግሞ በነገሩ ይበሽቃሉ ። እኛ ምንም ማድረግ አንችልም ታዘን ነው እባካችሁን ተረዱን ይላሉ ። በጣም ጥቂት የሆኑ የተጣለባቸውን የህዝብ አደራና ህገመንግስቱ ለዜጎች የሰጠው የእምነት ነፃነትን እንደመመሪያ አድርገው የሚያዩ ሀላፊዮች ደግሞ የመጅሊስ አመራሮችን ትእዛዝ ከልኩ ያለፈና ገደቡን የጣሰ በማለት ውድቅ አድርገው ሙስሊሙ ማህበረሰብ እምነቱ የሚያስተምረውን በነፃነት እንዲከታተል ያደርጋሉ ። ለዚህ አይነቱ አስገራሚ አቋም እንደምሳሌ የአሊቾ ወረዳና የሌራ ወረዳ የፀጥታ ሀላፊዮች እንደምሳሌ ይጠቀሳሉ ።
ከላይ ሆነው በድል አድራጊነት የልብሳቸውን ቁልፍ እየከፈቱ የሚንጠራሩት የኢኽዋንና ነሲሓ ጥምር የመጅሊስ አመራሮች ግን ነገ አላህ ፊት ራቁት ቆሞ መመርመር እንዳለ የሰሙ አይመስሉም ። በአላህ ቤቶች ላይ የአላህ ስም ከፍ ተደርጎ እንዳይወሳ ከመከልከል የበለጠ ምን በደል አለ ።
« وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن مَّنَعَ مَسَاجِدَ اللَّهِ أَن يُذْكَرَ فِيهَا اسْمُهُ وَسَعَىٰ فِي خَرَابِهَا ۚ أُولَٰئِكَ مَا كَانَ لَهُمْ أَن يَدْخُلُوهَا إِلَّا خَائِفِينَ ۚ لَهُمْ فِي الدُّنْيَا خِزْيٌ وَلَهُمْ فِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ »
البقرة ( 114)
" የአላህንም መስጊዶች በውስጣቸው ስሙ እንዳይወሳ ከከለከለና እርሷንም በማበላሸት ከሮጠ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ ፈሪዎች ኾነው እንጂ ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አላቸው ፡፡ ለነርሱም በመጨረሻይቱ አገር ታላቅ ቅጣት አላቸው " ፡፡
እነዚህ ተውሒድና ሱናን የሚዋጉት የመጅሊስ አመራሮች በየክ/ሀገሩ ያሉ ሰዎችን አላህን ከማምለክ አውጥተው ራሳቸውን ወደ ማምለክ የሚጠሩትን ህገመንግስቱ የሰውን ገንዘብ ያለአግባብ መብላትና በሰዎች ላይ ፍርሃትና ሽብር መንዛት ስለሆነ ወንጀል ነው ብሎ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ያስቀመጠለትን የጠንቋዮች ተግባርን ጭምር እውቅና የሚሰጡና ማንም ተሰብስቦ የፈለገውን ቢያደርግ የማይከለክሉ ናቸው ። ‼
በጣም የሚያሳፍረውና መልስ ያልተገኘለት ሀገሪቷ የምትመራው በመጅሊሶች መተደዳደሪያ ደንብ ነው ወይስ በህገ መንግስቱ የሚለው ነው ። በኢሀዲግ ዘመን የመጅሊስ አመራሮች እኛ ኢሀዲግ ነው ያስቀመጠን እሱ ያዘዘንን ነው የምናስፈፅመው ይሉ ነበር ። አሁን ደግሞ አብዛኛዎች በትላልቅ የስልጣን ደረጃ ላይ ያሉ የመንግስት አመራሮች ህገመንግስቱ ለዜጎች ያረጋገጠውን የዜግነት መብት ሲጠየቁ መጅሊሱ እንዳትፈቅዱ ብሎናል አንሰማም ይላሉ ። !!! አንሰማም ማለት ብቻ አይደለም ፍትህ በጎደለው የመጅሊስ አመራሮች በሚያስተላልፉላቸው ትእዛዝ ዜጎችን ያንገላታሉ ያስፈራራሉ ያስራሉ ። የዚህ አይነቱ እየተስፋፋ የመጣው የመብት ጥሰት ሀገሪቷ ወጥ የሆነ መንግስታዊ መመሪያ የሌላት እያስመሰላትና ሁሉም ለየክልሉ ለየዞኑና ወረዳው ያሻውን መመሪያ በማውጣት የበላይ የሌለበት መንግስት የሆነ እያስመሰለው ነው ።
አሁንም ለማስታወስ የምፈልገው የዶ/ር አብይ አስገራሚና ነገር ግን እየተናፈቀ የቀረ ንግግርን ነው ። ዶ/ር አብይ ከወልቂጤ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ባደረጉበት ጊዜ አንድ አባት የኔ ስጋት እርሶ እላይ ኖት ታች የሚሰራውን እንዴት ያውቃሉ የሚለው ነው ሲሏቸው
" የመጣሁት ከታች ስለሆነ የማላውቀው ነገር አይኖርም ስጋት አይግባዎት " የሚል ነበር ። ታዲያ ዛሬ ዶ/ር አብይ እየመሩት ያለው የብልፅግና አመራር ከላይ እስከታች ምን እየሰራ እንዳለ ያውቁ ይሆን የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው ።
ከመጅሊስ አመራሮች ጋር መሰረታዊ ልዩነት አለን እያልን ሰሚ ልናጣ አይገባም ። የመጅሊስ አመራሮች የሙስሊሞች የሆነውን ተቋም በቁርኣንና ሐዲስ በሰለፎች ግንዛቤ ከመሩት አንድ እንሆናለን ካልሆ ግን ልዩነታችን አንተም ተው አንተም ተው የሚባልበት አይደለም መሰረታዊ ነው ። የኛ ጥያቄ መጅሊሱን እኛ እንምራው አይደለም ። እናንተም በመንገዳችሁ እኛም በመንገዳችን በመብታችን አትግቡ ነው ። እንደሀገር በህገ መንግስቱ እንደሙስሊም በቁርኣንና ሐዲስ በቀደምት ደጋጎች ግንዛቤ ነው የምንመራው ። ይህን መብታችንን የሚረግጥ የትኛውንም አካል አንቀበልም ።
ስለዚህ ዜጎችን በእኩልነት ልታገለግሉ በየደረጃው የተቀመጣችሁ የመንግስት ተቋም ሀላፊዮች የተጣለባችሁን አደራ ተወጡ ስልጣንን ለግልና ለቡድን አመለካከት ማስፈፀሚያ አታድርጉ እንላለን ።
https://telegram.me/bahruteka