33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው እለት መካሄድ ጀምራል፡፡
(ነሀሴ 24/2016) ጉባኤው "ፍትሀዊና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል መካሄድ የጀመረ ሲሆን በጉባኤው ላይ ክቡር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ የኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስብሳቢ ፣ ክቡር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስተር ፣ የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታዎች ፣ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ፣ የዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች ፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊዎች ፣ ዶ/ር ዮሃንስ በንቲ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ፣ የትምርህት ባለድርሻ አካላት ፣ በየደረጃዉ የሚገኙ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ፣ መምህራን እንዲሁም የተማሪ ወላጆች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ለጉባኤው ተሳታፊዎች እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸውም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በተከናወኑ የተለያዩ ተግባራት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ምቹ የመማሪያ ማስተማሪያ አካባቢን በመፍጠር ትምህርት ቤቶችን ሳቢና ምቹ ለማድረግ በተሰሩ ስራዎች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን በመጥቀስ የተገኘው ስኬት ሀብትን ፣ ጉልበትን እና ቁርጠኝነትን አንድ ማድረግ ከተቻለ መስራት የምንፈልገውን ስራ ከማሳካት ወደ ሃላ የሚያደርግ ነገር እንደማይኖር ተናግረዋል፡፡