#ዓድዋ
በቀደምት ጀግኖች አያቶቻችን ታላቅ ተጋድሎ እና መስዋዕትነት እንዲሁም በታላቁ ታሪክ የማይረሳው ንጉሳችን ዳግማዊ አጤ ምንሊክ እና በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ብልህ አመራር እና አስተባባሪነት ለተቀዳጀነው አንፀባራቂው የ፻፳ ወ፱ኛው የአድዋ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ የሚል መልዕክቴን ሳስተላልፍ በታላቅ ብሔራዊ ኩራት ነው::
ይህ በታሪክ ተመዝግቦ በየአመቱ የምንዘክረው አድዋ ላይ የተቀዳጀነው ድል የኢትዮጵያን ነፃነት ያስከበረ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ የቅኝ ግዛት ቀንበር ተጭኗቸው ሲሰቃዩ ለነበሩ አፍሪካዊያን ወንድም እና እህቶቻችን እንዲሁም በመላው አለም በጭቆና ውስጥ የነበሩትን ጥቁር ህዝቦች ቀና ብለው እንዲሄዱ እና ነፃ እንዲወጡ በወቅቱ ታላቅ መነቃቃትን የፈጠረ ገናና የጥቁር ህዝቦች ድል ነው።
የዘንድሮውን የ፻፳ ወ፱ ኛው የአድዋ ድል በአል ስናከብር ሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት ቀላል ለማይባሉ አመታት አንድነቷን አስጠብቃ ወደ ፊት እንዳትራመድ ሰቅዞ የያዛትን ተከታታይ የብሔር ፖለቲካ አዙሪት እንደ ሀገር እና እንደ ህዝብ ያስከፈለንን እና እያስከፈለን ያለውን ዋጋ ግምት ውስጥ በማስገባት ካለንበት ውስብስብ እና እጅግ ኋላቀር የዘር ፖለቲካ ለመውጣት ከመቼውም ጊዜ በላቀ አንድነታችንን አስተባብረን የህልውናችን መሰረት የሆነችው እናት ሀገራችንን ለማዳን በንቃት መቆም ይጠበቅብናል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)