"ስምንት ሀገራት የኤችአይቪ ህክምና አቅርቦት እጥረት ሊያጋጥማቸው ይችላል" WHO
የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) መቋረጥ ምክንያት ስምንት ሀገራት የኤችአይቪ (HIV) ህክምና ሊያልቅባቸው ይችላል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ።
ድርጅቱ በሚቀጥሉት ወራት በሄይቲ፣ ኬንያ፣ ሌሴቶ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ማሊ፣ ናይጄሪያ እና ዩክሬን የኤችአይቪ ህክምና አቅርቦት በሚቀጥሉት ወራት ሊያሟጥጡ እንደሚችሉ ገልጿል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ "በኤችአይቪ ፕሮግራሞች ላይ የሚስተዋለው መስተጓጎል የ20 አመታትን ልፋት የሚቀለብሰው ሊሆን ይችላል" ብለዋል።
ይህም ከ10 ሚሊዮን በላይ ተጨማሪ የኤችአይቪ ተጠቂዎችን እንዲሁም በቫይረሱ ምክንያት ሶስት ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት ሊዳርግ እንደሚችልም አክለዋል። ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ሦስት እጥፍ በላይ ሊያደርሰው ይችላል ነው ያሉት።
"ዩናይትድ ስቴትስ ለሀገሮች ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ የምታቆም ከሆነ በሥርዓትና ሰብዓዊነት በተሞላበት መንገድ፥ አማራጭ የገንዘብ ምንጭ እንዲያገኙ በሚያስችል መልኩ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባት" ሲሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ ተናግረዋል። (Reuters)
@Tikvahethmagazine @tikvahmagbot