የአጠቃላይ ትምህርት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
(ጥር 6/2017 ዓ.ም) የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ከተመረጡ የመንግስት አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች ለተውጣጡ ርዕሳነ መምህራን በጥናትና ምርምር ስራ አስፈላጊነትና አይነቶች ዙሪያ መሰጠቱን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥናትና ምርምር ቡድን መሪ አቶ መለሰ ዘለቀ በትምህርት ቤት ደረጃ በተለይም በመምህራን የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች በመማር ማስተማር ሂደቱ የሚስተዋሉ ችግሮች እንዲቀረፉ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በየተቋማቱ የሚገኙ ርዕሳነ መምህራን ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንዲችሉ በማሰብ ስልጠናው መዘጋጀቱን አመላክተዋል።
ቡድን መሪው አያይዘውም ርዕሳነ መምህራኑ በየትምህርትቤቱ የጥናትና ምርምር ስራዎች እንዲሰሩ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉና ለመምህራን ተመሳሳይ ስልጠና እንዲሰጡ ለማስቻል መርሀግብሩ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc