በአሊ መስጂድ ጀመአ ላይ የደረሱ በደሎችና ግፎች ተቆጥረው የሚዘለቁ አይደሉም፣የዛሬ አመት ረመዳን ሲደርስ ወንድማችን ሰኢድን ከፎቅ ላይ ከነሂወቱ ያለ ስስት ሶስት ቦታ ወግተው የወሀብያ ወጣቶች ወርውረውታል። ከዚህ ባለፈ ከ90 ሰዎች በላይ ምንም ባልሰሩትበት ሁኔታ ከክፍለ ከተማ መጅሊስ ጋር በመሆን አሳስረዋል፣ከግማሽ ሚልየን ብር ባላነሰ የገንዘብ ዋስ ፍርድ ቤት አሰናብቷቸዋል ።ይህ በሙሉ ግፍ እየተፈፀም እያየ ዝም ከማለት አልፎ ለአጥፊዎች ተከላካይ የሆነው የክ/ከ መጅሊስ አቶ ባህረዲን ነው፣ይህን የተገነዘበው የፌዴራል መጅሊስ ነገሩን ለማረጋጋት ከሁለቱ ወገን አጣሪ እንዲሁም የሀገር ሽማግሌ አድርጎ የመወሰን ስልጣን ለእነዚሁ አጣሪ ኮሚቴ በመስጠት ነገሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሁሉን ባማከለ መልኩ በሰለም እንዲያልቅ ሸማግሌውች ድብዳቤ አሲዞ አሰማራ።አጠሪውም ኮሚቴ ከወሀብያ በኩል ኡስታዝ አቡ በክር አህመድ ከደአዋ ጀማአ ኡስታዝ አቡ በክር አብደሏህ የሀገር ሽማግሌ ኡስታዝ መሀመድ አጎናፈር ናቸው። የፌድራል መጅሊስ በሰጣቸው ስልጣን መሰረት ስራቸውን ሰፈር ድረስ በመውረድ እያንዳንዱንድ በመጎብኘትና በማናገር የመጨረሻ ውሳኔ በደብዳቤ ለመጅሊስ እንዲያስፈፅም አስረከቡ። ታዲያ ይህ ስምምነት የጎረበጣቸው የሰላም ጠላቶች በእረብሻ የግል ኪሳቸውን ለማደለብ እንደ ትልቅ አጋጣሚ የሚጠቀሙ ጥቂት ነውጠኞች ሽምግልናው ከመፈፀሙ በፊት ክ/ከ መጅሊስ ከሆኑት አቶ ባህረዲን ጋር ድብቅ ስብሰባ በማድረግ የአካበቢውን የመብራት ለቀናት መቋረጠ እድል በመጠቀም ተአሊምና መሹራ በተቀመጡ የደአዋ ሰውች ላይ ጥቃት ፍፀመዋል ይህ ብቻ አደለም የቻሉትን ፈንክተው የቻሉት አሳስረው እራሳቸው በለኮሱት መስጂዱና እንዲዘጋ አድርገዋል ።በአሁን ሰአት መስጂዱ የተከፈተ ቢሆንም ከአምስት መቶ በላይ ተማሪውች ያሉትን መድረሳ አዘግተዋል ።!