ኃላፊው በደፈጣ ጥቃት ተገደሉ‼
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የግራር ጃርሶ ወረዳ የጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ታደሠ ተፈሪ፣ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ትናንት ምሽት 11 ሰዓት ገደማ በፈጸሙት የደፈጣ ጥቃት ተገድለዋል።
እንደ ዋዜማ ራድዮ ዘገባ ከሆነ፣ ታጣቂዎቹ የደፈጣ ጥቃቱን የፈጸሙት፣ በወረዳው አዲስጌ ቀበሌ ልዩ ስሙ ''ሲልሚ'' በተባለ ሥፍራ ነው።
“ከኃላፊው ጋር አብረው የነበሩት የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዝናቡ በለጠ፣ ከታጣቂዎቹ የእሩምታ ተኩስ ለማምለጥ ሲሞክሩ ድንጋያማ ገደል ውስጥ ጉዳት እንደደረሰባቸው” የዘገበው ራድዮው “ፍቼ ሆስፒታል ለሕክምና መግባታቸውን” ምንጮቼ ነገረውኛል ብሏል።
ወረዳው ከአማራ ከልል ሰሜን ሸዋ ዞን ለሚ ወረዳ ጋር ድንበር እንደሚጋራ የጠቀሰው ዘገባው፤ አመራሮቹ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው፣ በአከባቢው በሚገኝ አንድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምልከታ አድርገው ሲመለሱ ነው ሲል አስረድቷል።
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ⤵️
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ይህንን በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ ⤵️
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g