አንድ ሰው ሌላውን ሰው ለምን ይወዳል? አንድ ብላቴና አንዲትን ኮረዳ የሚወዳት ለምንድን ነው? ስለሌሎች ሰዎች አላውቅም:: እኔ ግን ወሰንን የወደድኳት በብርሀን ተከባ ስላየሁአት ነው::
ለመስቀል ለመስቀል የከተማችን ህዝብ በጠቅላላ ተሰብስቦ ዳመራ የሚያቀጣጥልበት ጉብታ ከከተማው ወጣ ብሎ አለው::እስላሙ የሙስጠፋ አባት እንኳን ከነቤተሰባቸው ለወሬ ብለው ይመጣሉ:: ሲመሽ አንድና ሁለት ሰአት ገደማ ህዝቡ ዳቦቱን ይዞ ከየቤቱ ሲወጣ የንፋስ መውጪያ ከተማ ከሰማይ የወረደች ትመስል ነበር::
. . . . .
ወሰን የለሽን ያየሁዋት ይሄን ጊዜ ነበር:: ሰዎች ወደ የቤታቸው ለመሄድ መበተን ሲጀምሩ ወደ እሳቱ ተጠግታ ተቀመጠች:: ብን ያለች ነጭ ኩታ ለብሳለች::
. . . . .
የወሰን ፊት ፀጥ ያለ ነበር:: ሰላም ያለበት ይመስላል:: አልፎ አልፎ ምክንያቱን ባላውቅም በትንሹ ፈገግ ትላለች::አፌን ከፍቼ አያታለሁ:: ከበስተኋላዋ የቆመው ከነጠላና ከጋቢ የተሰራው የሰው ግድግዳ ሲፈርስ ተአምር ተፈጠረ:: ያ የኖራ አገር ባህል ልብስ ግድግዳ ሰማይ ላይ የምትፎልል ድፍን ጨረቃ ከልሎ ኖሯል:: ታዲያ ጠቆር ያለው የወሰን ጭንቅላት ድፍኗ ጨረቃ መሀል ላይ የተቀመጠ መሰለ:: ጨረቃዋ ቢጫ ናት:: የጨረቃዋ ማድያት የለም:: ታዲያ ወሰን በስዕል ላይ የማያትን ትንሽ ማሪያም መሰለችኝ::
**
#ግራጫ ቃጭሎች
#አዳም_ረታ
@wegoch