ኢትዮ ቴሌኮም በጅማ ከተማ የ5ጂ ኔትወርክ አገልግሎት አስጀመረ፤ የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ በማፋጠን ላይ!
በኢትዮጵያ ቀዳሚው የቴሌኮም እና ዲጂታል አገልግሎቶች አቅራቢ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) ኔትወርክ ማስፋፊያ አጠናክሮ በመቀጠል በዛሬው ዕለት በጅማ ከተማ አገልግሎቱን በይፋ አስጀምሯል፡፡
ኩባንያችን የ5ጂ አገልግሎትን በአዲስ አበባ እ.ኤ.አ በ2022 ካስጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ እስካሁን ድረስ፣ ጅማን ጨምሮ በ12 ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በጅግጅጋ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በባህር ዳር፣ በሐዋሳ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በሆሳዕና፣ በአርባ ምንጭ እና በቢሾፍቱ አገልግሎቱን ዕውን አድርጓል።
ቴክኖሎጂው የኔትወርክ አቅም ከመጨመር ባሻገር አዳዲስ የዲጂታል እና የፋይናንስ አገልግሎቶች፣ ለኦንላይን ትምህርት፣ ለጀማሪ የንግድ ተቋማት (startups)፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የዲጂታል ክፍተትን ለማጥበብ፣ የስማርት ስልክ አቅርቦት ለማሳደግ እና የዲጂታል ሊትሬሲን ለመጨመር አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራል።
የ5ጂ ቴክኖሎጂ የድርጅት ደንበኞችን የዕለት ተዕለት አሰራርን ከማዘመን በተጨማሪ፣ ቁልፍ በሆኑ ዘርፎች ላይ ማለትም ጤናን፣ ግብርናን፣ ትምህርትን፣ ማኑፋክቸሪንግን እና ማዕድንን፣ ትራንስፖርትን፣ ቱሪዝምን፣ መዝናኛን በስማርት ቴኮኖሎጂ በማዘመን ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡
ክቡራን ደንበኞቻችን የ5ጂ አገልግሎት ማስተናገድ የሚያስችሉ ቀፎዎች እና ሲም እንደፍላጎት በአገልግሎት ማእከላችን በማግኘት የእጅግ ፈጣኑን ኔትወርክ ተጠቃሚ በመሆን አስደናቂ ተሞክሮ እንድታገኙ በደስታ እንጋብዛለን፡፡
ለተጨማሪ፡- https://bit.ly/42Z0ygF
አዲስ ፍጥነት፣ አዲስ ምቾት፣ አዲስ አኗኗር!