“ በአምበልነት በመመረጤ ተደስቻለሁ “ ቹዋሜኒ
የሪያል ማድሪዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኦርሌን ቹዋሜኒ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድንን በሚቀጥሉት ጨዋታዎች በአምበልነት እንዲመራ ተመርጧል።
“ የብሔራዊ ቡድኑ አምበል በመሆኔ በጣም ተደስቻለሁ “ ሲል የገለፀው ቹዋሜኒ ሀላፊነቱን የምረከበው በትልቅ ክብር ነው በማለት ተናግሯል።
የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ በበኩላቸው ቹዋሜኒን ለሀላፊነት የመረጡት አስፈላጊ ያሏቸውን መስፈርቶች ያሟላ በመሆኑ እንደሆነ ገልጸዋል።
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አምበል ኪሊያን ምባፔ በጉዳት ምክንያት ብሔራዊ ቡድኑን እንዳልተቀላቀለ ይታወቃል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe