አጠቃላይ ትምህርት የምዘና ረቂቅ መመሪያ ዙሪያ በባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሄደ፡፡
(ጷጉሜ 1/2016 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የክፍለከተማ የሁለቱ ስርአተ ትምህርት አስተባባሪዎች፤ የትግበራ ቡድን መሪዎች እና የፈተና ባለሙያዎችን ጨምሮ ከተመረጡ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እንዲሁም የክፍለከተማና ክላስተር ሱፐርቫይዘሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ምዘና ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ረቂቅ መመሪያው በሁሉም የትምህርት እርከኖች የሚማሩ ተማሪዎችን በአግባቡ ለመመዘን እንዲቻል ታስቦ መዘጋጀቱን ጠቁመው ምዘናው የስርአተ ትምህርቱን ይዘት መሰረት አድርጎ የሚሰጥ እንደመሆኑ የተማሪዎቹ ለቀጣዩ የትምህርት እርከን በአግባቡ ዝግጁ እንዲሆኑ ታስቦ መመሪያው መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አያይዘውም ከውይይቱ ተሳታፊዎች የሚነሱ ሀሳቦችን እንደ ግብአት በመጠቀም መመሪያውን የማሻሻል ስራ እንደሚሰራ ገልጸው በቀጣይ ከቢሮው የማኔጅመንት እና የአጠቃላይ ካውንስል አባላት ጋር በረቂቅ መመሪያው ዙሪያ ውይይት ተካሂዶ መመሪያው ተግባራዊ እንዲሆን የሚሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በውይይቱ የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት የፈተና ዝግጅት አስተዳደር ቡድን መሪ ወይዘሪት መሰረት ኩማ የረቂቅ መመሪያውን ይዘት አቅርበው ተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን ለቀረቡ ጥያቄዎች መመሪያውን ባዘጋጁ አካላት ምላሽ ተሰቱዋል፡፡