ደበቷ ። ቀና ስትል ነበር እስከዛሬ ልብ
ብዬ ያላየሁትን ለየት ያለ ቀለም ያላቸውን አይኖቿን ያስተዋልኩት። አንደኛው ቡናማ ሲሆን
ሌላኛው ሰማያዊ ነበር። በሁኔታው ተገርሜ
"ዓይኖችሽ ደሞ እንዴት ነው የሚያምሩት!? ደስ ሲሉ! እንዳንቺ አይነት ዓይኖች በኖሩኝ"
ስላት የልጅነት ፊቷ እንደሙሉ ጨረቃ ሲበራ አስተዋልኩት። ያልጠኑ ለጋ እጆቿን አፈራርቄ
እየሳምኩ
"አባትሽ የት ሄዶ ነው የምትጠብቂው?"
"ዘመቻ!" አለቺኝ
"ዘመቻ ምንድነው?" አልኳት። አልመለሰቺልኝም። እኔም አላስጨነቅኳትም ። በስተማዶ
ያለውን ሱቅ እያየሁ
"ምን ልግዛልሽ?" ስላት መልስም ሳትሰጠኝ ከግቢ ውስጥ
"ፍቅር! የት ነው ያለሺው?" የሚል ድምፅ ስትሰማ ከእጄ ውስጥ ሹልክ ብላ ወደ ግቢ
ለመግባት ስትጣደፍ ካንዲት እንደ ጅማት ከቀጠነች ፣ ሻርፕ ነገር ካጣፋችና፣ አከታትላ
አፏን በሻርፗ አፍና ከምትስል ሴት ጋር ተገጣጠመች።
"አትውጪ አላልኩሽም?" ተቆጣቻት።
"እንደምን አደርሽ? እናቷ ነሽ? አትቆጫት እኔ ሰላም በይኝ ብያት ነው ። በአይን ስንተዋወቅ
ቆየን፣ ዛሬ ነይ ጨብጭኝ ብያት ነው" አልኳት እየሳ'ኩ።
*
*
እናቷን አስፈቅጄ አቅፊያት ባሻገር ወደሚገኘው ሱቅ ይዣት ሄጄ
"ምንድነው የምትፈልጊው?" አልኳት
"አቡወለድ" ድምፆን ዝቅ አርጋ አቀርቅራ ስለምታወራ በመከራ ነበር የሰማኋት። እሱንም
ባለሱቁ ከድር አግዞኝ ነው። አንዳንድ ሰው ጎበዝ ነው። እንደ ልሳን መተርጎም የልጅ አፍን
መተርጎም ይችላል። ነገሩ ሁለቱም የመላእክት ቋንቋ አይደል!
ግን ግን ጣፋጭ ልጅነታችንን ማነው የሚነጥቀን? ኮልታፋ አንደበት፣ ንፁህ ልብ፣ ጭንቀት
አልባ ኑሮ፣ ቅዠት አልባ እንቅልፍን ማነው የሚወስድብን??? ልጅነቴ፣ ልጅነቴ፣........
ብስኩቱን ብቻ አልነበረም የጋበዝኳት ፍቅርን። ምሪንዳም ጭምር እንጂ! አባቴ ከሰጠኝና
ቆጥቤ ለሻይም፣ ለባስም፣ ለፎቶኮፒም ከማረጋት ሃምሳ ብር ላይ ነበር ለፍቅር የፍቅር
ግብዣዋን በማለዳ "ደፍ" ያረኩባት። ከደስታዋ ብዛት ነብስም አልቀረላት ነበር። ከድር
መልሱን እስኪያዘጋጅልኝ ድረስ እርሷ ብስኩቷን በቀኝ እጇ ፣ ቀኝ እጄን በትንሽዬ ግራ እጇ
ይዛ እኔ ደሞ ተከፍቶ ቆርኪው የተገጠመበትን ሚሪንዳ በግራ እጄ ይዤ ትጠብቃት
ወደነበረችው ሳል ያደከማት ብቻ ሳትሆን ያሰለላት "እፍ ቢሏት እልም" ከምትል እናቷ ጋር
አድርሺያት አጎንብሼ ክብ ቢጫ ፊቷን ስሜ ምሪንዳውን አስጨበጥኳት።
"በይ ቻዎ ፍቅር እንገናኛለን" አልመለሰቺልኝም። ይልቅ በስስት ቁልቁል የምታያት እናቷ
ደጋግማ ደረቅ ሳል ስላ ስታበቃ
"አስቸገረችህ አይደል? እግዚአብሔር ይስጥልኝ!" አለቺኝ ጉርጉድ ያሉት አይኖቿ በደስታ
በርተው። እኔ የምለው ሰው ግን ለምንድነው ከራሱ በላይ የወለደውን ሲወዱለት ደስ
የሚለው??
ከዛ በኋላ ፍቅርን ያገኘኋት ከሶስት ቀን በኋላ ነበር። ዘወትር የምትቆምበት ስፍራ በትንሹ
በተከፈተው በር ስር ቆማ ቢጫና ቡናማ አይኖቿን እያቁለጨለጨች። ፊቷ ላይ የደረቀ እንባ
መስመር ሰርቷል ። እጆቿ አቧራ ልሰዋል። እንደ አዋቂ ጥልቅ ሃሳብ ውስጥ ገብታ
አመልካች ጣቷን አፏ ውስጥ እንደሻጠች መሬት መሬት እያየች ቆማለች። ስላላየቺኝ ቆም
ብዬ
"ፍቅል" አልኳት በራሷ አጠራር። ስታየኝ እምቡጥ ከንፈሯ ፍልቅቅ ብሎ ተከፍቶ ምስር
የሚያካክሉ የወተት ጥርሶቿ አንፀባረቁ። ወደ ኋላ ዞር ብላ ተገላምጣ በግማሽ በተከፈተው
በር ሾልካ ወደ እኔ መጣች። አቅፌ አንስቼ ደጋግሜ ስሚያት
"ዛሬስ ምን እየሰራሽ ነው በር ላይ ?"
"አባዬን እየጠበኩ" ልስልስ ባለ ዝግተኛ ድምፅ መለሰችልኝ። ግራ ተጋብቼ ዝም አልኩ።
በኋላ ግን ከባለሱቁ ከድር እንደሰማሁት አባቷ በመኪና አደጋ ሰበብ በነብስ ማጥፋት
ወንጀል ተፈርዶበት ወህኒ እንዳለ አጫወተኝ። ከታሰረ አንድ አመት ሆኖታል።
"ምን ሆነሽ ነው ያለቀሺው ደሞ?" ፊቷ ላይ የደረቀ እንባዋን በጣቴ እየነካካሁ
እየጠቆምኳት።
"አላጫውትም ብለውኝ"
"እነማን?" ስል ጠየኩ
በትንሽዬ ጣቷ ከማዶ ላይ አሸዋማውን አፈር እየካቡ የሚጫወቱትን ከእርሷ ትንሽ በእድሜ
ከፍ የሚሉ ልጆችን እየጠቆመችኝ
"እነሹ" አስከትላም "ዓይንሽ ያሽፈራል ይላሉ" ብላኝ ለምቦጯን ጣለች። ቅድም እንደ አዋቂ
ያስተከዛት ጉዳይ ይሄ እንደነበር ታወቀኝና ውስጤ በሃዘን ተመሳቀለ።
"ዝም በያቸው! ያንቺ አይነት የሚያምር አይን ስለሌላቸው ነው! ብዬ ሁለቱን አይኖቿን
" ቆይ ልሳምልሽ" ብዬ እያፈራረኩ ደጋግሜ ሳምኩላት።
ደ..........ስ አላት! ጥላው የነበረው ፊቷ ሲሰበሰብ፣ ተክዞ የነበረ ትንሽዬ ልቧ በኩራት
ሲያብጥ ፣ ሁለት ቀለም ያላቸው ያይኖቿ ብሌኖች ሲሰፉ እዛው ሆኜ መስክሪያለሁ። ፍቅር
ታከመች! አይኖቿን የሚወድላት፣ የሚያምሩ ዓይኖች እንዳሏት የነገራት፣ አፈራርቆ የሳመላት
አንድ ሰው አገኘች።
ከዛ በኋላ ለሁለት ወር ያህል እኔና ፍቅር ጔደኛሞች ሆንን። እዛው ሰፈር ካሉት የዘመዶቼ
የልጅ ልጆች ጋር ወስጄ ጔደኛ አደረግኳት። ቀድሜ በነገርኳቸው መሰረት ዓይኖቿን
"ሲያምር!" እያሉ አደነቁላት። ጥቂት ዘግይቶ እኔ ክፍለሃገር ስራ አግኝቼ ስሄድ በቁም ነገር
ፍቅርንና እናቷን ተሰናብቼ ነበር። ፍቅር አለቀሰች። ተመልሼ እንደምጠይቃት ብነግራት፣
ባባብላትም እምቢኝ አለች። እንዴት ትመን? አባቷም ድንገት ሄዶ በዛው ከቀረ ዓመት
አለፈው። ዘወትር ማለዳ አንስቶ ትጠብቀዋለች። ግን አልተመለሰም። እናቷ "ዘመቻ ሄዷል"
ነው ያለቻት። ታስሯል ላለማለት። አሁን ደግሞ እኔን ጔደኛዋን ልታጣ ነው። ፍቅር አልቅሳ
ደክሟት እንቅልፍ እስኪይዛት ጠብቄ ነበር ግንባሯን ስሚያት የወጣሁት። በርግጥ ከነቃች
በኋላ ከእውነቱ ትላተማለች። ከዓመት በኋላ ይመስለኛል እዛ ሰፈር ያሉ ዘመዶቼን ጥየቃ
ስሄድ ባስፈልጋት እርሷም እናቷም አልነበሩም። ከጥቂት ወራት በፊት ሰፈር እንደቀየሩ
ሰማሁ። እዛ ሰፈር በተመላለስኩበት ጥቂት ቀናት ውስጥ ትቆምበት በነበረው ግቢ በር ስር
አይኖቼን ወርወር አደርጋለሁ። ፍቅርን ግን ለብዙ አመታት አላየኋትም ነበር። ይህው ዛሬ
የክትፎ አምሮቴን ልወጣ እርሷም ፍላጎቷ ከአቡወለድ ብስኩት ወደክትፎ አድጎ ልትበላ፣
ካባቷ ጥበቃ ወደ ሰርጔ ቀን ጥበቃ አድጋ ተገናኘን። አጋጣሚው ህልም እየመሰለኝ
"እንዴት ልታውቂኝ ቻልሽ ግን? እንዴት አስታወሺኝ?" አልኳት።
"እንዴት እረሳሀለሁ ጋሼ? ሁለት ቀለም ያላቸው አይኖቼን እንደሚወድልኝ የነገረኝን ሰው
እንዴት ረሳዋለሁ!? ስትነግረኝ እኮ ስስ ትንሿ ልቤ ላይ ነበር ለዘላለም የፃፍከው። አይኖቼን
ስትስምልኝ አይኖቼን መሳሜ ብቻ አልነበረም የተሰማኝ። ነብሴንም ነበር የሳምካት።
በቃላትህ አከምከኝ ። አሁን ሰዎች በአይኖቼ ቀለም ተገርመው ትኩር ብለው ሲያዩኝ አንተ
'ደሞ እንዴት የሚያምሩ ዓይኖች ነው ያሉሽ? እንዳንቺ አይነት የሚያምሩ ዓይኖች በኖሩኝ ።
ዝም በይ ቀንተውብሽ ነው' ያልከኝ ቃላት እዝነህሊናዬ ውስጥ ያስተጋባል። ልዩና የሚያምሩ
ዓይኖች እንዳሉኝ ስለማውቅ ኮራባቸዋለሁ። እድሜ ላንተ! ጋሼ.....ደህና ነህ ግን?"
ጉንጬን እየዳበሰች ጠየቀቺኝ።
*
*
*
እነርሱ ያዘዙት ምሳ ሲመጣ እየተጫወትን አብረን መመገብ ጀመርን ። ስለ አባትና እናቷ
ደህንነት ልጠይቃት አስቤ ጥሩ ያልሆነ ዜና ብሰማ የጨዋታውን ድባብ ሃዘን ያጠላበታል
ብዬ ስለፈራሁ ለግዜው እሱን ትቼ ወደ እጮኛዋ እያየሁ
"እድለኛ ነህ! ይችን የመሰለች ቆንጆ ልጅ ልታገባ ነው!" አልኩት ። ሲስቅ ሚጥሚጣው ትን
ሲለው አይታ ውሃ የያዘውን ብርጭቆ እያቀበለችው እርሷም በተራዋ ስቃ
"ዛሬ እኮ አስቀያሚ የለም ጋሼ?! ልጆቹ ሁሉ ቆንጆዎች ናቸው" አለችኝ። የጎረስኩትን ውጬ
ሳበቃ
"አዎ ቆንጆዎች ናቸ