✝️ ተዝካረ አበው እንዳይዘነጋ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የካቲት 25 የዕረፍታቸው መታሰቢያ።
"ጸሎትክሙ ጽንዕት ሃይማኖትክሙ ርትዕት።"
✝️ ኢትጵያውያኑ የአባ አጋቶን ልጆች
"አንደበቱን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል።"
ምሳሌ 13፤3።
✝️ እግዚአብሔር ለምድራችን በዘመናችን የሰጠን ጸጋችን ክብራችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ የክብሩን ጸዳል ያበራባቸው እረኞቻችን።
✝️ ቅዱስ አባታችን አቡነ መርቆሬዎስ ሁሉን በልባቸው ይዘው አንተ ክፉ አንተ ደግ ሳይሉ እግዚአብሔር አንደበት የሆናቸው በግፍ ተሰደው በክብር የተመለሱ ለ30ዓመታት ከቃለ እግዚአብሔር ውጪ አንደበታቸው ለምንም ያልተከፈተ የጽናት የትዕግስት መድብል። እንዲሁም ዝምተኛው ተናጋሪ ፊታቸው እንደ ፀሐይ የሚያበራው ክቡር አባቴ አርምሞ ዘዋልድባ በገዳመ ዋሊ ለ40 ዓመታት በአርምሞ የኖሩ የበረከት የጸሎት አባት። ባንጠቀምባቸውም እግዚአብሔር እድፍ ጉድፋችንን ሳይቆጥር በዜና አበው የምንሰማውን የአባ አጋቶንን ገድል በዘመናችን ስላሳየን ክብር ይግባው።
✝️ ዛሬም በኢትዮጵያ ገዳማት የምናውቃቸውም እግዚአብሔር የሚያውቃቸውም ቃለ እግዚአብሔር ብቻ ሰርከ ሕብስታቸው የሆነ አበው አሉን። እኛስ ዛሬ በአንደበታችን ምን እየተናገርን በብዕራችን ምን እየዘራን ነው ???? ራሳችንን እንመርምር አምላከ አበው ኢትዮጵያን ከጥፋት እኛን ከስደት ይሰውረን የነደደውን የዘረኝነት የጥላቻ እሳት በአበው እንባ ጸሎት ይጥፋ የአባቶቻችን በረከት ይደርብን ከውሉደ መርገም መዳፍ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ይሰውረን አሜን አሜን አሜን።
@sigewe
https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL