#ከመናገር_ማሰብ_ይቅደም
በድሮ ጊዜ አንድ ሰው ጥፋት ያጠፋና ዳኛ ፊት ይቀርባል። ታድያ ዳኛው ሦስት ዓይነት የቅጣት ምርጫ አቀረቡለት፡፡
1. አንድ ኪሎ ሽንኩርት እየላጠ መብላትን
2. አንድ መቶ ጅራፍ መገረፍን
3. አምስት መቶ ብር መክፈልን
ሰውዬው ለማሰብ የሚሆን ልቡና የሌለው ነበርና የመጀመሪያዉ ምርጫ ሆኖ ስላየው ብቻ " ሽንኩርቱን እበላለሁ " አላቸው፡፡
አንድ ኪሎ ሽንኩርት ቀረበለት፡፡ ገና አንድ ሁለት መብላት ሲጀምር ታድያ ዓይኑ ማልቀስ ፣ ለሐጩም መዝረብረብ ጀመረ፤ አልቻለም። ከመቀመጫው ተስፈንጥሮ ተነሣና « መቶ ጅራፍ መገረፍ ይሻለኛል » አላቸው፡፡
ወዲያው ኃይለኛ ገራፊዎች ተጠሩና እየተፈራረቁ ይለበልቡት ጀመር፡፡ ግማሽ እንደደረሰ አልቻለም፡፡ እጁን ወደ ላይ አነሣ፡፡
«እህሳ» አሉት ዳኛው፡፡
«አልቻልኩም» አላቸው፡፡
«ታድያ ምን ይሻላል» አሉት እየሳቁ፡፡
«በቃ አምስት መቶ ብሩን እከፍላለሁ» አለ ከተኛበት እየተነሣ፡፡
«ያንተ ትልቁ ጥፋት መጀመርያ ወንጀል መሥራትህ ብቻ አይደለም፡፡ ማሰብ አለመቻልህ እንጂ፡፡ ምናለ አስበህ ከሦስቱ አንዱን ብትመርጥ ኖሮ፡፡ እኔ ከሦስቱ አንዱን እንድትቀጣ ነበር የወሰንኩት፡፡ አንተ ግን መናገር እንጂ ማሰብ ባለመቻልህ ሦስቱንም ተቀጣህ፡፡» አሉት።
👉ብዙዎቻችን ከመናገራችን በፊት ማሰብ ሳንቸል ቀርተን በዘፈቀደ በተናገርነው ቃል እራሳችንን ፣ ቤተሰቦቻችንን ፣ ጎረቤታችንን አልፎም ሀገርን እረብሸናል፤ ጎድተናል፡፡ ሁሌም ከማውራታችን ከመፃፋችን በፊት የምናገረው ፣ የምፅፈው ነገር ሰዎችን ያስከፋል? እውነት ነው ብለን እንጠይቅ፡፡ እውነት እራሱ የብዙሀንን ሰላም ለመጠበቅ ሲባል ካለቦታውና ካለወቅቱ አይገለፅም፡፡
እናም ወዳጆቸ ከመናገራችን በፊት እናስብ።