#ሰማይን የለጎመውና እሳት ያዘነመው ቅዱስ
ንጉሱ አክአብና ሚስቱ ንግስቲቱ ኤልዛቤል አብያተ ክርስቲያናትን ዘግተው አብያተ ጣኦታትን በመክፈት ነቢያትና ካሕናትን ያስገድሉ ጀመር፡፡ በዘመናቸው የነበረው ነቢዩ ቅዱስ ኤሊያስ “ተው” ቢላቸው አልሰማ አሉት፡፡ በዚህ ጊዜ "ሕያው እግዚአብሔር አምላከ ኃይል: ዘቆምኩ ቅድሜሁ: ከመ ኢይረድ ጠል በእላ መዋዕል ዘእንበለ በቃለ አፉየ" “በፊትህ የቆምኩ ሕያው እግዚአብሔር አምላክ ሆይ እኔ ካልተናገርኩ በስተቀር በዚህች ምድር ዝናም አይዝነም” ብሎ 3 ዓመት ከ6 ወር ዝናም ከሰማይ እንዳይወርድ ዘግቷል፡፡ ቤል የተሰኘውን ጣኦት አምላካቸውን እሙን ይዩት ብሎ፣ አንድም እግዚአብሔር የሰጣቸውን እየበሉ እንዴት ጣኦት ያመልካሉ የሚል የሃይማኖት ቅንአት ይዞት ነው፡፡
በተለይ የደሀውን ናቡቴ ርስት በመውሰዷ የገሰጻት ንግስቲቱ ኤልዛቤል ናቡቴን ስታስገድለው "የናቡቴ ደም በእናንተ ላይ አይቀርም፡፡ የአንቺንም ደም ውሻ ይልሰዋል" ብሏት ነበርና በእልህና በጥላቻ 900 ነቢያትና ካሕናት አስፈጅታለች፡፡ አንድ መቶ የሚሆኑትን ግን የአካአብ የጦር ቢትወደድ አቢድዩ በአንድ ዋሻ ደብቆ አድኗቸዋል፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ900 ዓ.ዓ የተወለደው ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤልያስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ርዕሰ ነቢያትም ተብሎ ይጠራል፡፡ ሲወለድ አራት ብርሃን የለበሱ ሰዎች መጥተው ወደ ቤታቸው መጥተው በእሳት መጎናጸፊያ ሲጠቀልሉት ቤቱ ብርሃን ተሞልቶ ነበር፡፡ ወላጆቹ ይህን ነገር በጊዜው ለነበሩ ነቢያትና ካሕናት ነግረዋቸዋል፡፡
በመጨረሻም ነቢዩ ቅዱስ ኤልያስ አክአብንና ቢትወደዱን አብድዩን አገኛቸው፡፡ “እስከመቼ በሁለት ልባችሁ ታነክሳላችሁ እግዚአብሔር አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ እርሱንም ተከተሉ፣ ቤል አምላክ ከሆነ ደግሞ እርሱን አምልኩ እርሱንም ተከተሉ፤ ይህ እንዲሆንም መስዋዕት ሰውተን መስዋዕት ከሰማይ ወርዶ የበላለት አምላክ ነው” አላቸው፡፡ በዚህ ተስማምተውም በመጀመሪያ የጣኦቱ ካሕናት መስዋዕት ቢሰዉ ከሰማይ እሳት ወርዶ የማይበላላቸው ሆነ፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ኤልያስም ያሾፍባቸው ጀመር፡፡ አምላካችሁ እንቅልፋም ነውና ተኝቶ ይሆናል ጮኻችሁ ጥሩት፣ አምላካችሁ እንጂ ዋዘኛ ነውና ከእረኞች ጋር ይጫወት ይሆናል” እያለ፡፡
በኋላም የሰር መስዋዕት ጊዜ ደረሰ ይበቃችኋል አላቸው፡፡ እርሱም መስዋዕቱን አዘጋጅቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ “አምላከ እስራኤል እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔ እከብርበት፣ እበላበት፣ እጠጣበት ብዬ አይደለም ለአምልኮትህ ቀንቼ እንጂ ይህነ መስዋዕት ተቀበል” ብሎ ቢያመለክት ከሰማይ እሳት ወርዶ ከመስዋዕቱና ከተረበረበው እንጨት እልፎ መሬቱን እስኪልሰው ድረስ በልቶለታል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህን ታላቅ ነቢይ እግዚአብሔር ስለሰጠው ሦስት ጸጋዎች ታከብረዋለች፡፡ ስለድንግልናው፣ ስለምንኩስናው (እጅግ ጥቂት ለቁመተ ስጋ ያህል ብቻ ይመገብ ነበርና)፣ ስለ ብሕትውናው (ከሰዎች ርቆ ይኖር ነበርና፡፡
ከሰማይ እሳት ያወረደ፣ ዝናም እንዳይወርድ ሰማይን የለጎመ ድንቅ ባህታዊ ነው፡፡ በመጽሐፈ 1ኛ ነገስት 17፣2 የሰፈረው ታሪኩ እንደሚሳየውም ወደብሔረ ሕያዋን በእሳት ሰረገላና በእት ፈረስ አርጓል፡፡ በመጨረሻም በዘመነ ሐሳዌ መሲህ መጥቶ በሰማዕትነት ያርፋል፡፡ መታሰቢያው ታሕሳስ 1 ነው፡፡ የዘመናችን ባሕታውያንም ስጋዊውን ዓለም ትተዋልና መንፈሳዊ በረከት የታደሉ ናቸው፡፡ ገዳማቸውን በማገዝ በዓታቸውን በማጽናት ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለተጨማሪ መረጃ:-
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957
ወይም 0938644444