እስራኤል በመላው ጋዛ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እንዲቋረጥ አዘዘች
የሀገሪቱ የኢነርጂ ሚኒስትር ኢሊ ኮኸን "ታጋቾችን ለማስለቀቅ እና ሃማስ ከጦርነቱ በኋላ በጋዛ ህልውና እንዳይኖረው ለማረጋገጥ ሁሉንም አማራጮች እንጠቀማለን" ሲሉ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ የሰጡት ትዕዛዝ በተለይ የተጣራ የመጠጥ ውሃ ለማቅረብ የሚውሉ ማሽኖችን ከስራ ውጭ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
የጠቅላይይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አስተዳደር በቀጣይም ወደ ጋዛ ውሃ እንዳይገባ ሊከለክል እንደሚችልም ነው የተነገረው።
እስራኤል ባለፈው ሳምንት እሁድ ማንኛውም የሰብአዊ ድጋፍ ወደ ጋዛ እንዳይገባ ማገዷ ይታወሳል።
እስራኤል ወደ ጋዛ ሰብአዊ ድጋፍ እንዳይገባ መከልከሏ ከፍተኛ ተቃውሞ እያስነሳባት ነው።
"ለንጹሃን ህይወት መቀጠል ወሳኝ የሆኑ ሰብአዊ ድጋፎች እንዳይገቡ መከልከል የጅምላ ቅጣት" ነው ብሏል የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጽህፈት ቤት።
https://t.me/voa_amharic1