ማስታወሻ
ሸዕባን ከመውጣቱ በፊት
:
የቀደመ የረመዳን ቀዷ ያለበት መጪው #ረመዳን ሳይገባበት ቀዷውን አውጥቶ ይጨርስ። ቀዷ ማውጣት እየቻለ ሳያወጣው ተከታዩ ረመዳን የገባበት ሰው: ‐
⚀ ኃጢኣተኛ ይሆናል፤
⚁ ቀዷእ ማውጣቱ አይቀርለትም፤
⚂ ፊድያ (ቤዛ) ማውጣት ግዴታ ይሆንበታል። ፊድያው ለአንድ ቀን አንድ እፍኝ ነው። አመቱ በጨመረ ቁጥርም ፊድያው ለአንድ አመት አንድ እፍኝ እየጨመረ ይመጣል።
:
በህመም፣ በማጥባት፣ በእርግዝና ወይም በሌላ ሸሪዓዊ ምክንያት ቀዷውን መክፈል ያልቻለ ሰው ግን በተመቸው ጊዜ ብቻ ቀዷ ማውጣት ይበቃዋል።
ይህ የሻፊዒዮች እና የአብዝሃኛዎቹ ልሂቃን ሃሳብ ነው!
ረመዷን ሊገባ ነውና እንተዋወስ!
መልካም አዲስ የሥራ ሳምንት ይሁንልን!
✏️ኡስታዝ_ቶፊቅ_ባሕሩ (ሐፊዘሁላህ)