«ሱና የኑሕ መርከብ ናት »


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


✍🏽‏ قال العلامة ربيع المدخلي -حفظه الله- :

*《 ما ضاع شباب الأمة وما ضاع الناس ،*
*إلا بالسكوت على الباطل 》.‏*
📓 |[ المَـصـدَرُ : المجموع (436/15) ]|

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter










ሁላችንንም የሚመለከት መልዕክት
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
➞➞➞➞➞➞
የተከበራችሁ  #ወንድሞቼ እና #እህቶቼ ቀን አልፎ ቀንን እየተካ  ይሄው  ትልቁ እንግዳችን  #ረመዷን  እየደረሰ ነው።
በመሆኑም  ይህን  ውድ እንግዳችንን  ተዘጋጅተን  መጠበቅ  አለብን።


#በተለይ_ደግሞ
ቀዷ ያለባችሁ ማለትም፦
                            ➲ #በህመም
                            ➩   በሀይድ
                            ➲ #በወሊድ
                            ➩   በጉዞ
                                ወይም
በሌላ ምክንያት  የባለፈውን #ረመዷን  በሙሉ ወይም በከፊል  ያልፆምን  እንድሁም  ቀዷውንም  እስካሁን  ያላወጣን  ካለን ይሄኛው #ረመዷን  ከመግባቱ በፊት  ማውጣት  አለብን።
ዝም ብለን ቆይተን ወሩ ከደረሰ በኋላ  ለፈታዋ #ከመሯሯጥ አሁኑ ቀዷ ያለብን  ቀዷችንን መፆም ተገቢ ነው።

በሌላ ከኩል በቀሩት ቀናት ውስጥ ደግሞ #ስለረመዷን ትምህርቶችን መማር አለብን።
#ይህ_ማለት
      ✅ ስለረመዷን ሁክም
      ✅ #ረመዷንን_መፆም ያለውን ደረጃ
      ✅ ረመዷንን ስለሚያበላሹት ነገሮች
      ✅ #ለፆመ_ሰው_ስለሚከለከሉ ነገሮች
      ✅  ለፆመ ሰውስለሚፈቀዱ ነገሮች
      ✅ #በረመዷን_ዙሪያ_ስለተሰጡ ፈታዋዎች
➷➴➘   
ወዘተ…ከተለያዩ #የመረጃ_ምንጮች  መማርና ማወቅ  ይጠቅመናል። 

ከመረጃ ምንጮች መካከል፦
                    ➜ የኡለሞች #ኪታቦች
                    ➜ የታማኝ
#ኡስታዞች
የቴሌግራምና የዋትሳፕ #ቻናሎች
#ስለረመዷን   የተለቀቁ   የታማኝ         
                           
#ኡስታዞች_ኦዲዮ
እንዴ ኡምደቱል እህካም መንሃጁ ሳሊኪን እና መሰል የፊቅህ ኪታቦች ላይ ኪታቡ ሲያም የሚለውን በአካባቢው በሚገኙ ኡስታዞች መሻይኾች ላይ ብትቀሩ (በትማሩ) መልካም ነው።

እና ሌሎችም።  እነዚህን #ተጠቅመን  ስለዚህ  ውድ  እንግዳችን  #ረመዷን  ተገቢውን  መረጃ  እና  #እውቀት  መሰብሰብ  አለብን።

ላልደረሳቸው Share በማድረግ  የአጅሩ  ተካፋይ  ይሁኑ!!!

▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴
⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

---------------⫷⫸-----------------
🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
⫷⫸⫷~⫸⫷⫸⫷~⫸⫷⫸⫷~⫸


«عظم شأن كلمة التوحيد: "لا إله إلا الله"، وبيان فضلها»

فَضِيلَة الشَّيْخِ عَبْد اللّه القُصَيِّـر
-حَفِظَهُ اللهُ-
join #telegram ቻናል
https://t.me/abuabdurahmen




🚫 ማቆሚያ የሌለው የነሲሓ ሙሪዶች መከራ

    የነሲሓ ከዐቅላቸው የተለያዩ ሙሪዶች ለሸይኻቸው ኢልያስ የሚደረድሩዋቸው ዑዝሮች መና የሚያስቀረው የኢልያስ ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቅስማቸው ተሰብሮ አንገታቸውን እንዲሰብሩ ማድረጉን ቀጥሏል ። ነገር ግን ኢልያስ የገባበት እንገባለን የሚያቆመን የለም የሚሉት በውዴታው የታወሩና የሰከሩ ጭፍኖቹ ተከታዮች ስህተቱን የሚያዩበት አይናቸው እንዲታወር ዱዓእ አድርገው ተቀባይነት ያገኘ ይመስላል ።
      የኢልያስ አሕመድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የማንነቱ ማሳያ ዛሬ ላይ ከሙሐመድ ዘይን ዘህረዲንና ከሀይደር  ከድር ጋር የኢኽዋን ሱፍይና አሕባሽ ጥምር መጅሊስ በ27/4/2017 ቦሌ ወሎ ሰፈር አቡ ሁረይራ መስጂድ ባዘጋጀው የዳዕዋ ፕሮግራም ላይ ፖስተሩ ተለጥፎ እኔ ማለት ይሄ ነኝ እዩኝ እያለ ነው ።
    ተቀጥፎት ነው እንዳትሉ ከተማው ላይ ዞር ዞር በሉ ለሱ ኩራት የመሰለው አሳፋሪው ከኢኽዋን አቀንቃኞች ጋር የተነሳው ፎቶ ፖስተር በሚቀጥለው ሊንክ ገብታችሁ እዩት : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/1qEAPEj2G4zg_4Qcomh8lShRul4N6XhK2/view?usp=drivesdk
       ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን ማለት ማን ምን አይነት ሰው እንደሆነ በሚከተለው ሊንክ ገብታችሁ ተመልከቱ : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/1rRiinpobQ_AUp_CcJXCkzwZYiPvc-YB7/view?usp=drivesdk

     መከረኛ ሙሪዶች ሆይ ይህ ነው ሸይኻችሁ ። ሱብሓነላህ !!! አሁንም ሲያነሱኝ ከአሮጊት ጋር አሁንም ሲያነሱኝ ከአሮጊት ጋር አለ ፎቶ ሲነሳ እድሉ ከአሮጊት ጋር የሆነው ሽማግሌ ። ምነው ሸይኻችሁ ከእነዚህ በኢኽዋንያ ፊክራ የጨረጨሱ አካላት ጋር አደረገው ጓደኝነቱ ? የናንተን ሙሪዶቹን መከራ ለማብዛትና ለኢኽዋኖች ታማኝነቱን ለማሳየት ነው ? ወይስ የናንተን መኖር ከነአካቴው ረስቶት ነው ? እናንተ ዐቅለቢስ መከረኛ ሙሪዶች አሁንስ ሸይኻችሁ ሰለፍይ ነው ? ወይስ ሰለፍይ ማለት ቢዳዓ ነው የደረሳችሁበት የመሟሟት ዝቅጠት ? ነው ወይስ  ሁወ ሰማኩሙል ሙስሊሚን የሚለውን አንቀፅ ያለ አግባብ ተረድተው የሚያቅራሩት  ቀረርቶ አደንቁሮዋችሁ ነው ? አው ካላችሁ የናንተና ቀብር ላይ ተደፍቶ እያለቀሰ እዱኝ ፣ አሽሩኝ ፣ አክብሩኝ ፣ ለምን ተውኝ እያለ የሙታን መንፈስን ከሚያመልከው ጋር አንድ ነው ? ካልሆነ ቀብር አምላኪዮችን ታከፍራላችሁ ማለት ነው ። ጣፋጩ መራራ ነው ከሁለት አንዱን ምረጡ ። እናንተና አቡ በከርን ፣ ዑመርን ፣ ዑስማንን ፣ ዓኢሻንና ሐፍሳን የሚያከፍሩ ሺዓዎች እስልምና አንድ ነው ? አሁንም አንዱን ምረጡ ።
     ዲሞክራሱ ከተከበረ ዲኔ ተከበረልኝ ማለት ነው ። ዒሳም ፍቅርን ያስተማረ ጌታ ነው, ሁሉም ሰማያዊ እምነቶች ፍቅርን ነው ያስተማሩት, ኢትዮዽያ የሸሪዓ ሀገር መሆን አለባት ብሎ ማሰብ በራሱ ወንጀል ነው ብለን ነው የምናምነው,  የፈለገ መውሊድ ያክብር የፈለገ ጫት ይቃም አንተ ምን አገባህ, የሚሉ ኢኽዋኖችና የናንተ እስልምና አንድ ነው ? ሸይኻችሁ አንድ ነን ብሎ አደባባይ ላይ አንድነቱን እያሳየ ነው ። እንደነዚህ አይነት ጥያቄዎች ሰምታችሁ መልሱን እንዳታስቡ ቃል ኪዳን ገብታችሁ ለሸይኻችሁ ቆርባችኋል? 
     አይ የነሲሓ ሙሪዶች ስታሳዝኑ ምነው መከራችሁ በዛ እስኪ የእንቅልፍ ክኒኑ ሀይል አልቆ ከሆነ ወደ አንደኛው ጎናችሁ ለመገልበጥ ሞክራችሁ እዩት !!! ነው ወይስ በድብቅ ካሜራ እይታ ውስጥ ናችሁ የሚል ፁሑፍ አለ ? ለማንኛውም አላህ ይድረስላችሁ ወደ ቅኑ መንገድ ይምራችሁ እንላለን ።
  
https://t.me/bahruteka


Forward from: Bahiru Teka
✅ ሰለፍዮች በትግላችሁ ቀጥሉ

የአላህ መሺኣ ነውና የሐቅና ባጢል ግብግብ እስከ ቂያማ ይቀጥላል ። በዚህም እውነተኛች በጫፍ ላይ ካሉት ይለያሉ ። ነገሮች ሲመቻቹ ሁሉም አማኝ ነው ሁሉም ሱና ወዳጅ ነው ነገር ግን በፈተና ጊዜ ነው እንክርዳዱ ከፍሬው የሚለየው ። የተወሰኑ የአላህ ባሮች እሳት ውስጥ ገብቶ እንደ ወጣ ወርቅ የዲኑ ጌጥ ሲሆኑ አብዛኞች ጎርፍ ያመጣው አረፋ ሆነው ዳር ይቀራሉ ።
የአላህ መልእክተኛ ፈተናን አስመልክተው ሲናገሩ ከኋላ የሚመጣው የፊተኛውን ቀላል ያደርገዋል ብለውናል ። አሁን እያየን ያለነው ይሄው ነው ። ድሮ የኢኽዋን አንጃ በነ ሓሚድ ሙሳ አማካይነት ወደ ሀገራችን ሳይገባ በፊት ሁሉም ወደ ተውሒድና ሱና ሲጣራ ሱፍዮች ካጠቃላይ የተውሒድ ሰዎች ጋር ነበር ትግላቸው ።
የሱናው ወጣት በኢኽዋን አስተሳሰብ መጠለፍ ሲጀምር ሰለፍይና ኢኽዋንይ ተብሎ ተከፈለ ። ሰለፍዮች ከሱፍይና ኢኽዋን ጋር ትግል ጀመሩ ። ብዙም ሳይቆይ ኢኽዋኖች ከሱፍዮች ጋር ተደመሩ በጋራ ሰለፍያን ለመጣል መስራት ጀመሩ ። ሰለፍዮች በጋራ የተከፈተባቸውን ትግል ተቋቁመው ወጣቱን ለማዳን የሞት ሽረት ትግል አደረጉ ። ተሳክቶላቸው የጥምር ሀይሉን መቋቋም ቻሉ ።
በዚህ ሁኔታ እያሉ የአሕባሽ አስተሳሰብ መጥቶ መጅሊሱን ተቆጣጥሮ የአወሊያ ተማሪዮችን ሲያባርር ኢኽዋኖች አጋጣሚውን ተጠቅመው መድረኩን ይዘው ከጫፍ እስከ ጫፍ ፀረ አሕባሽ ንቅናቄ አካሄዱ ።
ከአሽባሽ ጋር የነበረው ፀብ የስልጣን እንጂ የዐቂዳ አልነበረም ። ለዚህ ማስረጃው ኢኽዋን ያደርገው በነበረው ሀገራዊ ሰልፍ መፈክሩ " አሽ ሻዕብ ዩሪድ ኢስቃጠል መጅሊስ " ( ህዝቡ መጅሊስን መጣል ይፈልጋል ) የሚል የነበረ መሆኑ ነው ። በዚህ ንቅናቄ ኢኽዋን ካገኘው ያልጠበቀው ትርፍ አብዛኛው ሱና ሲደግፍ የነበረው ወጣትና ባለሀብት ወደ ትግሉ መቀላቀሉና የሰለፍያን ዳዕዋ ሲመራ የነበረውን ናጂያን መኮነኑ ነበር ። ጊዜው አብዛኛዎች የናጂያ ዱዓቶች አገር ጥለው የተሰደዱበት ወቅት ነበርና ይህ ሁኔታ ዋና ዋና የናጂያ መሪዮች አቋማቸውን እነዲቀይሩ አደረጋቸው ።
የሰለፍያው ዳዕዋ በተለያዩ መሻኢኾችና ዱዓቶች አማካይነት ትግል እያደረገ የነበር ሲሆን በሚዲያው ላይ በነኢብሙነወርና ሳዳት አማካይነት ዳዕዋው መነቃቃት ጀመሮ ከፍተኛ ትግል ይደረግ ነበር ።
በዚህ ጊዜ ትግሉ በዋነኝነት ወደ ኢብኑ መስዑድ ከተዘዋወረው ናጂያ አመራሮች ጋር ነበር ። በዚህም የሰለፍያው ዳዕዋ ትግል ከኢኽዋኖችና ኢብኑ መስዑዶች ጋር ሆነ ። ትግሉ ቀጥሎ የሰለፍያው ዳዕዋ ወጣቱን መልሶ መቆጣጠርና ከተቃራኒዮቹ መዳፍ አብዛኛውን ማውጣት ቻለ ።
ይህ በንዲህ እያለ ስርአቱ ከኢሀዲግ ወደ ብልፅግና ሲሸጋገር የመደመር ስሌት አሕባሽን ፣ ሱፍይን ፣ ኢኽዋንና ወደ ነሲሓ የተዛወረው ኢብኑ መስዑድ ተቋም አመራሮች አንድ ሆነው ወደ መጅሊስ መጡ ። ይህን የድምር ውጤት ያዩት እነኢብኑ ሙነወር መደመሩ ነው የሚያዋጣው ብለው የጥምሩ የእንጀራ ልጆች ሆኑ ። ባለውለታ ለመሆንም ሰለፍዮችን ባለ በሌለ ሀይላቸው መዋጋት ጀመሩ ። እነ ኢብኑ ሙነወር በእስክሪብቶ የጥምሩ መጅሊስ አመራሮች በመሳሪያ አፈሙዝ የሰለፍያ ዳዕዋ መዋጋት ጀመሩ ።
የጥምሩ መጅሊስ አመራሮች ሰለፍዮችን ከዳዕዋው ሜዳ ለማስወጣት መስጂዶችን መረከብ የመጀመሪያው ተግባር አድርገው ያዙት ። ይህ አካሄድ የሰለፍዮችንም መስጂዶች ጭምር መረከብን ያካተተ ነው ። ለዚህ ደግሞ በሰለፍዮች መስጂዶች ላይ ሁከትና ረብሻ በመፍጠር ሰለፍዮች የፈጠሩት በማስመሰል ለጅምላ እስር መንገድ ይከፍታል ብለው ነው ። በአሁኑ ሰአት በስራ ላይ ያዋሉት በስልጤ ዞን ላይ ሲሆን እንደሞመከሪያ ነው እየሰሩት ያሉት ። ሰለፍዮች መርሳት የሌለባቸው ኢብኑ ሙነወር ላይደርሱላችሁ መስጂዳችሁን ያሰነጥቁዋችኋል ማለቱን ነው ። ‼ ይህ ማለት እስትራቴጂውን ያውቀው ነበርና ለመጅሊስ እጅ ስጡ ነበር መልእክቱ ።
ማስገንዘቢያ ለሰለፍዮች :–
ሰለፍዮች ይህን እስትራቴጂ ማስቆም የምትችሉት በዳዕዋ ላይ በመፅናት ነው ። የተዘጋጀላችሁን ወጥመድ ተጠንቀቁ በፍፁም ስሜታዊ እንዳትሆኑ ። ከመስጂድ ቢያስወጡዋችሁ ጊቢ ውስጥ ዳዕዋ አድርጉ, ልጆቻችሁን እቤትችሁ አስተምሩ, አንዱ ዳዒ ሲታሰር ሌላው ይቀጥል ፍፁም ዳዕዋ እንዳታቆሙ, እነርሱ ይሰሩ እናንተ ዳዕዋችሁን ቀጥሉ, ሀይለቃልም ከመጠቀም ተቆጠቡ አብዛኛው ማህበረሰብ እናንተ ዲን ለማጥፋት የመጣችሁ ተደርጎ ስለተሳለለት እዘኑለት ። ትግላችሁ አፈር የለበሰውን ሐቅ አፈሩን ጠርጋችሁ ለማሳየት መሆን አለበት ።
ከአላህ ጋር እውነተኛ ሁኑ አላህ እውነተኞች ይረዳልና አብሽሩ ። ፅናት የትግል ድልድይ ናት ። ትግሉን ለመሻገር ፅኑ ። ለዚህ በሶብር ፣ በኢኽላስና ዱዓእ ታገዙ ። የነብዩ ሱና መርከብ ነውና ከሱ እንዳትወርዱ በቢዳዓ ባሕር እንዳትሰጥሙ ተጠንቀቁ ። ሌላው በፍፁም ዳዕዋ ላናደርግ ብላችሁ እንዳትፈርሙ ያለ ፈቃድ ለሚሉዋችሁ የህገመንግስቱ ፈቃድ በቂያችን ነው በመጅሊስ ደብዳቤ ከተሻረና ዳዕዋ ማድረግ ወንጀል ከሆነ ቅጣቱን ለመቀበል ዝግጁ ነን በሉ ። በሱና መርከብ ላይ ለመሳፈር ቆራጥ መሆን ያስፈልጋል ቆራጥ ያልሆናችሁ አላህ ፊት እንዳታፍሩ ፀንታችሁ ታገሉ ።
አላህ ተውሒድና ሱናን የበላይ ለማድረግ ሰበብ ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka


👉 ለሀገር ድህነትና ኋላ ቀርነት ኢስላም ተጠያቂ አይደለም ።

የአንድ ሀገር እድገትና ውድቀት የሚለካው ያ ሀገር በሚከተለው ፖሊሲ ነው ። ፖሊሲው ጤናማና ዜጎችን ስራ ወዳድና ምርታማ የሚያደርግ ከምዝበራና ባቋራጭ የመበልፀግ ፍላጎት የፀዳ ትውል መቅረፅ የቻለ ከሆነ ሀገር ማደግ ይችላል ።
የኢስላምን አስተምሮን ብንመለከት የሰው ልጅ በእጁ ማደር እንዳለበት ፣ በሚሰራ ጊዜ ስራውን ማጥራትና በአግባቡ ሀላፈነቱን መወጣት እንዳለበት አበክሮ ያወሳል ። ጉበኝነትን ፣ አስመሳይነትን ፣ ሌብነትን ፣ አለባብሶ ማለፍን ፣ የዛሬን ስራ ለነገ ማሳደርን ያወግዛል ። ከዚህ በላይ በጣም ትኩረት ሰጥቶ የሚያስተምረው ባለ መብቃቃትንና የሌሎችን አለመመኘትን ነው ።
ግብይትን አስመልክቶ በሰው ልጅ የህይወት ታሪክ አምሳያ የሌላቸው ረቂቅ የሆኑ ህግጋቶችን ያስቀምጣል ። ከእነዚህ ውስጥ እንደማሳያ የሚከተሉትን እንይ : –
– ስፍርና ሚዛንን መጠበቅ
– በእጅ ያልገባን ነገር መሸጥ መከልከል
– አየር ባየር የሚባልን ሽያጭ መከልከል
– ማታለልን መከልከል
– ገበሬ ምርቱን ወደ ገበያ በሚያመጣ ጊዜ
መንገድ ጠብቆ መግዛትን መከልከል
– ማንኛውንም ህዝብ የሚጠቀምበትን እቃ
( መጋዘን ) አከማችቶ ዋጋ ለመጨመር የለም ማለትን መከልከል የሚሉት ይገኙበታል ።
እነዚህ የኢስላም አስተምሮዎች ተግባራዊ የሆኑባት ሳውዲ አረቢያ የደረሰችበት ደረጃ የኢስላም አስተምሮ ለሀገር እድገት ያለው ሚና ትልቅ ማሳያ ነው ።
ሙስሊሞች ትክክለኛ እስልምናቸው እንዳያውቁና ልማዳዊ አምልኮን አጎልብተው ለስሜታቸውና ዝንባሌያቸው ያደሩ ኋላ ቀር እንዲሆኑ በሚደረግባት ዐለም ለሀገር ውድቀት እስልምናን ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አይደለም ።
ወደ ኋላ መለስ ብለን የታሪክ መዛግብትን ብናይ ሙስሊሞች በትክክለኛው የኢስላም አስተምሮ ሀገር በመሩበት ዘመን የት ደርሰው እንደነበር ማወቅ እንችላለን ። ከነብዩ ዘመን አንስቶ የአቡ በከር ፣ የዑመር ፣ የዑስማንና ዐልይ እንዲሁም የመጀመሪያዎቹ የአመዊዮች ስርወ መንግስት ዘመናትን ታሪክ ማወቅ ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው ።
የምእራቡ አለም ከኢስላም ሊቃውንቶች የወሰዷቸው ቀመሮች ለብልፅግናቸው መሰረት መሆኑን የፃፈው ጀርመናዊው ዘይጝሪድ ሆንካ
" ሸምሱል ዐረብ ( ኢስላም) ተስጠዕ ዓላ አልጘርብ " በሚል ወደ ዐረብኛ በተተረጎመው መፅሐፉ ላይ አስገራሚ በሆነ ሁኔታ አስፍሮታል ። ይህ ግለሰብ ምእራባዊያኖች እስልምናን ለመምታት የእስልምናን አስተምሮ እንዲያጠኑ የቤት ስራ ከሰጡዋቸው ግለሰቦች አንዱ ነበር ። የኢስላምን አስተምሮ ሲያጠና ከቆየ በኋላ ምእራቦቹ የሚጠቀሙባቸው ብዙ ቀመሮች የኢስላም ሊቃውንቶች ውጤት መሆናቸውና አብዛኛው የኢስላም አስተምሮ ለእድገታቸው ምክንያት መሆኑን ሲያይ በወቅቱ ትኩረቱ በዓረቡ ዐለም ስለነበርና ኢስላምን የሚያውቀው በእነርሱ በመሆኑ መፅሐፉን ከላይ በጠቀስነው ርእስ ፃፈው ። የርእሱ ትርጉም ( የዐረቡ ( የእስልምና) ብርሃን በአውሮፓ ሲፈነጥቅ ) የሚል ነው ።
ምእራባዊያን ከእስልምና አስተምሮ ወስደው መበልፀጋቸው ባልተጠላ ነበር ። ነገር ግን እነዚህ አካላት ከእነርሱ መበልፀግ ጎን ለጎን የኢስላሙ ዐለም ኋላ ቀር መሆን አለበት ብለው ከአስተምሮ ርቆ ቀብር አምላኪ እንዲሆንና የኢስላምን አስተምሮ ሳይሆን ስሜቱንና ዝንባሌውን እንዲከተል ባጀት መድበው የሰው ሀይል አሰማርተው መስራታቸው ነው ። እነዚህ አካላት ለዚህ እኩይ ተግባራቸው የሚያሰማሩዋቸው አካላት ዋነኛ ስራቸው ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ የእነሱን በመርዝ የተለወሰ አመለካከት የሚያራምድ መመልመል ነው ። በአሁኑ ሰአት አብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ በእነዚህ የምእራባዊያን ሴራ መረብ የተተበተበ ነው ።
ታዲያ በምን ሚዛን ነው በዚህ አይነት መረብ የተተበተበ ሙስሊም ማህበረሰብ ባለበትና በምእራቡ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የአለም መዘወሪያ ፖሊሲ በሚመራ ሀገር ላይ ለሚደርስ ኋላ ቀርነትና ድህነት ኢስላም ተጠያቂ የሚሆነው ? በምንም መመዘኛ ሊሆን አይችልም ። ነገር ግን ሙስሊሞች በየትኛውም ተፅኖ ስር ቢሆኑም የኢስላምን አስተምሮ መርህ በማድረግ ምርታማ በመሆን የተፅኖውን ካባ አውልቀው በመጣል ማንነታቸውን ሊያሳዩ ይገባል ።
ለዚህ የመጀመሪያው እርምጃ ኢስላም ማለት እመን ትድናለህ በሚል መርህ ሙስሊሞችን ያልከረቸመ መሆኑን በመረዳትና ኢስላም ማለት ማመን ፣ መመስከርና መተግበር ነው የሚል የህይወት መመሪያ መሆኑን አውቆ ለተግባራዊነቱ መዘጋጀት ነው ።
የኢስላም አስተምሮ መለኮታዊ የህይወት መመሪያ እንጂ spiritual cocept ( መንፈሳዊ ሀሳብ ) ላይ ብቻ የተገደበ ቁንፅል መርህ አይደለም ። በመሆኑም ኢስላምን አለመግደል ፣ አለመስረቅ በሚል መንፈሳዊ እምነት ብቻ ገድቦ ለመግለፅ መሞከር ተቀባይነት የሌለው ሙከራ ነው ። በኢስላም አስተምሮና በሙስሊሞች ዐቂዳ ላይ የሚደረገው ዘመቻ እየረቀቀና መልኩን እየቀየረ ሁሌም የሚቀጥል መሆኑን ሙስሊሞች አውቀው ዲናቸውን ሊገነዘቡና ሊጠብቁ ግድ ይላቸዋል ።

https://t.me/bahruteka


ከረድ ዝግጅት ወደ አድናቆት
🏝🏝🏝🏝

📝 የዐቂደል-ዋሲጢየህ ሸርህ ባለቤት የሆኑት ሸይኽ ሙሀመድ ኸሊል ሃራስ አል-አዝሀሪይ አላህ ይዘንላቸውና ከአዝሃር ተመርቀው የወጡ ናቸው። በፍልስፍና፣ በመንጢቅ እና በዒልመ-ልከላም (Logic) ስፔሻላይዝድ አድርገዋል።

በመቀጠል በሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ላይ ረድ እንዲጽፍ እና በዚህ ላይ ዶክትሬቱን እንዲሰራ አዘዙት!። ምክንያቱም እሱ የዒልመል ከላም የመንጢቅ(Logic) የፍልስፍና ጠላት ስለሆነ ከሸይኹል ኢስላም መጽሀፎች ከእጄ ያሉትን ሰበሰብኳቸው እና ለሶስት ወር ያክል ተማርኩ ይላል ከዚያም ውጤቱ ሳነባቸው እኔ በቃ ከዚህ በፊት እስልምናን እንዳልተረደሁ ገባኝ።

🔎 ከዚያም ኢብኑ-ተይሚየህ አስ-ሰለፊይ የሚል መጽሀፍ ጻፈ። ዶክተሬቱንም ሰለፊዩ ኢብኑ-ተይሚየህ በሚለው መጽሀፉ ሰራ። በሱ መልስ ለመስጠት ተዘጋጅቶ ነገሩ ተገለበጠ እና አል-አሽዐሪይ አል-ፈይለሱፍ አል-መንጢቂይ የነበረው በሸይኹል-ኢስላም እምነት አመነ

🎙 منقول عن محاضرة الشيخ محمد أمان الجامي رحمه الله

              قلت ➴➴➴➴➴
💡 እኔ የሚገርመኝ የሸይኹል ኢብኑ ተይሚየህ እውቀት ነው። የባጢል-ባለቤቶች ያላቸውን የባጢል እውቀት እሱ ከነሱ በላይ ያውቀዋል።


🏝 ለዚህም እኮ ነው ሸይኽ ሙሐመድ ኸሊል ሃራስ በዒልመል ከላም ወልመንጢቅ ሸይኹል ኢስላም ከሱ በላይ እንደሆነ የተረዳው።

🚥 ሸይኹል ኢስላምን በሆነ በዲን ካሉ ዲፓርትመንቶች ያገኘው ሰው ሁሉ በዚያ specialized እንዳደረገ ይናገራሉ።

👉 በዘመናችን የነበሩ እና ያሉትን ታላላቅ ዑለሞችን በምንመለከት ቃለ ሸይኹል ኢስላም ከማ ፊመጅሙዒል ፈታዋ... ከማለት አይወገዱም። በቃ እሱ በኛ ዘመን ያለ ነው የሚመስል።

♨️ ጠላቶቹ እራሱ በእውቀቱ ይመሰክራሉ። ህይወቱን በአጠቃላይ የአላህ ዲንን በመኸደም ጨረሰው።

✍ በየሁዳ፣ በነሷራ፣ በጀህሚያ፣ በሙዕተዚላ፣ በአሽዐሪያ፣ በማቱሪደያ... በመሳሰሉት የጥመት አንጃዎች አሏህ በለገሰው እውቀት መልስ በመስጠት እና በማስጠንቀቅ ሀያቱን ጨረሰው።

📿 ዚክር በማድረግ እና በተለያዩ አምልኳቸውም ጠንካራ እንደነበሩ ደረሶቻቸው ይመሰክሩላቸዋል።

🛏 رحمه الله رحمة واسعة واسكنه فسيح جناته!

📝 t.me/sead429
❴ከተወሰነ ማስተካከያ ጋር❵

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy



















20 last posts shown.