“ የአንድ አዞ ቆዳ አንድ ሴንቲሜትር 5 ዶላር ነው የሚሸጠው ” - የጋሞ ልማት ማኀበር
በተለይ የውጪ አገር የገበያ ትስስር ባለመኖሩ ኢትዮጵያ ከአዞ ሽያጭ እስከ 60 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ እያጣች መሆኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ የጋሞ ልማት ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
ከሦስት ዓመታት በፊት ትንሽ የአዞ ስጋና ቆዳ ለውጪ አገራት ይሸጥ እንደነበር፣ ከዚያ በኋላ በገበያ ትስስር ክፍተት ገቢው በመቀዛቀዙ እንደ አዲስ ለማንሰራራት እየተሰራ መሆኑን ማኀበሩ አስረድቷል።
ስለአዞ ሽያጭ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ የጠየቃቸው የማህበሩ አርባምንጭ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ዳኘ፣ “ ከ3 አመታት በፊት 10፣ 15 ነበር የሚሸጠው። ከ3000 እስከ 5000 አዞዎች ሲሸጡ የነበረው ከ10 ዓመት በፊት ነው። እየቀሰ መጥቷል ” ብለዋል።
የማኀበሩ ሥራ የአርባምንጭ አስኪያጅ አቶ ዲዊት ዳኘ ምን አሉ ?
“ የአዞ ቆዳ የሽያጭ ሂደቱ ተቀዛቅዞ ቆይቶ አሁን ሽያጭ አልተጀመረም። አሁን በማኀበሩ ተወስዶ እየተሰራ ነው። ቆዳቸው ለሽያጭ የደረሱ ከ2500 በላይ አዞዎች አሉን። እንዴት እንደሚቀጥል ከአገር ውስጥ ካምፓኒዎች ጋር እያወራን ነው።
አሁን ተነጋግረን የውል ሂደት ላይ ነው ያለነው እሱን ጨርሰን ሽያጩ ይካሄዳል ብለን እናስባለን። በፊት ሲሸጥ የነበረው ቆዳው ብቻ ነው። ግን የአዞ ስጋው፣ ጥርሱ፣ ይፈለጋል። ስጋው በሌሎች አገራት በጣም ይፈለጋል።
አሁን 4,000 የአዞ ጫጩቶችን ለመሰብሰብ እንቁላል ዝግጁ ሆኖ ነው ያለው። ከሦስት ወራት በኋላ ጫጩት ከተፈለፈለ በኋላ ከሀይቁ ወደ ማኀበር ይመጣሉ።
የአዞ ቆዳና ስጋ በጣም ዋጋው ውድ ነው። ስለዚህ ትክክለኛ ማርኬት ሊንኬጅ ተፈጥሮ ስርዓቱ ቢዘረጋ እንደ አገር ትልቅ ገቢ እናገኛለን። በተለይ በዘርፉ የሚሰሩ የውጪ አገር ካምፓኒዎችን እያነጋነርን ነው ” ብለዋል።
ከ2,500 በላይ አዞዎች ለሽያጭ ቢቀርቡ ምን ያክል ገቢ ማግኘት ይቻላል ? ስንል የጠየቅናቸው አቶ ዳዊት፣ የአንድ አዞ ቆዳ አንድ ሴንቲሜትር 5 ዶላር እንደሚሸጥ፣ የአንድ አዞ ቆዳ እስከ 45 ሴንቲሜትር እንደሚሆን፣ አንድ አዞ በትንሹ እስከ 22 ሺሕ ብር እንደሚሸጥ፣ በጠቅላላ ከ55 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሊገኝ እንደሚችል አስረድተዋል።
በማኀበሩ ስንት ሠራተኞች አሉ ? የአዞ ስጋ ምግብነት ላይ ይውላል ወይ ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቶ ዳዊት፣ “ የአዞ ስጋ ይበላል። በኛ አልተለመደም። ግን የኛ ሰዎች የ40 ዓመት ልምድ አላቸው። ብራንቹ ተቋቁሞ 41 ዓመቱ ነው። ረጅም ልምድ ያላቸው ሰዎች አዞ የመመገብ ልምድ አላቸው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
አቶ ዳዊትና አንድ የማኀበሩ አስጎብኝ በኢትዮጵያ ብዙ እንዳልተለመደ፣ ኬኒያን ጨምር በሌሎች አካባቢዎች አዞ ለምግብነት እንደሚውል ተናግረዋል።
አቶ ዳዊት፣ “ የአዞ ሬስቶራንት ለመክፈት ” እንዳሰቡ ገልጸው፣ “ ፈረንጆች ይመጣሉ እዚህ ይመገባሉ፤ ቀስ በቀስ የኛ ሰዎችም እያዩ እየተመገቡ ይሄዳሉ ” ነው ያሉት።
አክለው፣ በማኀበሩ ወደ 35 ገደማ ሠራተኞች እንዳሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹ ሲሆን፣ የማኀበሩ አስጎብኝ በሰጡት ገለጻ ደግሞ፣ “60 በመቶ የሚሆኑት ሰራተኞች የአዞ ስጋ ይመገባሉ” ብለዋል።
አንድ አዞ ለሽያጭ ለመቅረብ ብቁ እስከሚሆን ድረስ 62 ኪሎ ግራም ስጋ እንደሚመገብ፣ አዞ የሚመገበው የአሳ፣ የአዞ ስጋ እንደሆነ፣ አሳማ ሌሎች የእንስሳት ዝርያዎች እንዳሉ፣ የህክምናና ሌሎችን ጨምሮ በአጠቃላይ ማኀበሩ በአመት እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግ ተመልክቷል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia