Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🇰🇪 ኬንያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈውን የምስራቅ አፍሪካ የሰላም ግንባታ መርሃ ግብርን ልትመራ ነው
"ሽብርተኝነት ለኬንያ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው ከባድ ስጋት አስከትሏል። ይህ መርሃ ግብር ደህንነቱ የተጠበቀ እና ይበልጥ አስተማማኝ መጻዒን ለመፍጠር የሚያስችል እርምጃ ነው" ሲሉ የኬንያ የውስጥ ደህንነት ዋና ፀሐፊ ራይሞንድ ኦሞሎ ተናግረዋል። "ለወጣቶች አማራጭ መተዳደሪያ ማመቻቸት በጽንፈኛ ቡድኖች የመመልመል እድላቸውን ይቀንስላቸዋል" ብለዋል።
የኬንያ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገበው፣ ይህ ፕሮግራም በኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ሲሆን ለትግበራውም 2.3 ቢሊዮን ሺሊንግ (ከ17 ሚሊዮን ዶላር በላይ) ወጪ ያስፈልጋል።
ኦሞሎ አክለውም ፕሮግራሙ በሶማሊያ እና በደቡብ ሱዳን ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል። በሲቪሎች እና በፀጥታ አካላት መካከል ግንኙነትን ለማጠናከር ከ500 በላይ የማህበረሰብ ሰላም ግንባታ ኮሚቴዎች እንደሚቋቋሙ ተናግረዋል።
ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ
👉 ለአንድሮይ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዩጵያን ይወዳጁ 👉 @sputnik_ethiopia