💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
የታሪኩ ርዕስ
💁♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
#ክፍል ☞ አስራ አንድ 1⃣1⃣
✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን
ሚኒስትሪ ልንፈተን 2 ወራት ብቻ ቀርተውናል።ከድሬ ሳናግረው ይሸሸኛል። ያቺን የለመድኳት ፍቅሬን የምታሳየኝ ፖልም ብቻዋን ተገትራ ነው የማገኛት። አንዳንዴም እኔ በተራዬ ድንገት ከመጣ ብዬ ፖሉን ተደግፌ እቆማለው። እየሩስ ይሄ ተግባሬ ያናድዳታል ። ወንድ ልጅ ኮራ ስትይበት ነው የሚወደው ትለኛለች። አብረን እንድንተኛ እንደጠየቀኝ ግን አልነገርኳትም። ናፍቆቱ ሲበረታብኝ አላስችል ብሎኝ ነገርኳት።
.....እዩ መፍትሄ ብዙ ናት ምክንያት ሰበብ እና ዘዴ አታጣም።ሁል ጊዜ እስዋ ጋር የችግር ቁልፍ አለ። አሁን ግን ለኔ ምንም ልታገኝልኝ አልቻለችም።ገና በዚ እድሜሽ ሴክስ ከጀመርሽ መጨረሻሽ ሴተኛ አዳሪ ነው የምትሆኚው እውነት የሚያፈቅርሽ ከሆነ በራሱ ጊዜ ይታረቅሻል የማያፈቅርሽ ከሆነ ግን ብትርቂው ነው የሚሻልሽ ለስሜቴ ነው ማለት ነው ሚፈልግሽ ብላ ተስፍ አስቆረጠችኝ።
.....ያፈቀረ እና ያበደ አንድ ነው አይደል የሚባለው ንግግርዋን ከምንም አልቆጠርኩትም ። እንደተለመደው ከትምርህት ቤት ወጥተን ወደ መድረሳ ስሄድ ከድሬ ፖሉን ተደግፎ ቆሞ ጠበቀኝ። ሳላቅማማ ወደርሱ አመራሁ። ናፍቀከኛል ለምን ጠፋህብኝ?? ስልክስ ለምንድነው የማታነሳው ??በተለያየ ስልክ ደውዬልሀለው ግን አታነሳም አልኩት።
.....እሱም ንግግሬን ካዳመጠ በኋላ ወደ ገደለዉ እንግባ የጠየኩሽን ምን ወሰንሽ ??አለኝ
.......ማለት አልገባኝም ??አልኩት
.......ባለፈዉ የጠየኩሽን ፍቃደኛ ነሽ አይደለሽም ???ብሎ ጠየቀኝ
......ምንም የተለወጠ ነገር እንደሌለ በባለፈዉ አቋሜ እንደሆንኩ ነገርኩት።
....ከድር ጥሎኝ ወደቤቱ ገባ። እዛው ፖሉ ጋር ሆኜ አነባሁ።ያየኝ ሁሉ ሰዉ ምን ሆንሽ ልጄ የምታለቅሽዉ?? እያለ ይጠይቁኛል።
....እየሩስም እንባዬን ጠራርጋ ተነሽ በቃ ዛሬ መድረሳ ይቅርብሽ ወደቤት እንሂድ በጌታ እያለች ለመነችኝ
......ግን አይሆንም አላህ ፊት ቆሜ ማንባት ነው የምፈልገው ሂጅልኝ ብዬ ትቻት ወደ መድረሳ ሄድኩ። ግን አላህ ያለው መድረሳ ብቻ ነው እንዴ? አይ ልጅነት ይገርማል ንግግር እንኳን አናውቅም።
መድረሳ ሄጄ ቁርዐኔን ከፍቼ እየቀራሁ አነባሁ።እንባዬ ቁርዐኔን አርሶ አበላሸብኝ።
......ኡስታዛም ምን ነክቶሽ ነው አይዞሽ እያለች አባበለችኝ። የሆንኩትን ለማንም ሳልናገር ወደ ቤቴ ሄድኩ። ከዛም መግሪብ ከሰገድኩ በኋላ እራቴን ሳልበላ መስገጃዬ ላይ ቁጭ ብዬ የሙሀመድ አወል ሳላህን መስገጃሽ ላይ ታገሺ የሚለውን ነሺዳ እየሰማሁ እያነባሁ እንባዬንም እየጠረኩ ኢሻ እስኪያዝን ጠበኩ። ኢሻም አዛን ካለ በኋላ ሰላቴን ሰግጄ ዱአ አደረኩ። ከዛም አላህዬ ከድር የወደፊት አጋሬ ነው አይደለም? ለኔ ሀላሌ ነው አላህዬ? አሁን ምንም ብናደርግ ችግር የለውም? አላህዬ አሳውቀኝ እያልኩ አፍ እንዳልፈታ ህፃን ልጅ እየተንተባተብኩ ዱአዬን ጨርሼ ሰላተል እስቲሀራ ሰግጄ ስለከድሬ የሆነ ነገር እንዲያሳየኝ ለምኜ ተኛሁ።
ግን አላህ ምንም ያሳየኝ ነገር አልነበረም። በማግስቱም ሱብሂ ከሰገድኩ በኋላ አልፎም አላህዬ እሺ ከድር ለኔ የማይሆን ከሆነ ከልቤ አውጣልኝ ከዚህ ስሜት አስወጣኝ ብዬ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ። ያለወትሮዬ ሰላቴን በሰአቱ መስገድ ጀመርኩ በዱአም በረታሁ። ባላሰብኩት ፍጥነት ከከድር መራቅ እንዳለብኝ ልቤ ተሰማው። ከዛሬ ጀምሮ ከድሬን ላለማናገር እና በፍቅር ላለማሰብ ወሰንኩ ።ከዛም ቀን ጀምሮ ፖሉን ተደግፎ ቆሞ ሲጠብቀኝ ባይም ባላየ ማለፍ ጀመርኩ። አልፎ ሲናፍቀኝ አይኔን አጣምሜ ሰርቄ አየዋለው ግን አላናግረውም።
የሚኒስትሪ ፈተና ከወሰድን አንድ ወር አለፈን። የሚኒስትሪ ውጤት ተለቀቀ የሚል የሀሰት ወሬ ብዙ ጊዜ ይሰራጭ ስለነበር በሰማን ቁጥር ለማረጋገጥ እኔና እዩ ትምህርት ቤት እንሄድ ነበር። አንድ ቀንም ይሄንን የሀሰት ወሬ ሰምተን ለማረጋገጥ ስንሄድ ከድሬን አገኘሁት።
.....ዘይባ ዘይባ እያለ ጠራኝ። አላስችል ብሎኝ ላናግውረ ወደርሱ ሄድኩ።
....ጠፋሽ ምን ሆነሽ ነው?? ናፈቅሽኝ እኮ ለምን አትደውይም?? እያለ ጥያቄ አዘነበብኝ።
.....ያን ሁሉ ያሳለፍኩትን መከራ ረስቼ ስልክ ስላላገኘሁ ነው ካሁን በኋላ እደውልሀለው አልኩት።
አሁንም ጥያቄውን ቀጠለ። ከኔጋ የጠየኩሽን ለመፈፀም ዝግጁ ሆንሽ ? ብሎ የረሳሁትን ጥያቄ ድጋሚ ጠየቀኝ።
..... የማውቀውን እና ይገባዋል ያልኩትን ስድብ በሙሉ ሰደብኩት ለሱ ያለኝ ስሜት ከዛን ቀን ጀምሮ ሞተ።ለማግባት ዝግጁ እስካልሆንኩ ድረስ ከወንድ ጋር የሀራም ግንኙነት ላልጀምር በአላህ ቃል ቁርአን መትቼ ማልኩ
Part 1️⃣2️⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል
🔻ክፍል 1️⃣2️⃣ ከ6️⃣0️⃣ 👍 በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍😀 ማድረግ አይርሱ
የፍቅር ቴሌግራም ቻናል
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!