‼
አስቸኳይ መልዕክት በአማራ ክልል የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል እና መቆጣጠር ከተቋቋመው ኮማንድ ፖስት፦
1. ባለፋት 3 ሣምንታት ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ቤት የተመለሳችሁ እና በአማራ ክልል ውስጥ የምትኖሩ በአስቸኳይ በየአካባቢያቸሁ ወደሚገኝ የመንግሥት የጤና ጥበቃ ተቋም ሪፖርት እንድታደርጉ እና ራሳችሁን እና ያገኛችኋቸውም ሠዎች ራሣቸውን እንዲያቅቡ!
2. ለመላ የክልላችን የገጠር ነዋሪዎች በሙሉ ያጋጠመን ችግር መድኃኒት ያልተገኘለት ወረርሽኝ መኾኑን ተረድታችሁ ለግብይትም ሆነ ለሌላ ማኅበራዊ ጉዳዮች ወደ ከተማ የምታደርጉትን ጉዞ በማቆም ባላችሁበት ራሳችሁን ከበሽታው እንድትከላከሉ፣
3. መላው የክልላችን ነዋሪዎች አሁን ካለው የወረርሽኙ አሣሣቢ ኹኔታ አንጻር እንደ አስፈላጊነቱ ታይቶ በክልሉ ውስጥ የሚደረግ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቆም ትዕዛዝ ሊሠጥ ሥለሚችል ይኸንኑ አስቀድማችሁ በማወቅ ወደ ቋሚ የመኖሪያ (መቆያ) ቦታችሁ ላይ በመኾን ከመንግሥት የሚሠጠውን ትዕዛዝ በትኩረት እንድትጠባበቁ እንዲደረግ እናሳውቃለን፡፡
የአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከል እና መቆጣጠር ኮማንድ ፖስት
ባሕርዳር