💐የእግዜር ልጓም💐
ክፍል 24
ተከታታይ ልብ-ወለድ
✍Aksan Adane
........... አንደኛው አጠገቤ ደርሶ በጥፊ ደረገመኝ እሺ የኛ ተዋናይ አንቺ ነሽ ጌታችንን ልታታይ ምትሞክሪው? አንቺ ትንኝ :: ፀጉሬን ጨምድዶ ያዘኝ ይታይሻል ይሄ ካሜራ አለኝ ከአናቴ በላይ የተደቀነ ካሜራ እያሳየ ሁሌም ቢሆን እይታ ውስጥ ነሽ ሰማሽ ?ፀጉሬን የያዘበት ህመም ብቻ ነው የተሰማኝ ለእኔ ዚያድ ከተኛበት ብድግ አለ ፀጉሬን ለቀቀኝና አንገቱን አነ ቀው ከተቀመጥኩበት ብድግ ስል ገፍትሮ ወረወረኝ ኑ ያዙአቸው እነዚህን ቆራርጦ መጣል ነው አላቸው ሁሉም እኛን ለመያዝ ተጣደፉ :: ሁሉም እጁን ሰነዘረብን :: እንደዚያ እየደበደቡን ገና ሳያገግም ከአሁን አሁን ዚያድን ገደሉት ብዬ ተሳቀኩ :: ከአፍንጫዬ ደም ይንቆረቆር ጀመር :: እንደ ውሻ መሬት ለመሬት እየጎተቱን የሆነ ጨለማ ክፍል አስገቡን እንደፈራሁትም ዚያድ ራሱን ስቷል ትንፋሹ ይሰማኛል ነገር ግን የእኔም ሰዉነት በመድቀቁ ልጠጋው አልቻልኩም አንዳች የብርሀን ጭላንጭል እንኳን የለም ዚያድ ብሎ መጣራት አማረኝ እንዴት አድርጌ ድምፅ ላውጣ :: በዚህ ሁሉ ውስጥ ዚያድ ሲነግረኝ የነበረዉን በአእምሮዬ እየሳልኩ እደሰት ጀመር ::
አንድ ዝማሬ ልክ በትልቅ ስፒከር ከውጪ እንደተከፈተ ሆኖ ይሰማኝ ነበር ::
"በከንቱ እንዳልለፋ ስለራራልኝ ስላዘነልኝ
" የህይወትን መንገድ አቅጣጫ አሳየኝ
"ያየኹትን መንገድ ይዤ እዘልቃለሁ
" እንደ ሄድኩም አልቀር ወደ እረፍቴ እገባለሁ :: የቤቲ ተዘራ ዝማሬ ነበር በራሷ ድምፅ በጆሮዬ ይንቆረቆር ነበር በዚያው ልክ በጀርባዬ እንደወደኩ እምባዬ በጆሮዎቼ እየ ወረደ ይንቆረቆር ጀመር ለረጅም ሰዓት በእንደዚህ ሁኔታ ነበርኩ አይኖቼ እንቅልፍ አሸነፋቸው ::ስነቃ ያስታወስኩት ነጭ በግ ሲያወራኝ እንደ ነበረ ነው :: ሰዉነቴ ላብ በላብ ሆኖ ነበር አፍንጫዬ በወረደው ደም ደርቆ ነበር ::ወደ ቀኝም ወደ ግራም መገላበጥ ተሳነኝ እንደ ቀደሙ የዚያድ ትንፋሽም አልሰማ አለኝ ይሄ ልጅ ሞተ እንዴ ?እንዴት ተጠግቼ ልየው ጨለማው በቃል አይገለፅም ::
💐💐
@wengelbeArt 💐💐
ከረጅም ሰዓታት በኋላ በሩ ሲከፈት ቀይ ብርሃን ቤቱን ሞተ ጨለማው በስንት ጣዕሙ አይኔ መቋቋም እስኪያቅተው አስቀያሚ ብርሃን ነበር :: የብዙ ሰዉ ኮቴ ነበር የተሰማኝ :: ወንበር ስበው አስቀመጡት አንገቴን ማንቀሳቀስ ስላቃተኝ ሚሆነውን በመስማት ነው እየተረዳሁ የነበረው :: እንዲያውም ዛሬ ሌሊት ለሚቀርበው መስዋዕት ብናውላቸው ባይ ነኝ ቅድም በጥፊ ያለኝ ሰውዬ ድምፅ ነበር ::
ተው ተው ወዳጄ ዞያር እነዚህ ርካች ለአምላካችን መስዋዕትነት ይመጥናሉ እያልክ ነው? የአቶ ዴቪድ ድምፅ ነበር ማመን አልቻልኩም :: አይደለም ወዳጄ እነዚህ ትናንሽ ትንኞች የአምላካችን ትልቅነት እስኪገባቸው እየቀጣን እናቆያቸው ::ከዚያም ጥሩ ሌሎችን ማራኪዎች እናደርጋቸዋለን ::
:-አቶ ዴቪድ ለአምላካችን አይመጥኑም ባልከው ብስማማም ጥሩ ማራኪ የሚለው ቃል ጎርብቶኛል እነዚህ ከሀዲዎች በምን ሂሳብ የአባታችን ትልቅነት ይገባቸዋል? ለድፍረታቸው እዚሁ ቆራርጬ ልተዋቸው እንጂ ::
ወዳጄ ዞያር አትቸኩል እኛም በግዜ ሂደት መስሎኝ እውነቱ የገባን በእኔ ጣላቸው ::
ክርክሩ ጦፈ ግሩፑ ለሁለት ተከፈለ ግማሾቹ ከአ ዴቪድ ጋር ግማሾቹ ከሰውየው ጋር ሆኑ ሰዉየው እሱ በበላይ አካል የሚወሰን ይሆናል እያለ ሄደ ሌሎችም ተከተሉት ::
አቶ ዴቪድ ሀሳቦን ተስማምቼ የቀረሁ ብሆንም ግን እንዳሉት ማድረግ እንችላለን? አንደኛዋ ጠየቀች::
:-እንችላለን ክሩዳ አላማችን ሁሉን አባል ማድረግ አይደለም? እዚህ ድረስ ከመጡ አባል ማድረግ ካቃተን እኛም ብንሞት አይሻለንም?
አዎ አዎ ሁሉም አጉረመረሙ በጣም ጥሩ አሉ አቶ ዴቪድ ::
ይሄ ሰዉዬ የምሩን ነው? እኛ በአንዴ የተያዝን እርሱ እንዴት እስከዛሬ ሊነቁበት ከይችሉም? የአሁኑ ሁኔታ እንኳን በቂ ነበር ለነገሩ መንፈስ ቅዱስ አሳውሮአቸው ነው :: እኔም ነገሩን ስለማውቀው ይሆናል እያልኩ ደግሞም በካሜራ መያዛችን ወይ ሰይጣን ተብዬ ሰዎች እኮ ሁለም ባይሆኑም ሁሉን ማድረግ ምትችል ይመስላቸዋል :: በእኔ ህይወት ግን እድል ፈንታ የለህም አልኩኝ በውስጤ ::
ወዲያው ቃሬዛ አምጥተው ወደ አንድ ክፍል ተወሰድን ::
ጥግና ጥግ ሁለት አልጋዎች ነበሩበት ግሉኮስ ተደረገልን :: አቶ ዲቪድ በአይናቸው ምልክት ሰጡኝ አንደኛዋ ይህንን ክስተት በመመልከቷ በክፉ አይን አየቻቸው ፊቷ ላይ የሚታይ አውሬ ነበር አይኖቿ ደም ለበሱ አቶ ዴቪድ ፊት ለፊቷ ቆመው ተፈጠጡ ለእኔ ራዕይ እስኪመስለኝ ከእርሷ ግንባር ላይ የምትወራጭ ትንሽዬ እባብ ከእርሳቸው ግንባር እንደ ነበልባል የሚንተከተክ እሳት ተመልከትኩ ወዲያው እሳቱ ተወንጭፎ አባቢቱን ገመድ አደረጋት ሴትየዋ ተዝለፍልፋ ወደቀች ::
ሌሎቹ ይሄ ክስተት የታያቸው አልመሰለኝም ተሸካክመው ይዘዋት ወጡ ..........
........ይቀጥላል.......
✍written by Aksan Adane
💐💐
@wengelbeArt 💐💐
💐💐
@wengelbeArt 💐💐