ነጭ እኮ አይደንግጥ?!
.
«ዘውድአለም ታደሠ»
.
አውስትራሊያ እስካሁን በኮሮና ጉንፋን 249 ሰዎች ተይዘው
የሞቱት 3 አዛውንቶች ብቻ ናቸው። ነገር ግን ህዝቡ በተጋነነው
የሚዲያ ወሬ panic ስላደረገ ልክ ፊልም ላይ እንደምናየው
ባለው ብር ሁሉ እህል እየገዛ ሱፐርማርኬቱን ባዶ አድርጎታል።
በግፊያው አካል ጉዳተኞችና አዛውንቶች እየተረጋገጡ ስለሆነ
ሱፐርማርኬቶቹ ተጨማሪ ሴኪዩሪቲዎች ለመቅጠር ተገድደዋል።
ምግብ ተርፎ በሚደፋባት ሃብታሟ አወስትራሊያ ባሁን ሰአት
ዘይት እንደሜርኩሪ እያደባደበ ነው። እግዚኦ አትሉልኝም ታዲያ?
በሽታው እጅ በመታጠብና ንክኪን በመቀነስ በቀላሉ የሚቆም
ቢሆንም የምእራባውያን ሚዲያ የቻይናን ኢኮኖሚ ለማንኮታኮት
ቻይና ላይ ኮሮና የተባለ መአት ወረደ ብለው አራገቡ። የቻይና
የንግድ እንቅስቃሴ በአንድ ቀን ወደቀ። ግዙፍ ካምፓኒዎቿ
ሰራተኛ በተኑ። ለአለም ገበያ ለማቅረብ ያመረተቻቸውን ምርቶች
መጣያ ስታጣ በመርከብ ወደቬትናም ወስዳ በርካሽ ጣለቻቸው!
አሁን የሆዷን በሆዷ ይዛ ነዋሪው ከቤቱ እንዳይወጣ በሩን
በመበየድ ጭምር አግሬሲቭሊ በሽታውን ተቆጣጠረችውና ኳሱን
መልሳ ወደአሜሪካና ወደአውሮፓውያኑ ጠለዘችው። እነአሜሪካ
ቻይናን ለማንኮታኮት ከሚገባው በላይ አጋንነው ያወሩለት ኮሮና
ወደራሳቸው back fire አደረገ! ይኸው ዛሬ በአመት 39 ሺ
ሰው በጉንፋን ብቻ የሚሞትባት አሜሪካ ህዝቧ ፓኒክ ስላረገባት
ብቻ ሳትወድ በግድ state of emergency ስታውጅ ቻይና
ፈገግ ብላ ታያታለች።
የአሜሪካና የቻይና trade war መጨረሻ ላይ የደረሰ
ይመስላል። ተንታኞቹ እንደሚሉት ከ 9/11 ጥቃት በኋላ ስቶክ
ማርኬቱ እንዳሁኑ ወድቆ አያውቅም። ኮንሲኩዌንሱ የኛን የሰፈር
ወንዝ ዳር ያለች ጀልባም ከአለት ጋር ማላተሙ አይቀርም።
ኦልሞስት ሁሉንም ነገሮች import እናደርጋለን። ከውጪ
የምናስገባው ከምርታችን ጋር በስልክም አይገናኝም። ( 3
billion ገደማ export እያረግን ለ import 11 billion
የምናወጣ ጉዶች ነን)
ቻይና በእርግጠኝነት በመጪው ጥቂት ቀናት ውስጥ ሪከቨር
አርጋ እንደመንግስቱ ሃይለማሪያም “ለምሳ ያሰቡንን ለቁርስ
አደረግናቸው” ብላ ወደሽቀላዋ መመለሷ አይቀርም።
አሁን ላደጉት ሐገራት በሽታው ሳይሆን ድንጋጤው ነው አስጊ
ደረጃ ላይ የደረሰው። ሰውን መቆጣጠር አቅቷቸዋል። ነጭ ለካ
እንዲህ ድንጉጥ ነው? እኛኮ ሴንትራል አፍሪካ ያ አስቀያሚ
ኢቦላ የተባለ በሽታ ሲከሰት እንዲህ አልቀወጥነውም። ነጮቹ
ግን ፍርሃታቸውን ማኔጅ ማድረግ አልቻሉም ነው የሚባለው። ለ
toilet paper ተናንቀው ሲደባደቡ ሁሉ አይተናል። ጣሊያን ሼባ
ስለሚበዛ ነው መሰለኝ በዛ ያለ ሰው ጭሮባታል። ሁለት
ጣሊያናውያን ኢትዮጵያ ለጉብኝት መጥተው መመለሻ ግዚያቸው
ሲደርስ “ተመልሰን አንሄድም” ማለታቸውን ስንሰማ «ቧ ግዜ
ለኩሉ» ብለናል!
እናማ ባሻዬ እንደነገርኩህ ነው ... ከአቅሙ በላይ የገዘፈው
ኮሮና እስካሁን 160 ሺ ሰዎችን ይዞ ስድስት ሺ ሰው ገድሏል።
ከ70 ሺ በላዩ ደግሞ ድነው ወደቤታቸው ሄዱ። ትናንት ቢቢሲ የ
104 አመት አዛውንት ከኮሮና አገገሙ ብሎ ፒፓውን ለማረጋጋት
ሞክሯል (“አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው” አለች ቢዮንሴ
)
እስካሁን አንድ ጥቁር ብቻ ነው የሞተው። (እሱም ሌላ ተጓዳኝ
በሽታ ነበረበት አሉ) ፈይሳ አዱኛ በኪነጥበቡ ጋርዶናል አባዬ።
ለማንኛውም ህዝቤ ሆይ ውሃ አይገድልም እጅህን ታጠብ።
እንደእቁብ ዳኛ ያገኘኸውን አትጨብጥ። ብትችል ባውቶቢስ
አትጠቀም (ዎክ እኮ ለጤናህም ጥሩ ነው) የኮሮና ሚመስል
ምልክት ካየህ ወደሰው ሳታስተላልፍ ሳትጨናነቅ ሃኪም ጋር
ደውል። ታክመህ ትድናለህ። በቀላሉ ለሚያገግም በሽታ
አምቡላንስ ሰብረህ የምታመልጠውኮ አለቅጥ አጋነው
ስላስደነበሩህ ነው። ንፅህናህን በመጠበቅና ቶሎ በመታከም
ሃላፊነትህን ተወጣ! ከዚህ ውጪ ግን አታካብድ! ከሰማይ
የወረደ መቅሰፍት አይደለም። ኮሮና በሽታም፣ ፖለቲካም፣
የኢኮኖሚ ጦርነትም፣ የሚዲያ ቢዝነስም ነው!
@wegoch
@wegoch
@wegoch
.
«ዘውድአለም ታደሠ»
.
አውስትራሊያ እስካሁን በኮሮና ጉንፋን 249 ሰዎች ተይዘው
የሞቱት 3 አዛውንቶች ብቻ ናቸው። ነገር ግን ህዝቡ በተጋነነው
የሚዲያ ወሬ panic ስላደረገ ልክ ፊልም ላይ እንደምናየው
ባለው ብር ሁሉ እህል እየገዛ ሱፐርማርኬቱን ባዶ አድርጎታል።
በግፊያው አካል ጉዳተኞችና አዛውንቶች እየተረጋገጡ ስለሆነ
ሱፐርማርኬቶቹ ተጨማሪ ሴኪዩሪቲዎች ለመቅጠር ተገድደዋል።
ምግብ ተርፎ በሚደፋባት ሃብታሟ አወስትራሊያ ባሁን ሰአት
ዘይት እንደሜርኩሪ እያደባደበ ነው። እግዚኦ አትሉልኝም ታዲያ?
በሽታው እጅ በመታጠብና ንክኪን በመቀነስ በቀላሉ የሚቆም
ቢሆንም የምእራባውያን ሚዲያ የቻይናን ኢኮኖሚ ለማንኮታኮት
ቻይና ላይ ኮሮና የተባለ መአት ወረደ ብለው አራገቡ። የቻይና
የንግድ እንቅስቃሴ በአንድ ቀን ወደቀ። ግዙፍ ካምፓኒዎቿ
ሰራተኛ በተኑ። ለአለም ገበያ ለማቅረብ ያመረተቻቸውን ምርቶች
መጣያ ስታጣ በመርከብ ወደቬትናም ወስዳ በርካሽ ጣለቻቸው!
አሁን የሆዷን በሆዷ ይዛ ነዋሪው ከቤቱ እንዳይወጣ በሩን
በመበየድ ጭምር አግሬሲቭሊ በሽታውን ተቆጣጠረችውና ኳሱን
መልሳ ወደአሜሪካና ወደአውሮፓውያኑ ጠለዘችው። እነአሜሪካ
ቻይናን ለማንኮታኮት ከሚገባው በላይ አጋንነው ያወሩለት ኮሮና
ወደራሳቸው back fire አደረገ! ይኸው ዛሬ በአመት 39 ሺ
ሰው በጉንፋን ብቻ የሚሞትባት አሜሪካ ህዝቧ ፓኒክ ስላረገባት
ብቻ ሳትወድ በግድ state of emergency ስታውጅ ቻይና
ፈገግ ብላ ታያታለች።
የአሜሪካና የቻይና trade war መጨረሻ ላይ የደረሰ
ይመስላል። ተንታኞቹ እንደሚሉት ከ 9/11 ጥቃት በኋላ ስቶክ
ማርኬቱ እንዳሁኑ ወድቆ አያውቅም። ኮንሲኩዌንሱ የኛን የሰፈር
ወንዝ ዳር ያለች ጀልባም ከአለት ጋር ማላተሙ አይቀርም።
ኦልሞስት ሁሉንም ነገሮች import እናደርጋለን። ከውጪ
የምናስገባው ከምርታችን ጋር በስልክም አይገናኝም። ( 3
billion ገደማ export እያረግን ለ import 11 billion
የምናወጣ ጉዶች ነን)
ቻይና በእርግጠኝነት በመጪው ጥቂት ቀናት ውስጥ ሪከቨር
አርጋ እንደመንግስቱ ሃይለማሪያም “ለምሳ ያሰቡንን ለቁርስ
አደረግናቸው” ብላ ወደሽቀላዋ መመለሷ አይቀርም።
አሁን ላደጉት ሐገራት በሽታው ሳይሆን ድንጋጤው ነው አስጊ
ደረጃ ላይ የደረሰው። ሰውን መቆጣጠር አቅቷቸዋል። ነጭ ለካ
እንዲህ ድንጉጥ ነው? እኛኮ ሴንትራል አፍሪካ ያ አስቀያሚ
ኢቦላ የተባለ በሽታ ሲከሰት እንዲህ አልቀወጥነውም። ነጮቹ
ግን ፍርሃታቸውን ማኔጅ ማድረግ አልቻሉም ነው የሚባለው። ለ
toilet paper ተናንቀው ሲደባደቡ ሁሉ አይተናል። ጣሊያን ሼባ
ስለሚበዛ ነው መሰለኝ በዛ ያለ ሰው ጭሮባታል። ሁለት
ጣሊያናውያን ኢትዮጵያ ለጉብኝት መጥተው መመለሻ ግዚያቸው
ሲደርስ “ተመልሰን አንሄድም” ማለታቸውን ስንሰማ «ቧ ግዜ
ለኩሉ» ብለናል!
እናማ ባሻዬ እንደነገርኩህ ነው ... ከአቅሙ በላይ የገዘፈው
ኮሮና እስካሁን 160 ሺ ሰዎችን ይዞ ስድስት ሺ ሰው ገድሏል።
ከ70 ሺ በላዩ ደግሞ ድነው ወደቤታቸው ሄዱ። ትናንት ቢቢሲ የ
104 አመት አዛውንት ከኮሮና አገገሙ ብሎ ፒፓውን ለማረጋጋት
ሞክሯል (“አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው” አለች ቢዮንሴ
)
እስካሁን አንድ ጥቁር ብቻ ነው የሞተው። (እሱም ሌላ ተጓዳኝ
በሽታ ነበረበት አሉ) ፈይሳ አዱኛ በኪነጥበቡ ጋርዶናል አባዬ።
ለማንኛውም ህዝቤ ሆይ ውሃ አይገድልም እጅህን ታጠብ።
እንደእቁብ ዳኛ ያገኘኸውን አትጨብጥ። ብትችል ባውቶቢስ
አትጠቀም (ዎክ እኮ ለጤናህም ጥሩ ነው) የኮሮና ሚመስል
ምልክት ካየህ ወደሰው ሳታስተላልፍ ሳትጨናነቅ ሃኪም ጋር
ደውል። ታክመህ ትድናለህ። በቀላሉ ለሚያገግም በሽታ
አምቡላንስ ሰብረህ የምታመልጠውኮ አለቅጥ አጋነው
ስላስደነበሩህ ነው። ንፅህናህን በመጠበቅና ቶሎ በመታከም
ሃላፊነትህን ተወጣ! ከዚህ ውጪ ግን አታካብድ! ከሰማይ
የወረደ መቅሰፍት አይደለም። ኮሮና በሽታም፣ ፖለቲካም፣
የኢኮኖሚ ጦርነትም፣ የሚዲያ ቢዝነስም ነው!
@wegoch
@wegoch
@wegoch