💛 የ መዝሙር ግáŒĨሞá‰Ŋ 💛


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


đŸ‡Ē🇹 የáŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ áŠĻርá‰ļá‹ļክáˆĩ ተዋሕá‹ļ ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን  አáˆĩተምህሮ ና áˆĩርአá‰ĩን የጠበቁ ቆየá‰ĩ á‹Ģሉና አá‹ŗዲáˆĩ👇👇
👏 የቸá‰Ĩቸá‰Ļ መዝሙáˆĢá‰ĩ đŸŽģ የበገና መዝሙáˆĢá‰ĩ  
👑 የቅዱáˆŗ መዝሙáˆĢá‰ĩ â›Ēī¸ የንግáˆĩ መዝሙáˆĢá‰ĩ
💍 የሠርግ መዝሙáˆĢá‰ĩ đŸŒĻ ወቅá‰ŗዊ መዝሙáˆĢá‰ĩ መገኛ

đŸ“ĸለ ማáˆĩá‰ŗወቂá‹Ģ áˆĩáˆĢዎá‰Ŋ @Miki_Mako

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


✞ á‹ĩንግል ሆይ ወደ áŠĨኔ á‰ĩመáŒĒ ዘንá‹ĩ ✞


ደንግል ሆይ ወደ áŠĨኔ á‰ĩመáŒĒ ዘንá‹ĩ
á‹ĩንግል ሆይ ወደ áŠĨኔ á‰ĩመáŒĒ ዘንá‹ĩ áŠĨንዴá‰ĩ ይሆናል
áŠĨመቤቴ ወደ áŠĨኔ á‰ĩመáŒĒ ዘንá‹ĩ áŠĨንዴá‰ĩ ይሆናል ደáŠĢማ ነኝ áŠĨኔ ምግá‰Ŗር ይጎá‹ĩለኛል (2x)
ወደ ተáˆĢáˆĢማው ይሁደ ከተማ
ፈáŒĨነáˆŊ áˆĩá‰ĩመáŒĒ á‹ĩምፅáˆŊ የተሰማ
የኤልáˆŗቤáŒĨ ዘመá‹ĩ የዘáŠĢርá‹Ģáˆĩ
á‹ĩምፅáˆŊን አሰሚኝ á‰Ŗንá‰ē ልቀደáˆĩ



በማኀፀንáˆŊ ይዘáˆŊ የሰማይ áŠĨንግደ
አንዴá‰ĩ á‰ĩመáŒĢለáˆŊ ከá‰ŗናáˆŊዋ ጓደ
አንዴá‰ĩ ልቀበልáˆŊ áŠĨምላáŠŦን ይዘáˆŊ
መንፈáˆĩ ቤቴን ሞላው ሲሰማ á‹ĩምፅáˆŊ
አዝ= = = = =
በáˆĨጋዊ áˆŗይሆን በመንፈáˆĩ ዓይኖá‰ŧ
ለማየá‰ĩ አáˆģለሁ ከልቤ ጓጉá‰ŧ
áˆĨáˆĢá‹Ŧ የከፋ መሆነን áŠĨውቀáˆĩሁ
á‹ĩምፅáˆŊን ለመáˆĩማá‰ĩ አጅግ አፈáˆĢለሁ
አዝ= = = = =
አንá‰ē ቡርክá‰ĩ ነáˆŊ ቡሩክ á‹Ģንá‰ē ፍáˆŦ
ላመንáˆŊዋ á‰Ĩፅዕá‰ĩ á‰ĩዘምር ከንፈáˆŦ
ፅንሰን ደáˆĩ አሰኘ የá‹ĩምፅáˆŊ ሰላምá‰ŗ
ለዚህ á‰ŗላቅ ነገር ይገá‰Ŗል አልልá‰ŗ
አዝ= = = = =
በሁሉ የሞላው ዙፋኑ á‰ĸá‹ĢደርግáˆŊ
የመላáŠĨክá‰ĩ መዝሙር ተሰማ ከሆá‹ĩáˆŊ
ሁáˆĩተኛ ሰማይ á‹ĩንግል ማርá‹Ģም
á‰Ŗንá‰ē á‹ĩንቅ አá‹ĩርጓል መá‹ĩኀኔዓለም

የአáŠĨላፋá‰ĩ ዝማáˆŦ መዝሙር
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ ══╯


✞áˆŗር ቅጠሉ ሰርá‹ļው✞

áˆŗር ቅጠሉ ሰርá‹ļው ሰንበሌáŒĨ ቄጤማው
በዚá‹Ģá‰Ŋ ቀን በዚá‹Ģá‰Ŋ ወር ለምልሞ የነበረው
በáŠĨልልá‰ŗ ዘመሩ በደáˆĩá‰ŗ ተሞልተው
ጌá‰ŗ መወለዱን የምáˆĩáˆĢá‰Ŋ ሰምተው


áŠĨልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌሉá‹Ģ
የፍቅር የሰላም ነáˆŊና ገበá‹Ģ(áĒ)


áŠĨረኝነá‰ĩ á‰ĩንáˆŊ የወáˆĢá‹ŗ ግá‰Ĩር
á‰Ĩሎ ሰው በልማá‹ĩ ደንግጎ ነበር
የá‰Ĩዙ ሰው áˆĢáˆĩ መሆኑን áŠĨረኛ
ክርáˆĩá‰ļáˆĩ ሲወለá‹ĩ ተረá‹ŗነው áŠĨኛ
አዝ= = = = =
የተነበዩለá‰ĩ ነá‰ĸá‹Ģá‰ĩ በሙሉ
ጌá‰ŗ ተወለደ የምáˆĨáˆĢá‰Ŋ በሉ
ሰውን በመውደዱ ሰማá‹Ģዊው ንጉáˆĨ
ይኸው ተወለደ áŠĨኛን ለመቀደáˆĩ
አዝ= = = = =
የሩቅ ምáˆĩáˆĢቅ ሰዎá‰Ŋ ሰá‰Ĩአ ሰገል ሰምተው
ሊሰግዱለá‰ĩ መጡ በኮከá‰Ĩ ተመርተው
ዕáŒŖንና ከርቤ ወርቁንም አመጡ
áŠĨንደየ áˆĩርአቱ áŠĨጅ መንáˆģ ሰጡ
አዝ= = = = =
áˆĩለተወለደ መá‹ĩኅን የáŠĨኛ ተáˆĩፋ
በደል ተወገደ ኃáŒĸአá‰ĩም ጠፋ

መዝሙር
ዲá‹Ģቆን መገርáˆŗ በቀለ

"አንá‰ēም ቤተ ልሔም ኤፍáˆĢá‰ŗ ሆይáĨ አንá‰ē በይሁá‹ŗ አáŠĨላፋá‰ĩ መáŠĢከል á‰ĩሆኚ ዘንá‹ĩ á‰ŗናáˆŊ ነáˆŊ፤ ከአንá‰ē ግን አወáŒŖጡ ከቀá‹ĩሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነáĨ በáŠĨáˆĩáˆĢኤልም ላይ ገá‹Ĩ የሚሆን ይወáŒŖልኛልáĸ"
ሚክ ፭áĨáĒ
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


✞ልቤ በáŠĨግዚአá‰Ĩሔር ጸና✞

ልቤ በáŠĨግዚአá‰Ĩሔር ጸና(áĒ)
አፌን አላቀኩኝ ለáˆĩሙ ምáˆĩጋና

በጠላá‰ļá‰ŧ ላይ አፌ ተከፈተ
ማá‹ŗኑን አይá‰ŧ ልቤ ተደሰተ
áŠĨንደ áŠĨግዚአá‰Ĩሔር á‹Ģለ ረá‹ŗá‰ĩ ማን አለ
ደáŠĢማ á‰Ŗርá‹Ģውን áˆĩለተቀበለ
አዝ= = = = =
ጠግበው የነበሩ áŠĨንጀáˆĢን ተáˆĢቡ
ተርበው የሚá‹Ģá‹ĩሊá‰ĩ áŠĨረኩ ጠገቡ
መá‰Ŋ ጎá‹ĩሎá‰Ĩኝ á‹Ģውቃል አንተን ተደግፌ
በáŠĨጆá‰Ŋህ በረከá‰ĩ ተሞልቷል መá‹ŗፌ
አዝ= = = = =
áŠĨግዚአá‰Ĩሔር ይገá‹ĩላል áŠĨንዲሁም á‹Ģá‹ĩናል
የኃይለኞá‰Ŋን ቀáˆĩá‰ĩ ሰá‰Ĩሎ ይá‰ŗደጋል
መáŠĢኒቱ ሃና ወለደá‰Ŋ ሰá‰Ŗá‰ĩ
áˆĨáˆĢህ ይደንቀኛል በቀን በሌሊá‰ĩ
አዝ= = = = =
ምáˆĩáŠĒኑን ከጉá‹ĩፍ á‹Ģነáˆŗል ከምá‹ĩር
ይዘረጋለá‰ŗል የክá‰Ĩርን ወንበር
ተመከረ ልቤ ሐናን ተመልክá‰ļ
áŠĨግዚአá‰Ĩሔር ለጋáˆĩ ነው ለጠበቀው ከá‰ļ
     
             መዝሙር
       ዲ/ን ወንá‹ĩወሰን በቀለ

"ሐናም áˆĩá‰ĩጸልይ áŠĨንዲህ አለá‰Ŋáĸ ልቤ በáŠĨግዚአá‰Ĩሔር ጸናáĨ ቀንዴ በáŠĨግዚአá‰Ĩሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላá‰ļá‰ŧ ላይ ተከፈተ፤"
      ፊáˆŗሙ áĒáĨፊ

╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


✞áŠĨግዚአá‰Ĩሔር ኃá‹Ģል ነው✞

áŠĨግዚአá‰Ĩሔር ኃá‹Ģል ነው የሚáˆŗነው የለም
በዙፋኑ ጸንá‰ļ ይኖáˆĢል ዘላለም
ማዕበሉን ከፍሎ ሕዝቡን á‹ĢáˆģግáˆĢል
ለሰው የሚáˆŗነው ለርሹ ግን ይá‰ģላል

ማá‹ŗንና áŒĨበá‰Ĩ ኃይል በáŠĨጁ ሆኖ
ለሰው የማይá‰ģል ለáŠĨሹ ቀሊል ሆኖ
ፈáŒĨኖ ይጎበኛል የምáˆĩáŠĒኑን ጓá‹ŗ
ፈáŒŊሞ አይዘገይም ጌá‰ŗ ሲሰናá‹ŗ
አዝ= = = = =
አንዱን áŠĨየáˆģረ አንዱን áŠĨየሾመ
የተዋረደውን ክá‰Ĩር áŠĨየሸለመ
ከኋላ á‹Ģለውን ከፊá‰ĩ አáˆŗልፎ
በጎ ቀን á‹ĢመáŒŖል ጨለማውን ገፎ
አዝ= = = = =
áŠĨንደ ቋáŒĨኝ á‰ĸከá‰Ĩá‹ĩ የሕይወá‰ĩ ፈተና
ሰውን የሚá‹ĢáŒŊናና አምላክ አለንና
ደáˆĩ á‹Ģሰኛል áŠĨርሹ መከáˆĢን አáŒĨፍá‰ļ
á‰ŗግáˆļ የቆመ ማን አፈረ ከá‰ļ
አዝ= = = = =
የሚá‹ĢáˆĩፈáˆĢ ጊዜ á‰ĸመáŒŖ ክፉ ቀን
áŠĨናልፋለን áŠĨኛ áŠĨግዚአá‰Ĩሔርን ይዘን
ወáˆĢá‰ĩ ከá‰Ĩá‹ļá‰Ŗá‰Ŋሁ á‹Ģጎነበáˆŗá‰Ŋሁ
á‰ŗáˆĒክ ሆኖ á‹Ģልፋል áŠĨግዚአá‰Ĩሔር ሲá‹Ģá‹Ģá‰Ŋሁ

       መዝሙር
ዲá‹Ģቆን ፍቃዱ አማረ

"áŠĨግዚአá‰Ĩሔርን አመáˆĩግኑ መዝሙር መልáŠĢም ነውና"
                መዝáģáĩ፯áĨፊ
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


✞ አáˆŗá‹ŗጊá‹Ŧ ✞

አáˆŗá‹ŗጊá‹Ŧ ማይልህ አንተ á‹Ģላáˆŗደግከው
ማን አለ ሚáŠĢኤል ከፍ á‹Ģላደረግከው
የሕይወቱ ነህ ከፍá‰ŗ ክá‰Ĩርና ማዕረጌ
አልረáˆŗም áˆĨáˆĢህን በቤá‰ĩህ አá‹ĩጌ

ከልጆቹ መሐል አንዷ ምáˆĩክር ነኝ
ሚáŠĢኤል አá‰Ŗቴ áŠĨርሹ áŠĨየጠበቀኝ
መጠበቅን á‹Ģውቃል መሰወር ከክፉ
አለው áŠĨየረá‹ŗኝ ከልሎኝ በክንፉ
መልáŠĢምን á‹Ģደርጋል ወá‹ŗጅ ለወá‹ŗጁ
á‹ĩንቅ አá‹ĩርጎልኛል ሚáŠĢኤል ለልጁ
አዝ= = = = =
ይሰምáˆĢል የልቤ ጠይቄው አላፍርም
áŠĨርሹ ከáŠĨኔ ጋር ነው á‰Ĩá‰ģá‹Ŧን አልቆምኩም
የá‰ĩላንá‰ĩ á‰ŗáˆĒáŠŦ መዝገቡ á‰ĸከፈá‰ĩ
በነገáˆŦ ሁሉ ሚáŠĢኤል አለበá‰ĩ
መልáŠĢምን ይደርጋል ወá‹ŗጅ ለወá‹ŗጅ
á‹ĩንቅ አá‹ĩርጎልኛል ሚáŠĢኤል ለልጁ
አዝ= = = = =
መገኛá‹Ŧ ደጁ ሌላ አá‹ĩáˆĢáˆģ የለኝ
የሚáŠĢኤል ልጅ ነኝ በፍቅሩ á‹Ģደኩኝ
በመላኩ ምልጃ አጊጧል ሕይወቴ
ለኔ á‹Ģላረገው ምን አለ አá‰Ŗቴ
መልáŠĢምን á‹Ģደርጋል ወá‹ŗጁ ለወá‹ŗጁ
á‹ĩንቅ አá‹ĩርጎልኛል ሚáŠĢኤል ለሌጁ
አዝ= = = = =
ከኔ አልተለየም ዛáˆŦም በሕይወá‰ĩ
አየዋለሁ ቀá‹ĩሞ ሁልጊዜ ከፊቴ
ይሄ ነው ምáˆĩáŒĸáˆŦ ወáŒĨá‰ļ የመግá‰Ŗቴ
ሚáŠĢኤል ይመáˆĩገኔን ኃá‹Ģሉ አá‰Ŗቴ
መልáŠĢም á‹Ģደርል ወá‹ŗጅ ለወá‹ŗጁ
á‹ĩንቅ አá‹ĩርጎልኛል ሚáŠĢኤል ለልጁ
አዝ= = = = =
መገኛá‹Ŧ ደጁ ሌላ አá‹ĩáˆĢáˆģ የለኝ
የሚáŠĢኤል ልጅ ነኝ በፍቅሩ á‹Ģደኩኝ
በመላኩ ምልጃ አጊጧል ሕይወá‰ĩቴ
ለኔ á‹Ģላደረገው ምን አለ አá‰Ŗቴ
መልáŠĢምን á‹Ģደርጋል ወá‹ŗጅ ለወá‹ŗጁ
á‹ĩንቅ አá‹ĩርጎልኛል ሚáŠĢኤል ለልጁ

መዝሙር
ዘማáˆĒá‰ĩ ሊዲá‹Ģ á‰ŗደሰ

╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ ══╯


​​​​አá‰Ŗ áˆŗሙኤል
ዘዋልá‹ĩá‰Ŗ


አá‰Ŗ áˆŗሙኤል ዘዋልá‹ĩá‰Ŗ
መነኮáˆĩ ሃá‹Ģል ቤቴ ግá‰Ŗ
á‰ŗáˆĩá‰ŖርáŠĢለህ ሰውን ምá‹ĩር
ቅርá‰Ĩ ነህ አንተ ለáŠĨግዚአá‰Ĩሔር

የበረሃው መናኝ ግሩም ነው ገá‹ĩልህ
ምá‹ĩርን አáˆĩá‰Ŗርከሃል ከፍ አá‹ĩርገህ በáŠĨጅህ
ተአምር ነው ገá‹ŗምህን ላየ
ረá‹ĩኤá‰ĩ በረከá‰ĩ ገበየ
ልጆá‰Ŋህ በገá‹ŗም ውáˆĩáŒĨ á‹Ģሉ
áˆŗሙኤል áˆŗሙኤል ይላሉ
አዝ = = = = =
አይáˆģገርá‰ĨáˆŊ áŠĨህልም ኃáŒĨአá‰ĩ
ጌá‰ŗá‰Ŋን á‰Ĩሏá‰ŗል ዋልá‹ĩá‰Ŗን መáˆŦá‰ĩ
ሕርመá‰ĩ ይዘው ልጆቹ በሙሉ
ቋርፍ ነው ዘውá‰ĩር የሚበሉ
የáŒŖመ የላመ አáŒĨተን
ዮርá‹ŗኖáˆĩ ፀበል ምግá‰Ĩ ሆነልን
አዝ = = = = =
አáˆĩáŠŦማውን ለá‰Ĩáˆļ በገá‹ŗም ሲኖር
የá‰ĩሕá‰ĩና አá‰Ŗá‰ĩ ነው የሕግ መምህር
ሃሌ ሉá‹Ģን ሄደን አይተን
አá‰Ĩረን áŠĢንተ áŠĨንኑር አልን (áĒ)

መዝሙር
ቀሲáˆĩ áŠĨንግá‹ŗወርቅ በቀለ


"በቤቴና በቅáŒĨáˆŦ ውáˆĩáŒĨ â€Ļâ€Ļ
የማይጠፋም የዘላለም áˆĩም áŠĨሰáŒŖቸዋለሁ"

áŠĸáˆŗ áļፎáĨ፭
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ ══╯


✞ ኑ በá‰Ĩርሃኑ ተመላለሱ ✞

ኑ በá‰Ĩርሃኑ ተመላለሱ (áĒ)
ኑ በá‰Ĩርሃኑ ተመላለሱ
የፍቅርን ሕይወá‰ĩ áŠĨንá‹ĩá‰ĩለá‰Ĩሹ
ኑ በá‰Ĩርሃኑ ተመላለሱ

ሁሉን በሚá‰Ŋል በአምላክ áŒĨላ
በáŠĨረፍá‰ĩ ውኃ áˆĩር አርፈናልና
ሰላምና ፍቅር ሕይወá‰ĩ በሚሰáŒĨ
ወደ ጌá‰ŗá‰Ŋን áŠĨንሂá‹ĩ áŠĨንሩáŒĨ
አዝ= = = = =
ምሕረá‰ĩና ፍርá‹ĩ በáŠĨጁ የá‹Ģዘው
የሰላም አá‰Ŗá‰ĩ መá‹ĩኅኔዓለም ነው
ሕይወá‰ĩ የሆነን በመáˆĩቀል ውሎ
á‰Ĩርሃንን ሰጠን ጨለማን áˆŊሎ
አዝ= = = = =
የሚá‹ĢáˆĩደነግáŒĨ የሚá‹Ģáˆĩጨንቀን
ይጠፋልና áŠĨርሱን ተማáŒŊነን
በቀን ከሚበር ፍላáŒģ ሁሉ
ይá‰ŗደገናል በቅዱáˆĩ ቃሉ
አዝ= = = = =
áŠĨግርህ በá‹ĩንጋይ áŠĨንá‹ŗይመá‰ŗ
በፈተና ውáˆĩáŒĨ áŠĨንá‹ĩá‰ĩበረá‰ŗ
መቅሠፍá‰ĩ ከቤá‰ĩህ áŠĨንዲከለከል
ይጠá‰Ĩቅሃል ሌሊá‰ĩና ቀን
አዝ= = = = =
áˆĩሙን á‹Ģወቀ ሕይወá‰ĩ መሆኑን
ይመላለáˆŗል ከኀይል ወደ ኀይል
ረጅም ዕá‹ĩሜ ይጠግá‰Ŗል áŠĨርሹ
á‰Ĩርሃን ይሆናል የጸጋ ልá‰Ĩሹ
አዝ= = = = =
አቤቱ አንተ ተáˆĩፋ ነህና
የምá‰ĩመግá‰Ĩ የፍቅር መና
ማá‹ŗንህ áŠĨኛን አáˆĩደáˆĩá‰ļናል
áŠĨንዲህ á‹Ģለ ክá‰Ĩር ከየá‰ĩ ይገኛል

መዝሙር
የአáŠĨላፋá‰ĩ ዝማáˆŦ
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
  @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


የሃገáˆĢá‰Ŋን የዩኒቨርáˆĩቲዎá‰Ŋ á‰ŗáˆĒክ ሲነáˆŗ አá‰Ĩሎ የሚነáˆŗው #ግá‰ĸ_ጉá‰Ŗኤ ነው

በáŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ የመጀመáˆĒá‹Ģው ዩኒቨርáˆĩቲ አዲáˆĩ አበá‰Ŗ ዩኒቨርáˆĩቲ ሲሆን ግá‰ĸ ጉá‰Ŗኤ የተጀመረውም በ6 áŠĒሎ áŠĢምፓáˆĩ ነውáĸ

áŠĨኛም በግá‰ĸ ጉá‰Ŗኤ á‰ŗáˆĒክ የመጀመáˆĒá‹Ģውን የአዲáˆĩ አበá‰Ŗ ዩኒቨርሲቲ የ6 áŠĒሎ ግá‰ĸ ጉá‰Ŗኤ የቴሌግáˆĢም á‰ģናል áŠĨነሆ á‰Ĩለናል👇👇
         @SidistKiloGibiGubae
         @SidistKiloGibiGubae
         @SidistKiloGibiGubae


Forward from: 💛 የ መዝሙር ግáŒĨሞá‰Ŋ 💛
"ልጄ ሆይ áˆĩሚ áŠĨá‹Ē ጆሮáˆŊንም አዘንá‰Ĩá‹Ē ወገንáˆŊን á‹Ģá‰Ŗá‰ĩáˆŊንም ቤá‰ĩ áŠĨርáˆē ንጉáˆĨ ውበá‰ĩáˆŊን ወá‹ĩá‹ļአልና áŠĨርሹ ጌá‰ŗáˆŊ ነውና"

               መዝ áĩ፭áĨ፲

    🎊 áŠĨንáŠŗን አደረáˆŗá‰Ŋሁ አደረሰን🎊
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯




✞ንáŒŊህተ ንጹሐን✞

ንáŒŊህተ ንጹሐን ከዊና ከመá‰ŗá‰Ļá‰ĩ ዘá‹ļር ዘሲና
ውáˆĩተ ቤተ መቅደáˆĩ ነበረá‰ĩ በá‹ĩንግልና ነበረá‰ĩ
ሲáˆŗá‹Ģ ህá‰Ĩáˆĩተ መና ወáˆĩቴ ሀኒ áˆĩቴ áŒŊሙና
     
áˆĩá‰ŗá‹ĩጊ በቤተመቅደáˆĩ
በቅዱáˆĩ áŠĨግዚአá‰Ĩሔር መንፈáˆĩ
አጊጠáˆŊ በá‰ĩህá‰ĩና
ተውበáˆŊ በቅá‹ĩáˆĩና

ምግá‰ĨáˆŊ የሰማይ መና
  ከምá‹ĩር አደለምና
  አáŠĢላዊው ቃል መርáŒĻáˆģል
  á‰ĩውልዱ á‰Ĩፅዕá‰ĩ ይሉáˆģል
አዝ= = = = =
መልዐኩ ፋኑኤል ወርá‹ļ
በክንፉ ለá‰Ĩá‰ģáˆŊ ጋርá‹ļ
መገበáˆŊ ህá‰Ĩáˆĩተ መና
አቅርá‰Ļ áˆĩግደá‰ĩ ምáˆĩጋና

ምግá‰ĨáˆŊ የሰማይ መና
  ከምá‹ĩር አደለምና
  አáŠĢላዊው ቃል መርáŒĻáˆģል
  á‰ĩውልዱ á‰Ĩፅዕá‰ĩ ይሉáˆģል
አዝ= = = = =
ሐርና ወርቁ ተáˆĩማምá‰ļ
አጌጠ በáŠĨጅáˆŊ ተሰርá‰ļ
በመቅደáˆĩ á‹Ģለው ማህሌá‰ĩ
አáˆĩረáˆŗáˆŊ የአá‰Ŗá‰ĩáˆŊን ቤá‰ĩ

ምግá‰ĨáˆŊ የሰማይ መና
  ከምá‹ĩር አደለምና
  አáŠĢላዊው ቃል መርáŒĻáˆģል
  á‰ĩውልዱ á‰Ĩፅዕá‰ĩ ይሉáˆģል
       አዝ= = = = =
በአምላክ ሕሊና á‰ŗáˆĩበáˆŊ
ከፍáŒĨረá‰ĩ ሁሉ ተመርጠáˆŊ
á‹ŗግሚá‰ĩ ሰማይ ሆነáˆģል
መለኮá‰ĩ በአንá‰ē አá‹ĩሎá‰Ĩáˆģል
 
ምግá‰ĨáˆŊ የሰማይ መና
  ከምá‹ĩር አደለምና
  አáŠĢላዊው ቃል መርáŒĻáˆģል
  á‰ĩውልዱ á‰Ĩፅዕá‰ĩ ይሉáˆģል

          መዝሙር
    ጸሐፌ á‰ĩዕዛዝ ዲá‹Ģቆን
        á‰ŗዴዎáˆĩ ግርማ

"áŠĨነሆምáĨ ከዛáˆŦ ጀምሮ á‰ĩውልá‹ĩ ሁሉ á‰Ĩፅዕá‰ĩ ይሉኛል፤"
            ሉቃ፩áĨáĩ፰
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


Forward from: የርáŠĨሰ ሊቃውንá‰ĩ አá‰Ŗ ገá‰Ĩረ áŠĒá‹ŗን ግርማ á‰ĩምህርá‰ļá‰Ŋ
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
መዝሙረ á‹ŗዊá‰ĩ áŠĨየጸለá‹Ģá‰Ŋሁ ማá‰ĨáˆĢáˆĒá‹Ģውን በርዕሰ ሊቃውንá‰ĩ አá‰Ŗ ገá‰Ĩረ áŠĒá‹ŗን ግርማ ተማሩ
የመዝሙረ á‹ŗዊá‰ĩ á‰ĩምህርቱን ለማግኘá‰ĩ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/abagebrekidan/4245




✞  ቸርነá‰ĩህ á‰Ĩዙ  ✞

ቸርነá‰ĩህ á‰Ĩዙ ምሕረá‰ĩህ á‰Ĩዙ
በጉዟá‰Ŋን áŠĨርá‹ŗን ጠá‰Ŗá‰Ĩ ነው መንገዱ
á‹ĩንቅ ነው አምላክ ሆይ ፍቅርህ ለáŠĨኛ
á‹ĩንቅ ነዉ ለáŠĨኛ አንተ ነህ መልáŠĢም áŠĨረኛ

አáˆĩáˆĢኤል ወደቀ áŠĨáˆĩáˆĢኤል ተነáˆŗ (áĒ)
መንገዱ አልቀናውም አምላኩን á‰ĸረáˆŗ(áĒ)
የá‹Ģዕቆá‰Ĩ አምላክ áŠĨግዚአá‰Ĩሔርን ይዞ(áĒ)
ምን áŠĨንá‹ŗተረፈ አውቆá‰ŗል በጉዞ (áĒ)
          አዝ= = = = =
መንገዱ አይá‰ŗክá‰ĩም ጎá‹ŗናዉ የቀና (áĒ)
áŠĨግዚአá‰Ĩሔር በፊá‰ĩም ከኋላሞ አለና (áĒ)
áŠĨርሹ በሌለበá‰ĩ á‰ĸመá‰Ŋም መንገዱ(áĒ)
አቅáŒŖáŒĢው ወደ ሞá‰ĩ አይቀርም መውሰዱ (áĒ)
          አዝ= = = = =
በመንገዱ ዝለን ወá‹ĩቀን መá‰Ŋ ቀርተናል (áĒ)
የá‹Ģዕቆá‰Ĩ አምላክ ደግፎ አንáˆĩá‰ļናል(áĒ)
áŠĨግዚአá‰Ĩሔር ሲጠáˆĢን በቀደመው መንገá‹ĩ (áĒ)
ጉዞአá‰Ŋን ወዴá‰ĩ ነው በሞá‰ĩ ለመወሰá‹ĩ (áĒ)
          አዝ= = = = =
አምላክ ሆይ ፍቅርህን በልá‰Ŗá‰Ŋን áˆŗለው (áĒ)
áŠĨáˆĩከሞá‰ĩ በመáˆĩቀል የወደደን ማነው (áĒ)
በበረሃዉ áŒŊናá‰ĩ ሲጸናá‰Ĩን ርሀቡ (áĒ)
በረከá‰ĩ ሞላኸን ተረፈልን ምግቡ(áĒ)

                መዝሙር
         በዘማáˆĒ አሸናፊ ተሾመ

╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


✞ áˆļበ ተዘከርናሃ ለáŒŊዮን ✞  

áˆļበ ተዘከርናሃ ለáŒŊዮን áˆļበ ተዘከርናሃ ለáŒŊዮን 
ውáˆĩተ አፍላገ á‰Ŗá‰ĸሎን  ህየ ነበርነ ወበከይነ
áŠĨንዚáˆĢቲነ ሰቀልነ ውáˆĩተ ጒዓቲሃ

á‰Ŗሰá‰Ĩናá‰ĩ ጊዜ áŒŊዮንን á‰Ŗሰá‰Ĩናá‰ĩ ጊዜ áŒŊዮንን
በá‰Ŗá‰ĸሎን ወንዞá‰Ŋ አጠገá‰Ĩ ተቀምጠን አለቀáˆĩን
መሰንቆዋá‰Ŋንን ሰቀልን በዛፎá‰ŋ ላይ

ፅኑ መከáˆĢን ተቀበልን ተጨነቅን በፈተና
የደዌ ሞá‰ĩ በላá‹Ģá‰Ŋን áŠĨንደዝናá‰Ĩ ወርá‹ļዋልና
አህዛá‰Ĩም ዘበቱá‰Ĩን áŠĨንዲ á‰Ĩለው በየተáˆĢ
ዘምሩለá‰ĩ ላምላáŠĢቹ á‰ĸá‹Ģá‹ĩናቹ ከመከáˆĢ

  áŠĨግዚአá‰Ĩሔር ፅዮንን በመንግáˆĩቱ መርጧá‰ŗል áŠĨና
  ማደáˆĒá‹Ģው á‰ĩሆነው ዘንá‹ĩ ወዷá‰ŗል áŠĨና
  ፅዮን ሆይ áŠĨናá‰ŗá‰Ŋን ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ á‹ĩንግል ማርá‹Ģም
  ፅዮን ሆይ áŠĨናá‰ŗá‰Ŋን ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ ቤተ ክርáˆĩቲá‹Ģን
  አንá‰ēን á‰Ĩንረáˆŗ ቀኛá‰Ŋን á‰ĩርáˆŗን
           አዝ= = = = =
የማረኩን በáŒĻáˆĢቸው በኃይላቸው የተመኩ
በáŒŊዮን ደጅ á‹Ģለፍርሃá‰ĩ የáŒŊዮንን ክá‰Ĩሯን ነኩ
ይህን á‹Ģየ ከላይ ሆኖ በደመና ተሸፍኖ
á‰Ŗá‰ĸሎንን አáˆģገረ የማረኩንን በá‰ĩኖ

  áŠĨግዚአá‰Ĩሔር ፅዮንን በመንግáˆĩቱ መርጧá‰ŗል áŠĨና
  ማደáˆĒá‹Ģው á‰ĩሆነው ዘንá‹ĩ ወዷá‰ŗል áŠĨና
  ፅዮን ሆይ áŠĨናá‰ŗá‰Ŋን ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ á‹ĩንግል ማርá‹Ģም
  ፅዮን ሆይ áŠĨናá‰ŗá‰Ŋን ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ ቤተ ክርáˆĩቲá‹Ģን
  አንá‰ēን á‰Ĩንረáˆŗ ቀኛá‰Ŋን á‰ĩርáˆŗን
           አዝ= = = = =
áˆĩጋá‰Ŋንን ሊገንዘን የሞá‰ĩ áŒĨላ á‰ĸá‹Ģጠላም
áŠĨናልፋለን ሁሉን á‰Ŗንá‰ē  የአምላክ áŠĨናá‰ĩ á‹ĩንግል ማርá‹Ģም
ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ ሆይ ከá‰ŖረክáˆŊን áŠĨንá‹ĩናለን ከደወዌá‹Ģá‰Ŋን
ለáˆĩጋና ለነá‰Ĩáˆŗá‰Ŋን መá‹ĩኃኒá‰ĩ ነáˆŊ áŠĨናá‰ŗá‰Ŋን

   áŠĨግዚአá‰Ĩሔር ፅዮንን በመንግáˆĩቱ መርጧá‰ŗል áŠĨና
   ማደáˆĒá‹Ģው á‰ĩሆነው ዘንá‹ĩ ወዷá‰ŗል áŠĨና
   ፅዮን ሆይ áŠĨናá‰ŗá‰Ŋን ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ á‹ĩንግል ማርá‹Ģም
   ፅዮን ሆይ áŠĨናá‰ŗá‰Ŋን ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ ቤተ ክርáˆĩቲá‹Ģን
    አንá‰ēን á‰Ĩንረáˆŗ ቀኛá‰Ŋን á‰ĩርáˆŗን

                    መዝሙር
ዘማáˆĒ መጋቤ ምáˆĨáŒĸር ሰሎሞን ተáˆĩፋá‹Ŧ

╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


ህá‹ŗር ፅዮን 21 áŠĨንáŠŗን አደረáˆŗá‰Ŋሁ

በዚህá‰Ŋ ቀን የáŠĨáˆĩáˆĢኤላውá‹Ģን መመáŠĒá‹Ģ በáŠĨመቤá‰ŗá‰Ŋን áˆĩም የተሰየመá‰Ŋው á‰ŗá‰Ļተ áŒŊዮን á‹ŗጐን በተá‰Ŗለው áŒŖáŠĻá‰ĩ ላይ ኃይሏን ክá‰Ĩሯን የገለጸá‰Ŋበá‰ĩ ቀን ነው፤ ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን áŒŊዮን ማርá‹Ģም áˆĩá‰ĩል ዕለቱን á‰ŗከá‰Ĩረዋለá‰Ŋáĸ


á‰ŗáˆĒክ

አክሱም áŒŊዮን áŠĨንደዛáˆŦው á‹ĩርቅ á‹Ģለ መáˆŦá‰ĩ አልነበረም á‰Ŗህር ነበር áŠĨንጂ ፤ አá‰Ĩርሃና አáŒŊá‰Ĩሃ ለá‰ŗá‰Ļተ áŒŊዮን ምን ዓይነá‰ĩ ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን ነው የምንሰáˆĢላá‰ĩ á‰Ļá‰ŗውáˆĩ የá‰ĩ ጋር ነው የሚሆነው áŠĨá‹Ģሉ ሲጨነቁ ጌá‰ŗá‰Ŋን ተገለጸላቸው á‹ĩንጋይ ላይ ቆሞም አዩá‰ĩ፤ ቤተክርáˆĩቲá‹Ģኗን áŠĨዚህ á‰Ŗህር ላይ áˆĩሊá‰ĩ áˆĩሟንም በáŠĨናቴ áˆĩም ሰይሟá‰ĩ፤ ይላቸዋል ጌá‰ŗ ሆይ ይህ áŠĨኮ á‰Ŗህር ነው ይሉá‰ŗል ቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤልን ከገነá‰ĩ አፈር ይዞ áŠĨንዲመáŒŖ á‹Ģደርገዋል á‰Ŗህሩ ላይ ነሰነሰው ደረቀ የዛáˆŦውንም ቅርáŒŊ á‹Ģዘ ይላል ጌá‰ŗá‰Ŋን የቆመበá‰ĩ የáŠĨግሩ ምልክá‰ĩ ዛáˆŦም á‹ĩረáˆĩ ይá‰ŗá‹Ģል ፤ ምንጭ á‹ĩርáˆŗነ áŒŊዮን፤ በá‹ĩንáŠŗን ቅርáŒŊ የተሰáˆĢው ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን ግርማዊ ቀá‹ŗማዊ አፄ ኃይለ áˆĨላሴ á‹Ģáˆŗነጹá‰ĩ ሴá‰ļá‰Ŋም ወንá‹ļá‰Ŋም የሚገቡበá‰ĩáĸ

በመሐል á‰ŗá‰Ļተ áŒŊዮን á‹Ģለá‰Ŋበá‰ĩ áŠĨቴጌ መነን á‹Ģáˆŗነጹá‰ĩ áˆĩመ áŒĨምቀá‰ŗ ወለተ ጊዮርጊáˆĩ በáˆĩሊ የáŒĨንቱ ቤተመቅደáˆĩ ፍርáˆĩáˆĢáˆŊ ይá‰ŗá‹Ģል በአáˆĢá‰ĩ መአዘን ቅርáŒŊ á‹Ģለው አፄ ፋሲለደáˆĩ á‹Ģáˆŗነጹá‰ĩ ሴá‰ļá‰Ŋ የማይገቡበá‰ĩ áŒĨንá‰ŗዊ ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን ነውáĸ

ፅዮን ማርá‹Ģም á‰Ŗልንበá‰ĩ ፀሎá‰ĩ ልመናá‰Ŋንን á‰ĩáˆĩማን


©ልá‰Ļና ቲዩá‰Ĩ


╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ ══╯




ጾም ሙáˆŊáˆĒá‰ĩን á‰ĩመáˆĩላለá‰Ŋ፤ ሙáˆŊáˆĒá‰ĩን በሠርግ አá‹ŗáˆĢáˆŊ ኾነው የሚቀበሏá‰ĩ ሰዎá‰Ŋ ቤቱን á‹Ģáˆĩጌጡá‰ŗል፤ ይሸልሙá‰ŗል፡፡

ወደ ሠርጉ አá‹ŗáˆĢáˆŊ የሚገá‰Ŗውን ሰው የሠርግ ልá‰Ĩáˆĩ ለá‰Ĩáˆļ áŠĨንደኾነáŖ የቆሸሸ áŠĨንá‹ŗልኾነ አይተው á‹Ģáˆĩገቡá‰ŗል፡፡

áŠĨኛም áŠĨንዲáŠŊ ልንኾን ይገá‰Ŗናል á‰Ĩá‹Ŧ áŠĨነግáˆĢá‰Ŋኋለኹ፡፡ ልቡናá‰Ŋንን በማንáŒģá‰ĩáŖ ልል ዘሊል ከመኾን በመáˆĢቅáŖ የክፋá‰ĩ áŠĨርሾን በማáˆĩወገá‹ĩáŖ ከጾም ጋር አá‰Ĩረው የሚመጡá‰ĩን የሚá‹Ģጅቧá‰ĩን መልáŠĢም ምግá‰ŖáˆĢá‰ĩንም ለመቀበል የልቡናá‰Ŋንን ውáˆŗጤ በመክፈá‰ĩ የምግá‰Ŗር áŠĨናá‰ĩáŖ የማáˆĩተዋል áŠĨንዲኹሉም ለሌሎá‰Ŋ ምግá‰ŖáˆĢá‰ĩ ኹሉ ንግáˆĨá‰ĩ የምá‰ĩኾን ጾምን ልንቀበላá‰ĩ ይገá‰Ŗናል á‰Ĩá‹Ŧ áŠĨነግáˆĢá‰Ŋኋለኹ፡፡

ይáŠŊን á‹Ģደረግን áŠĨንደኾነ á‰ŗላቅ ሐሴá‰ĩ áŠĨናደርጋለን፤ ርሷም ቁáˆĩለ ነፍáˆŗá‰Ŋንን á‰ĩፈውáˆĩልናለá‰Ŋ፡፡

ቅዱáˆĩ ዮሐንáˆĩ አፈወርቅ


áŠĨንáŠŗን ለጾመ ነá‰ĸá‹Ģá‰ĩ አደረáˆŗá‰Ŋሁáĸ በጾሙ በረከá‰ĩ ረá‹ĩኤá‰ĩ áŠĨንá‹ĩናገኝ áŠĨግዚአá‰Ĩሔር አምላáŠĢá‰Ŋን ይርá‹ŗንáĸ

╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ ══╯


ኅá‹ŗር ፎ ቊáˆĩቋም ማርá‹Ģም


áŠĨንáŠŗን ለáŠĨመቤá‰ŗá‰Ŋን ለቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ á‹ĩንግል ቊáˆĩቋም ማርá‹Ģም ዓመá‰ŗዊ ክá‰Ĩረ በዓሏ በሰላም አደረáˆŗá‰Ŋሁ áĸ

በዚህá‰Ŋ ቀን áŠĨመቤá‰ŗá‰Ŋን ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ á‹ĩንግል ማርá‹Ģም ከልጇ አንዲሁም ከዮሴፍና áˆļሎሜ ጋር 3 ዓመá‰ĩ ከ 6 ወር በáˆĩደá‰ĩ ከተንገላá‰ŗá‰Ŋ በኋላ ወደ አገáˆĢቸው የተመለሱበá‰ĩ ቀን ነው áĸ

ከግá‰ĨáŒŊ ሲመለሹ ጌá‰ŗá‰Ŋን በáŠĨመቤá‰ŗá‰Ŋን ጀረá‰Ŗ ላይ ሆኖ áŒŖá‰ļቹ ወደ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ይጠቁም á‹Ģመለክá‰ĩ ነበር፤ áŠĨመቤá‰ŗá‰Ŋንም ልጄ ሆይ ለምንá‹ĩነው áŒŖá‰ĩህን የምá‰ŗመለክተው á‰Ĩá‰ĩለው

"
á‹Ģá‰ē የተá‰Ŗረከá‰Ŋ አገር ናá‰ĩ áŠĨኔን የሚá‹Ģመልኩ አንá‰ēን የሚማልዱ በፍቅርáˆŊ የነደዱ ቅዱáˆŗን መነኮáˆŗá‰ĩ የሚፈልቁá‰Ŗá‰ĩ አገር áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ናá‰ĩ፤ በዚህá‰Ŋ አገር á‹Ģሉ áˆŗይዩኝ á‹Ģመኑኛል፤ አáˆĩáˆĢá‰ĩ በኩáˆĢá‰ĩáˆŊ á‰ĩሁን á‰Ĩሎ ሰáŒĨቷá‰ŗል፡፡
በáŠĒደተ áŠĨግáˆĢቸውም áŒŖና ሐይቅን ፤ ዋልá‹ĩá‰Ŗንና ሌሎá‰Ŋንም á‰Ļá‰ŗዎá‰Ŋ ዞረው áŠĨንደá‰Ŗረኩ á‹ĩርáˆŗነ ኡáˆĢኤልና ተአምረ ማርá‹Ģም ላይ በáˆĩፋá‰ĩ ተáŒŊፏል፡፡

ቸሩ መá‹ĩኃኔ ዓለም የá‹ĩንግል áŠĨናቱን áˆĩደá‰ĩ አáˆĩá‰Ļ ከመንግáˆĩተ ሰማá‹Ģá‰ĩ áˆĩደá‰ĩ ይሠውረን:: ከáˆĩደቱ በረከá‰ĩም á‹Ģá‹ĩለን::

©ልá‰Ļና ቲዩá‰Ĩ


╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ ══╯


‎
áŒĨቅምá‰ĩ ፲áŦ የአá‰Ŗá‰ŗá‰Ŋን አቡነ አረጋዊ የተሰወሩበá‰ĩ መá‰ŗሰá‰ĸá‹Ģ በዓል ነው


áŠĨንáŠŗን ለአá‰Ŗá‰ŗá‰Ŋን ለአቡነ አረጋዊ ዓመá‰ŗዊ በዓል በሠላም አደረáˆŗá‰Ŋሁ

ከአá‰Ŗá‰ŗá‰Ŋን ከአቡነ አረጋዊ በረከá‰ĩ ረá‹ĩኤá‰ĩ á‹Ģáˆŗá‰ĩፈን ከቅዱáˆĩ አá‰Ŗá‰ŗá‰Ŋን አቡነ አረጋዊ ከቅዱáˆĩ ሙáˆŊáˆĢው ገá‰Ĩረ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ ከቅዱáˆĩ ፊልáŒļáˆĩ በረከá‰ĩ ረá‹ĩኤá‰ĩ ይክፈለን ምልጃቸው አይለየን ወá‰ļ ከመቅረá‰ĩ áŠĢልá‰ŗሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውሩን አሜን በáŠĨውነá‰ĩ

╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ ══╯

20 last posts shown.

135 654

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel

✞  ቸርነá‰ĩህ á‰Ĩዙ  ✞ ቸርነá‰ĩህ á‰Ĩዙ ምሕረá‰ĩህ á‰Ĩዙ በጉዟá‰Ŋን áŠĨርá‹ŗን ጠá‰Ŗá‰Ĩ ነው መንገዱ á‹ĩንቅ ነው አምላክ ሆይ ፍቅርህ ለáŠĨኛ á‹ĩንቅ ነዉ ለáŠĨኛ አን...
✞ áˆļበ ተዘከርናሃ ለáŒŊዮን ✞   áˆļበ ተዘከርናሃ ለáŒŊዮን áˆļበ ተዘከርናሃ ለáŒŊዮን  ውáˆĩተ አፍላገ á‰Ŗá‰ĸሎን  ህየ ነበርነ ወበከይነ áŠĨንዚáˆĢቲነ ሰቀልነ ው...
📲áˆĩልኩን áˆĩá‰ĩነኩá‰ĩ የሚወáˆĩá‹ŗá‰Ŋሁ á‰ģናል ለህይወá‰ŗá‰Ŋሁ ጠቃሚ áˆĩለሆነ áˆĩልኩን  ይáŒĢኑ /Start 👇👇 ╭━━━━━━━╮ ┃   ● ══  â–Ēī¸Â Â Â Â Â Â  ┃█████...
ህá‹ŗር ፅዮን 21 áŠĨንáŠŗን አደረáˆŗá‰Ŋሁ በዚህá‰Ŋ ቀን የáŠĨáˆĩáˆĢኤላውá‹Ģን መመáŠĒá‹Ģ በáŠĨመቤá‰ŗá‰Ŋን áˆĩም የተሰየመá‰Ŋው á‰ŗá‰Ļተ áŒŊዮን á‹ŗጐን በተá‰Ŗለው áŒŖáŠĻá‰ĩ ላይ ኃይሏን ክ...
"ሁለá‰ĩ ክንፎá‰Ŋ" áŠĨጅግ á‹ĩንቅ á‰ĩምህርá‰ĩ በርዕሰ ሊቃውንá‰ĩ አá‰Ŗ ገá‰Ĩረ áŠĒá‹ŗን ግርማ https://youtube.com/watch?v=Mg12D2GkL44&si=I_4...