" ከፍተኛ የመድኃኒት፣ የሳሙና እና የተለያዩ ግብአቶች እጥረት ገጥሞኛል " ተስፋ አዲስ የካንሰር ህሙማን ህፃናት ማዕከል
ከተቋቋመ 11 ዓመታት ያለፉት ተስፋ አዲስ የካንሰር ህሙማን ህፃናት ማዕከል ሥራውን የጀመረው በ2005 ዓ.ም ነበር።
ተቋሙ አሁን ላይ ከአዲስአበባ ውጭ በተለያዩ የክልል ከተሞች በጅማ፣ ጎንደር እና በትግራይ እየተንቀሳቀሰ ይሰራል።
ዋና ዓላማውም አቅም የሌላቸው በካንሰር በሽታ የተያዙ ህፃናትን ሙሉ ወጫቸውን እስከ አስታማሚ ቤተሰቦቻቸው በመሸፈን ማገዝ ሲሆን ላለፉት ዓመታትም ለብዙ ህጻናት እንደደረሰ ይገልጻል።
አሁን ላይ ወደ ማዕከሉ የሚመጡ ህፃናት ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ከፍተኛ የሆነ የመድኃኒት እጥረት መከሰቱን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሳራ ኢብራሂም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ድርጅቱ ከተመሠረተበት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ሦስት ሺሕ ገደማ የሚሆኑ የካንሰር ታካሚ ሕፃናትን ታድጓል ሲሉ ዋና ሥራ አስኪያጇ ገልጸዋል።
አሁን ላይ ደግሞ ባሉት የአዲስ አበባ፤ የጅማ፤ ጎንደር እና መቐሌ ማዕከላት ለ260 ህፃናት እና ቤተሰቦች ሙሉ ወጫቸውን በመሸፈን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በተጨማሪም በተመላላሽ እና በቋሚ የህክምና አገልግሎት ደግሞ ከ1140 በላይ ለሚሆኑ ማዕከሉ እየሰጠ መሆኑን ሥራ አስኪያጇ ገልፀዋል።
አያይዘውም ህፃናት ሕክምናቸውን እንዳያቋርጡ ከማደሪያ እስከ ምግብና መድኃኒት፣ የሥነ ልቦና ትምህርት እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠን ነው ሲሉ ሥራ አስኪያጇ ተናግረዋል።
እስካሁን ለማዕከላቱ ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጆቶች ድጋፋቸውን ባያቋርጡም ድጋፉ ግን በቂ ባለመሆኑ በማዕከሉ ከፍተኛ የሆነ የመድሀኒት እና የሳሙና እጥረት መከሰቱን ወ/ሮ ሳራ ጠቁመዋል።
የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ሳሙና፣ ዱቄት ወተት፣ ስኳር፣ ዘይት እና የመሳሰሉ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን በመግለጽ አሁን ላይ ግን ድጋፉ መቀዛቀዙን አክለዋል።
የካንሰር በሽታ ረጅም ጊዜ የህክምና ክትትል ስለሚወስድ ማዕከሉ ለታካሚዎች እና ላስታማሚዎች ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት ለመቀጠል የግብአት አቅርቦት እጥረት በመከሰቱ ማኅበረሰቡ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ማዕከሉን ማግኘት እና ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ
📌አዲስአበባ :- ወ/ሮ ሳራ ኢብራሂም
ስልክ:- 0911725455
📌ጅማ :- ወ/ሮ ብርቱካን
ስልክ:- 0935071136
📌ጎንደር:- አቶ ወንድሙ
ስልክ:- 0928503970
📌መቀሌ:- ወ/ሮ ጺዮን
ስልክ:- 0904231532
እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Tesfa Addis Parents Childhood Cancer Organization (TAPCCO) 1000036686492
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine