🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ጥቁር ልብ❤️
ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ 💟
ክፍል 8️⃣
ከሷ ማርገዝ በላይ ትልቁ አሳሳቢ ጉዳይ የእህል መሰብሰቢያ ወቅት እስኪደርስ ድረስ አርሰን ምንበላው በራሱ አለመኖሩ ነው።
እንዳረገዘችም ያወቅነው ቢያንስ አራት ወሯ ላይ ነበር።
አጨዳ የለ እርሻ የለ ተጨነቅን እኔ መልሼ መነገድ ጀመርኩ ባለቤቴ እኔ በሌለሁበት አዲስ አበባ መጥታ ሰው ቤት ገባች ሰውነቷ ሞላ ያለ ስለነበር ጭራሽ እርጉዝ እንደሆነች አታስታውቅም ነበር በወር 14 ብር ተቀጥራ ገባች ።
እኔ ከንግዱ ቦታ ስመለስ መሬት ብገባ ሰማይ ብወጣ ድራሿ ጠፋብኝ።
ከመሄዷ በፊት ግን ለእመቤት ነግራት ስለነበር እሷ የተፈጠረውን አጫወተችኝ ከዛሬ ነገ ትመጣለች እያልኩ ጠበኳት እንደቀልድ ሁለት ወር ሆናት ስልክ የለ አንደዋወል ።
ብቻ ከሁለት ወር ቡሀላ አለቃዋ አወቀችባት በዛ እድሜዋ ማርገዟ አስደንግጧት ከደሞዟ ላይ ሁለት ብር ጨምራ ሰላሳ ብር ሰጥታ ሸኘቻት።
ተመልሳ ወደገጠር መጣች ደስ አለኝ በሰራቸው ገንዘብ ለተወሰነ ጊዜ የሚያቆየንን ምግብ ሸማምታ ነበር ።
እሷ ለመውለድ እየተቃረበች እንደዛ ምታደርጋት እናቷ ታማ ሚያስታምማት አጥታ አልጋ ስር ሞታ ተገኘች ።
እናቷን ቀበረች። በዳይ ከመሬት በታች ተበዳይ ከመሬት በላይ ሆኑ።
እናቷ ከሞተች ቡሀላ መሬቱም ሚታረስበት ወቅት ነበር።
መሬቱ ሲገኝ እኛ ግን ምናርስበት በሬና ምንዘራው እህል እራሱ አልነበርንም አጎቴ እግር ላይ ወደኩና እባክህን ሰው እንድሆን አግዘኝ ከብቶችህን አበድረኝ አልኩት ምን ቸግሮኝ አንተ ምታርሰው ካገኘህ አለኝ አረስኩኝ ከዛ ደሞ እህሉ እስኪደርስ ሌላ መከራ።
በድጋሜ
ስትወልድ የምትበላው ይቸግራታል ብዬ ለመነገድ እራቅ ወዳለ አገር ሄድኩኝ።
(ሁሌም ቢሆን ከኛ ሀገር እራቅ ወዳለ ቦታ ሄደን ነው ምንሸምተው)
እኔ እንደሄድኩኝ ባለቤቴ ለካ ባዶ ቤት ሞትሽ ወይ ዳንሽ ወይ የሚላት ሰው በሌለበት ሀምሌ 22 ከቀኑ ሰባት ሰአት አካባቢ ሳያማት ድንገት ምጧ ይመጣል
ወገቧን ቆረጥ ሲያደርጋት መደብ ላይ ጠጋ ትልና አረፍ ትላለች አረፍ ባለችበት ቅፅበት ልጁ ከሆዷ ለመውጣት ያጣድፋታል መቼስ ፈጣሪ ደግ አደል አንዲት ሴትዮ በኛ ቤት ጀርባ እያለፈች ወይኔ ብላ ስትጮህ ትሰማትና እሮጣ ትገባለች።
ስታያት ምጧ መጥቷል ሴትዮዋ ወደቤት በገባችበት ቅፅበት ባለቤቴ ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ ዱብ ታደርጋለች የዛኔ እሷ 15 አመቷ ነበር።
ሴትዮዋም ከእግዚአብሔር ነውና የተላከችው የልጁን እትብት ቆርጣ ደሙን ጠርጋ መሬት ላይ ጨርቅ ደልድላ አንጥፋ ታስተኛትና ሰው ትጠራለች ።
በዛን ሰአት እመቤት ነበረች አብራት ያደረችው ።
ያላትን ከልጆቿ አፍ እየገመሰች አምጥታ እህል ያቀመሰቻትም እሷ ነበረች።
አጎቶቿ ዘመዶቿ ሞልተው በፈሰሱበት ሀገር ላይ አንዴ እናቷ ስትንቃትና ጎዳና ለጎዳና ስትንከራተት ስላዩ ብቻ ናቋት አንቋሸሿት ልጅ ነው ወይስ አውሬ የወለድሽው እንይልሽ ሳይሏት ቀሩ። በአራተኛው ቀን ሀገር አማን ብዬ ወደ ቤቴ ስመለስ ባለቤቴ ወልዳ ባዶ ቤት ተኝታ አገኘኋት።
አጎቴጋ ሄድኩኝ ባለቤቱን ሚስቴ እንደወለደችና ለአራስ የሚሆነኝነ ምግብ እንድታዘጋጅልኝ ለመንኳት በልውጫው እኔ ሸምቼ ከመጣሁት እህል እንደምሰጣት ነገርኳች እሺ አለችኝ።
በአጋጣሚ በነጋታው ደሞ የእመቤት ሴት ልጅ ታገባ ነበርና እሷጋ ሰርግ ቤት ሄድኩኝ ቀድሜ ምግብ ቋጥሬ ለባለቤቴ አምጥቼ ከሰጠኋት ቡሀላ እየተጣደፍኩ አራሷን ሚስቴን ትቼ ወደ ሰርጉጋ ሄድኩኝ እዛው ስጠጣ ሳስተናግድ ከሰዎችጋ ስሳሳቅ ጊዜ ምስኪኗን ሚስቴን እረሳኋት እዛው ሰክሬ ባዶ ቤት ትቻት አደርኩ ።
ስተቴ ሚጀምረው ከዛን ሌሊት አንስቶ ነው። ያደርኩት ከሌላ ሴትጋ ነበር ።
በነጋታው ከስካሬ ስነቃ ባለቤቴና ልጄ ትዝ አሉኝ እየተጣደፍኩ ወደ ጎጇችን አመራሁ።
አየኋት በአራስነቷ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች አገኘኋት ለልጁ ምታጠባው ጡት እራሱ ደርቆ ነበር።
ገና እንደገባሁ እየተንሰቀሰቀች ማታ በሌሊት ውሀ ጠምቷት እንደምንም ተነስታ ግቢ ውስጥ መሬት ላይ ከተጠራቀመው የዝናብ ውሀ ቀድታ እንደጠጣች ነገረችኝ።
ሳስበው ዘገነነኝ በር በሌለው ቤት መብራት በማያውቀው ከተማ አራስ ልጅ ይዛ ትን ቢላት ምትቀምሰው ውሀ ሳይኖር ትቻት ውጪ ማደሬን ሳስብ ጭንቅላቴ በትክክል ስለመስራቱም ተጠራጠርኩ
ይቀጥላል .....
🔻ክፍል9️⃣ ከ 1️⃣0️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet💔
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔