ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ "የኅብረተሰብ ጤና ዶክተር" የተሰኘ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት አዘጋጀ።
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የኅብረተሰብ ጤና ዶክተር / Doctor of Public Health (DrPH) ተማሪዎች ሊቀበል መሆኑን አስታውቋል።
ዩኒቨርስቲው ያዘጋጀው ይህ የትምህርት ሥርዓት በሀገራችን ከዚህ ቀደም ያልነበረ ትምህርት መሆኑ ነው የተገለጸው።
ይህም በሀገራችን የኅብረተሰብ ጤና አገልግሎት ውስጥ የሚታዩ መሰረታዊ ችግሮችን መፍታት የሚችሉ ባለሙያዎችን ለማፍራት ታስቦ የተዘጋጀ በመሆኑ ነው የተገለጸው።
ሥርዓተ ትምህርቱ አስፈላጊውን ሂደት አጠናቆ እውቅና የተሰጠው በመሆኑ በቅርቡ ተማሪዎችን እንደሚቀበል የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንሥ ኮሌጅ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር አህመድ መሐመድ ገልጸዋል።
የኅብረተሰብ ጤና ዶክተር (DrPH) ሁለገብ ዲግሪ ሆኖ በህዝብ ጤና የላቀ ትምህርት አመራር ፣ አስተዳደር ፣ ኮሙኒኬሽን እና የፈጠራ አስተሳሰብ ክህሎትን ማጎልበትና መቀየር ላይ አተኩሮ በስራ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የሚሰጥ ትምህርት ነው ተብሏል።
@tikvahethmagazine