የኢትዮጵያ የስነ-ህዝብ እና ጤና ዳሰሳ ጥናት 82 በመቶ ደርሷል ተብሏል።
በየአምስት አመቱ የሚከናወነው የኢትዮጵያ የሥነ ሕዝብና ጤና ዳሰሳ ጥናት (EDHS) መካሄድ ከነበረበት ጊዜ በኮቪድ እና በሌሎች ልዩ ልዩ ምክንያቶች ሳይካሄድ በ 4 ዓመታት ዘግይቷል።
ይህ ጥናት በስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም ትግበራ ላይ በማካተት ከ ሐምሌ 20/2016 ዓም ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል።
በአሁኑ ሰዓት ጥናቱ 82 በመቶ መድረሱን እና እስከ ታህሳስ 30 ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሳፊ ገመዲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ከጤና ሚኒስቴር እና ሌሎችም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ጥናቱ እየተሰራ ነው የተባለ ሲሆን ሲጠናቀቅ የእናቶች ፣የህጻናት እና የወጣቶችን ሃገራዊ የጤና ሁኔታ፣ ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ስርጭት ፣የስነ ተዋልዶ ጤና ፣ጾታዊ ጥቃቶች ሁኔታ እንዲሁም የእናቶችን የእርግዝና ጊዜ እንክብካቤ ሁኔታን ያሳያል ተብሎለታል።
ከ 22 አመታት በኋላ እየተከናወነ የሚገኘው ሁለተኛው ዙር የግብርና ምርቶች ቆጠራም በናሙና የተመረጡ አርሶ አደሮች የግብርና ምርት አመራረትና የግብዓት አጠቃቀማቸውን የሚመለከት ቆጠራ ሲሆን ከ 50 ሺ በላይ ወጣቶች በቆጠራው እየተሳተፉ መሆኑን አቶ ሳፊ ነግረውናል።
በናሙናነት በተመረጡ 39,345 የቆጠራ ቦታዎች የግብርና ቆጠራው እየተከናወነ ነው የተባለ ሲሆን ቆጠራው ሰኔ 30/2017 ዓም ይጠናቀቃል ተብሏል።
ይካሄዳሉ ከተባሉ ቆጠራዎች አንዱ የሆነው የኢኮኖሚ ድርጅቶች(ኢንዱስትሪዎች) ቆጠራ አንዱ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት እየተከናወኑ የሚገኙት ጥናቶች በርካታ የሰው ሃይል እየተሳተፈባቸው የሚገኙ በመሆናቸው አለመጀመሩን ተነግሯል።
አቶ ሳፊ "ለጊዜው ተይዞ ነው ያለው እነዚህ ቆጠራዎች ከተጠናቀቁ በኋላ ለማካሄድ ሃሳብ አለ እስካሁን የመጨረሻ ውሳኔ ላይ አልተደረሰም" ብለዋል።
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ከትንንሽ ቢዝነሶች እስከ ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ምን ያህል ያመርታሉ፣ምን ያህል የሰው ሃይል አላቸው፣ ምን ያህሎቹ ለሚያመርቱት ምርት የሃገር ውስጥ ግብዓቶችን ይጠቀማሉ ከውጪስ ምን ያህል ምርት ያስገባሉ የሚለውን ይመለከታል ተብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethmagazine