ካለህበት ቦታ ተነስ 😁
የአባቴ ልጆች እኔ ወንድማቹ ሰሞኑን ቤተ ክርስቲያን የገጠመኝን ላወራቹማ ስሙኝ... 🥰 ሰዓቱ የእግዚአብሔር ቃል የምንሰማበት ሰዓት ነበር እና አንድ የእግዚአብሔር ሰው መድረኩን ይዞ የጌታ ቃል በሚገርም መልኩ መስበክ ጀመረ እኔና አንድ ወንድሜ ደግሞ ከበስተዋላ ጥግ ላይ ተቀምጠን ስብከቱን እየሰማን ነው ከጎኔ ደግሞ አንድ ልቤ ያረፈባቸው ቢበዛ የ ስድስት አመት ልጅና አባት ተቀምጠዋል፤ ሰባኪው በሰዓቱ እንደማንኛው ኢትዮጵያዊ ሰባኪ ከጎናቹ ያለው ሰው ያዙ እና እንዲህ በሉት ማለት ያበዛል😀( ይቺም ደግሞ ቃል ሆና እንዳሰነጥቋት Just የተለመደ ስለሆነ ነው) እና ከጎኔ ያለውን ወንድሜን እንዲ እንዲያ ስለው ቆየውና ፤ ከስድስት አመት ልጇቸው ጋር ተቀምጠው የነበሩትን አባት አየት ሳደርጋቸው ከጎናቹ ሰባኪው በሉ የሚሉትን ሰው አጥተው ያንኑ ከጎናቸው ያለውን ልጃቸውን እጁን ይዘው ሰባኪው በሉ ያለው ቃል በሙሉ ሲነግሩት አስተዋልኩ በመሀል ላይ ግን ሰባኪው ከጎንህ ያለውን ሰው ካለህበት ቦታ ተነስ በልና ንገረው ብሎ ሲያውጅ እኚህ አባትም እንደለመዱት ልጃቸውን ይዘው በሉ የተባሉትን ቃል ቢሉት ልጃቸው ግን ከወንበሩ ተነስቶ አባ ልወጣ ፈቀድክልኝ ብሏቸው አረፈው😁 አባት ልጃቸውን ምን ማለት እንደፈለጉ ሊያስረዱት ቢሞክሩም ልጃቸው ግን ልቡ ውጪ ውጪውን ያይ ስለነበር ሊሰማቸው አልፈለገም ኃላ ላይ ግን አባት ሳይፈልጉ ልጃቸውን ቆጣ ብለው ወንበሩ ላይ አስቀመጡት... ምን ልላቹ መሰላቹ 🥰 አንዳንዴ እግዚአብሔር አንዳንድ ነገሮች የማይነግረን እኛ ለራሳችን በሚመቸን መልኩ ተርጉመን እንዳንረዳውና እንዳንጠፋበት ስለሚፈልግ ነው፤ እኚህ አባት ልጃቸውን በቅጡ እንዲህ በል ለማለት በአይምሮ ሳያሳድጉት ስለነገሩት ልጃቸው ማጥፋቱን ሳያውቀው ጥፍተኛ ሆኖ ተገኘባቸው፤ እግዚአብሔር ግን ይህ ህይወት በእኛ እንዲፈጠር አይፈልግም ለዚህም ነው ከእርሱ ለምንሰማቸው ነገሮች መጀመሪያ ሳያሳድገን ምንም ነገር የማያደርግልን፤ የተወደዳቹ ምንም ያህል ልጆች ብትሆኑም የታሰበላቹ ሁሉ ግን ይነገራቿል ማለት አይደለም ፤ አንዳንድ የእግዚአብሔር ዝምታዎች የእናንተን ማደግ ነው የሚጠብቁት።
@thedayofpentecost