የሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡
(መስከረም 6/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚኖረዉን ጠቀሜታ እና በቀላሉ በሰራተኞች ሊተገቡ የሚችሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ሰነድ በወ/ት ኤልሳቤት በዮራ በቢሮ የስፖርት ባለሙያ አማካኝነት ከቀረበ እና ሰራተኞች ቀላል የሚባሉ የስፖርት እንቅስቃሴዎችን በተግባር እንዲያሳዩ ተደረጋል፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነ ምግባርና ጸረ ሙሰና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አስራት ሽፈራው በተግባር የተገለጸ እና ብቁና ንቁ እንዲሁም ጤናማ ለመሆን የሚያግዝ እውቀት መሸመት የተቻለበት የዕውቀት ሽግግር መድረክ መሆኑን ገልጸዋል፡፡