ጥቂት ነጥቦች ለሃብት ባለቤቶች
~
1- በቅድሚያ እጅህ ላይ ያለው ሃብት ባንተ ልፋት ብቻ የመጣ እንዳይመስልህ። በልፋትም ካንተ የበለጠ የሚለፉ፣ በእውቀትም ካንተ የሚበልጡ ሆነው ሳለ ሃብት የሌላቸው ብዙ ሰዎች ዙሪያህን እንዳሉ አትርሳ። እወቅ! ገንዘብህ የፈለገ ሰበብ ብታደርስ ከአላህ የመጣ ችሮታ ነው። ይህንን እውነታ ልብህ ውስጥ አርቀህ ትከለው። ይህንን እውነታ ካልተቀበልክ ካንተ ጋር መግባባት ከባድ ነው።
2- ሃብትህ ትእቢትና ኩራት አያውርስህ። ኩራትና ንቀት ብዙ ሃብታሞችን የሚያጠቃ በሽታ ነው። በኩራት የተለከፈ ሰው ምክር ይፀየፋል። እወቅ! "ልቡ ውስጥ የብናኝ ክብደት ታክል ኩራት ያለበት ሰው ጀነት አይገባም" ብለዋል ነብያችን ﷺ። [ሙስሊም፡ 91] ደግሞም ኩራት ለአኺራ ቀርቶ ለዱንያም አይጠቅምህም። የቸገረው ወይም የረከሰው ቢያሸረግድልህ እንኳ "እሱ ቀብራራ፣ ጢባራም ነው" እያለ ያወቀህ ይጠላሃል። የኣኺራው ደግሞ የከፋ ነው። ዱንያ ላይ አገር አይብቃኝ፣ መሬት አይንካኝ ያለው በጥራራ በቂያማ ቀን እንደ ጉንዳን አንሶ ሰዎች እየረጋገጡት፣ ከያቅጣጫው ውርደት አካቦት ጀሃነም ይወርዳል ብለዋል ነብያችን ﷺ። [ቲርሚዚይ: 2492]
3- ሃብትህ በየትኛውም ዘርፍ ድንበር አያሳልፍህ። ስትናገር አደብ ይኑርህ። በሰው ላይ አትተላለፍ። ስትራመድ አደብ ይኑርህ። ስለነጠርክ ተራራ አትደርስም። በየትኛውም ጉዳይ ላይ በሃብትህ መነሻ የተለየ ለመሆን አትጣር። ከሰው የተለየ ነገርም አትጠብቅ።
4- ዘካህን አውጣ። ዘካ ከኢስላም አምስቱ ምስሶዎች ውስጥ መሆኑን አትዘንጋ። እወቅ! ራስህን ብታስለምድ ደስ እያለህ በጉጉት ትሰጣለህ። ኢማንህ ይጨምራል። ኣኺራዊ ምንዳህ ደግሞ እጅግ የላቀ ነው። በተቃራኒው ግዴታ ከሆነበት በኋላ ዘካ የማይሰጥ ሰው ነገ የቂያማ ቀን የገዛ ገንዘቡ መሰቃያው ነው የሚሆነው።
5- አቅምህ እስከቻለ ድረስ በሌሎችም ኸይር ስራዎች ላይ ተሳተፍ። ከማንም በላይ የምታተርፈው ራስህ ነህ። ስለዚህ ችግረኛ ዘመድ፣ ጎረቤት፣ የዲን አስተማሪዎችን፣ ኢማሞችን፣ ሙአዚኖችን፣ ችግረኛ ወገኖችን፣ ... እርዳ። የምታውቀው ኸይር ስራ ላይ ለመሳተፍ ጎትጓች አትፈልግ። ወደ ጀነት ለሚደረግ ጥሪ ደስታ እንጂ ቅሬታ አትያዝ። ገንዘብህ ጠፊ፣ አንተም ሟች እንደሆንክ አትርሳ።
6- ገንዘብህ የልጆችህ መጥፊያ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። በወላጅ ገንዘብ ተበላሽተው ከመስጂድ የራቁ፣ በሱስ የደነዘዙ፣ አኺራቸው ቀርቶ ዱንያቸው አደጋ ላይ የወደቀባቸው ብዙ የሃብታም ልጆች አሉ። ስለዚህ ጥንቃቄ ይኑርህ።
7- ገንዘብህን አመጣጡንም አወጣጡንም ተከታተል። በሐራም እንዳይመጣ። በሐራምም እንዳይወጣ። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
" لَا تَزُولُ قَدَمَا عَبْدٍ يَوْمَ الْقِيَامَةِ حَتَّى يُسْأَلَ عَنْ عُمُرِهِ فِيمَا أَفْنَاهُ، وَعَنْ عِلْمِهِ فِيمَ فَعَلَ، وَعَنْ مَالِهِ مِنْ أَيْنَ اكْتَسَبَهُ وَفِيمَ أَنْفَقَهُ، وَعَنْ جِسْمِهِ فِيمَ أَبْلَاهُ"
"በቂያማ ቀን የትኛውም ባሪያ አራት ነገሮችን እስከሚጠየቅ ድረስ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንደቋጨው፣ እውቀቱን ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና በምን ላይ እንዳዋለው እና አካሉን በምን እንደፈጀው።" [ቲርሚዚይ: 2417]
8- የዱንያ ወከባ አኺራን አያስረሳህ። ከመስጂድ አትራቅ። ዝምድናህን ቀጥል። ሐጅ ካላደረግክ ዛሬ ነገ ሳትል ባስቸኳይ ፈፅም። ባጭሩ እጅህ ላይ ያለው ሃብት ካወቅክበት የአኺራህን ቤት የምትገነባበት ነው። ካልሆነ ግን ዘላለማዊ ህይወትህን የምታበላሽበት ነው። የሚሻልህን መምረጥ ያንተ ድርሻ ነው። የቂንህ አይድከም፣ አኺራህን ምረጥ። ሰላም ላንተ ይሁን።
@yasin_nuru @yasin_nuru