🔰ነቢዩ ﷺ ነቢይ ሆነው ከመላካቸው በፊት ትክክለኛው መንገድ ላይ ነበሩ።?🔰
➸ነቢዩ ﷺ ነቢይ ሆነው ከመላካቸው በፊት በአላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ጥበቃ አንድም ቀን ለጣዖትም አምልኮ ሰጥተው፣አስካሪ መጠጥ ጠጥተው፣ዝሙት ሰርተው አያውቁም።በወጣትነት ዘመናቸውም ማንኛውም ወጣት
ከሚወድቅባቸው ልዩ ልዩ ፀያፍና ክህደት ነገሮች ጥበቃ አድርጎላቸዋል። አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ እንደዚህ አይነት ፀያፍ ወንጀሎች ነቢዩ ሰላሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘንድ የተጠሉ ነገሮች እንዲሆኑ አደረገላቸው። በህዝቦቻቸው ሃይማኖት ላይም አልነበሩም።
📚 መጅሙዑል ፈታዋ ቅጽ 13 ገፅ 501
📚 ተፍሲሩል ቁርጡቢይ 18 ገፅ 513
📚 ሶሂህ ኢብኑ ሒባን 49
ነቢዩ ﷺ በነቢዩላሂ ኢብራሂም ዓለይሂ ሰላም መንገድ ላይ ነበሩ።
(ነቢዩላሂ አብራሂም ደግሞ👇
ما كَانَ إِبْرَاهِيمُ يَهُودِيًّا وَلَا نَصْرَانِيًّا وَلَـٰكِن كَانَ حَنِيفًا مُّسْلِمًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ
📚 (ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 67)
ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም፡፡ ግን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበረ፡፡ ከአጋሪዎችም አልነበረም፡፡
ነቢዩ ﷺ ከሸይጣን ጉትጎታና ትንኮሳ ፍፁም የተጠበቁ በማድረግ እና
የውስጣቸውንም ጤንነት በመጠበቅ በጂብሪል አማካኝነት
ሁለት ግዜ ከልባቸው የረጋ ደም አይነት ነገር በማውጣት ይሄ የሸይጣን ድርሻ ነው በማለት ልባቸውን አጥቦላቸዋል። በንዲህ አይነት ጥበቃዎች በእነዚህ መልኩ ለነቢይነት ዝግጁ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።
ነቢዩ ﷺ ዕድሜያቸው ወደ አርባ ዓመት በተጠጋ ጊዜ ሕዝባቸው የሚገኙበት ተጨባጭ ሁኔታና ዕምነት መረጋጋት ነስቷቸው ብቸኝነትን
እየወደዱ መጡ። የበሶ እና የውኃ ስንቅ በመያዝ ከመካ ሁለት ማይል ያህል ርቀት በመጓዝ ወደ ሒራ ዋሻ
ይጓዙ ጀመር።
ወደሳቸው የወረደላቸው መመሪያ ህግጋት ባይኖራቸውም በዚያም በነቢዩላሂ ኢብራሂም መንገድ ላይ ሆነው አምላካቸውን አላህን በብቸኝነት
በመገዛት ያሳልፉ ነበር፤
📚 ፈትሁል ባሪ ሸርህ ሶሂህ አልቡኻሪይ ቅጽ 1 ገፅ 54
ይህ የነቢዩ ﷺ ብቸኝነት መምረጥ ለሚጠብቃቸው ታላቅ
ጉዳይና ከባድ አደራ የመቀበል ከአላህ ዘንድ የተቸራቸው ቅድመ ዝግጅት
አንድ አካል ነበር።
ነቢዩ ﷺ ዕድሜያቸው አርባ ዓመት በሞላ ጊዜ አላህ ለዓለማት
አብሳሪና አስጠንቃቂ ይሆኑ ዘንድ ላካቸው፤ ጂብሪልም (ዐ.ሰ) ከዓለማት
ጌታ መልዕክት ይዞ.እሳቸው ዘንድ ወደ ሒራ ዋሻ በመምጣት
“አንብብ”
አላቸው፤ እሳቸውም ﷺ ማንበብ አልችልም” አሉት። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦ “ያዘኝና እስከሚጨንቀኝ ድረስ ጨመቀኝ፤ ከዚያም
ለቀቀኝና “አንብብ” አለኝ፤ እኔም “ማንበብ አልችልም” አልኩት፤
በሦስተኛውም እንዲህ አለኝ፦ “አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ
ስም። ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)። አንብብ፤ ጌታህ በጣም
ቸር ሲሆን፤ ያ በብዕር ያስተማረ፤ ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲሆን።
”አል ቀለም (1-5)፣
📚ሀዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል።
ከዚያ በኃላ ወህይ(ራዕይ) በጂብሪል አማካኝነት ወደ ነቢዩ ﷺ ለ 23 አመታት ወረደ።
ስለዚህ ነቢዩ ﷺ በነቢዩላሂ ኢብራሂም ዓለይሂ ሰላም መንገድ ላይ ሆነው አላህን በብቸኝነት ያመልኩ ነበር እንጂ ጣዖታትን አምልከው በፍፁም አያውቁም።
➸ እንደውም በጥቅሉ ሁሉም ነቢያት ነቢይ ሆነው ከመላካቸው በፊት አማኞች ነበሩ።
📚 ተፍሲር አያት አሽከለት ሊብኑ ተይሚያህ ገፅ 181
ስለዚህ ካፊሮች ነቢዩ ﷺ ሙሽሪክ ነበሩ ብለው የሚያወሩት ቅጥፈት ነው።
አላህ እንዲህ ይላል
*¶በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»*
{📗 Qur'an17:81}
ከላይ የጠቀሰኳቸውን ማስረጃዎች ከኪታብ በማስረጃ ከፈለጉ ይህንን ይጫኑ👇👇
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
አላሁመ ሶሊ ዓላ ነቢዪና ሙሐመድ
➤➤አልሃምዱሊላህ ረቢል ዐለሚን➤➤

https://t.me/iwnetlehullu1/413?single
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
አላሁመ ሶሊ ዓላ ነቢዪና ሙሐመድ
➤➤አልሃምዱሊላህ ረቢል ዐለሚን➤➤