🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ ማኔ
ክፍል 8️⃣
በነጋታው ልክ ከፋኖስጋ እንደተገናኘን የጓደኛዋን ስልክ ሰበብ ፈልጌ ወሰድኩባትና ጓደኛዋን ማውራት ጀመርኩ።
ልደቷ በሚቀጥለው ወር ላይ እንደሆነ ነገረችኝ አጋጣሚ ሆኖ ሚውለው እሁድ ቀን ነበር በደስታ ብዛት ላብድ ምንም አልቀረኝም።
ቀጣዮቹን ጊዜዎች እንዴት ወጥሬ ሰርቼ
ለሷ ፕሮግራሙን እንደማዘጋጅላት እያሰብኩ መተኛት መነሳቱን ተያያዝኩት።
ወሩ ሁላ ረዘመብኝ ፋኖስ ሁሌ ምትሄድበት ቤት ስላለ እዛ ይዛኝ ሄዳ ቁጭ ብለን እያወራን የልደቷን ቀን እንዴት ማሳለፍ እንደምትፈልግ ጠየኳት።
ልደት የማክበር ልምድ ስለሌለኝ ተኝቼ ነው ምውለው ስትለኝ ይበልጥ ደስ አለኝ ካላሰበችበት እንደውም ለኔ ጥሩ ሰርፕራይዝ ይሆንልኛል ብዬ ተደሳሰትኩ።

ለእናቴና ለጓደኞቼ ነገርኳቸው ሁሉም ያንን ቀን በጉጉት እንደሚጠብቁ ነገሩኝ።
የሷንም ጓደኞች የዛን ቀን ሰርፕራይዝ እንደምናረጋት ነገርኳቸው ሁሉም ደስተኞች ነበሩ።
እናቴ ቤት እናዘጋጅላት ፈጣሪ ይመስገን ቤታችን ቆንጆ ነው አያሳፍርም አደል እንዴ አለችኝ።
በደስታ ተስማምቼ ፕሮግራሙን ቤት ለማድረግ ወሰንና ቀኑ ሲደርስ ቤት ዝግጅቱን ጀመርን።
እኔ ቀኑ እስከሚደርስበት አምስት ቀናት ውስጥ እንቅልፍ አልወሰደኝም ሁሉም ነገር ብርቅ ሆነብኝ አንዳንዴ ሌሊት ላይ እየተነሳሁ እንዴት እንደምንበረከክ ሁላ እየተለማመድኩ ብቻዬን እስቃለሁ።
የፕሮግራሙ ቀን 8 ሰአት ላይ ቤት እንድትመጣ ነገርኳት ልእልት ከዋዜማው ጀምሮ ከኔ በላይ ከእናቴጋ እየተጋገዘች ሁሉንም ነገር ስትሰራራ ነበር።
የፋኖስ ጓደኞች ከሷ ቀደም ብለው መጡ የኔም የስራ ባልደረቦች ተገኙ።
እኔ የሆነ ጭንቀት ውስጤን ተናነቀኝ።
ዝም ብዬ መቅበዝበዜን ያየችው እናቴ እቅፍ አደረገችኝና ልጄ እራስህን እያየኸው ነው አደል እንደልጅ እየተቅበዘበዝክኮ ነው አለችኝ። ፈገግ ብቻ ብዬ ዝም አልኳት።
ሰአቱ ደረሰ ፋኖስ ደውላ እየመጣች እንደሆነ ነገረችኝ።
መጣች። መጀመሪያ ዝምብለን ልደቷን ሰርፕራይዝ ያደረግናት እንዲመስላት ስትገባ ቀለል አድርገን ሰርፕራይዝ አልናት በፍፁም እንዳልጠበቀችና ደስ እንዳላት ሆና አለቀሰች። አቅፌ አባበልኳት።
ለልደቷ የተዘጋጀውን ኬክ ከመቁረሷ በፊት እኔ የጋብቻ ጥያቄዬን ማቅረብ ስለነበረብኝ ሁሉም በአይናቸው አሁን አሁን ጠይቃት የሚል ምልክት ሲሰጡኝ
ሳታስበው ከኋላዋ ተንበርክኬ በፍርሀት ውስጥ እንዳለሁ ታገቢኛለሽ ብዬ ጠየኳት።
በውስጤ የልጅነት ህልሟን የሁልጊዜ ፍላጎቷን ስላሳካሁላት ምን ያህል እድለኛ ወንድ እንደሆንኩ እያሰብኩ ነበር።
እሷ ግን ልክ ከፊት ለፊቷ ተንበርክኬ ጥያቄውን ሳቀርብላት ቃል ካፏ ሳይወጣ ወደጓደኞቿ ዞረችና ከት ብላ ሳቀች ጓደኞቿም አላስቻላቸውም አብረዋት ሳቁ..........
ግራ ገባኝ ምን እየተካሄደ እንዳለ እኔ ከተንበረከኩበት ሳልነሳ የሁሉንም አይን በየተራ እያየሁ ምንድነው ፋኖስ ታገቢኛለሽ ብዬ እየጠየኩሽ ነውኮ አልኳት።
እሱኮ ነው ያሳቀኝ አየህ አደረኩት ፊት ለፊቴ አንበረከኩህ ይቺን ቀን ለማየት አመት ከምናምን መጠበቄ እራሱ ቆጭቶኛል ግን አደረጉት አንበረከኩህ ብላ በእልህ እየተናገረች እንባዋ ካይኗ ጠብ ጠብ አለ።
ጓደኞቿ እኔን በግልምጫ እያነሱ እየጣሉ እሷን አየሽ አንቺ አውርተሽ አልተውሽውም አሳካሽውኮ ጀግና ነሽ በቃ ለምን ታለቅሻለሽ እያሉ ይዘዋት ወጡ እኔ ነገሩ ህልም እየመሰለኝ ዝም ብዬ እናቴን አይን አይኗን እያየሁ ቆምኩኝ።
ወዲያው ተመልሳ መጣችና ለሌላ ጊዜህ ግን ሰዎች ላይ አትበጣጠስ ምድር ላይ ያለሁት ወንድ እኔ ብቻ ነኝ አትበል እሺ የምድራችን ባዶው ወንድ አንተ ነህ ብላ ተመልሳ ወጣች እኔ እየሮጥኩ ተከተልኳትና ምን እያወራች እንዳለች ጠየኳት ላንተ ማብራራት የለብኝም ምክንያቱም አንተ ለኔ ምንም ነህ ብላ ጥላኝ ወጣች የሚተናነቀኝን እንባ ዋጥ አድርጌ ወደቤት ተመልሼ ገባሁ ።
እናቴ መሬት ላይ ወድቃ ከበዋት እንድትረጋጋ እየነገሯት ነበር እሷ ዝም ብላ ታቃስታለች እየሮጥኩ ሄጄ እማዬ እማዬ እያልኩ ከወደቀችበት ለማንሳት ስሞክር ልጄ በሰው ፊት አዋረደችህ አደል እኔ ባይኔ ሙሉ ለማየት የምሳሳልህን ልጄን ሰው ፊት አንበርክካ ጥላህ ሄደች ምን አርገሀት ነው ልጄ አንተ ለሰው ክፉ አታስብ ምን ሴጣን አሳስቶህ ምን ጥፋት ሰርተህ ነው አለችኝ እያለቀሰች የእናቴን ንግግር ስሰማ እኔ ሳግ እየተናነቀኝ አብሪያት ማልቀስ ጀመርኩ።
አንስተን ወደመኝታ ቤት ወስደን አስተኛናት ዶክተር ልጥራ ወይ ሀኪም ቤት ልውሰድሽ ስላትም አሻፈረኝ ስትል ምንም ማድረግ አልቻልኩም።
ጓደኞቼ ምንም አታረጉም ሂዱ በቃ ብያቸው መቆየት ቢፈልጉም አስኬድኳቸው።
እኔ ከእናቴ አጠገብ ቁጭ ብዬ አስሬ ትንፋሿን ቼክ እያደረኩ.....
ይቀጥላል...
🔻ክፍል 9️⃣ከ 1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔