የኔ ግጥም


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ግጥም ይወዳሉ ?
ክብሯትና ክቡራን የተለያዩ መዝናኛዎችን ይፈልጋሉ
✍ግጥሞች
ጥቅሶች
የታዋቂ ሰዎች ታሪክ
አጫጭር ልብወለዶች
❤️የፍቅር ታሪኮችን

እና ሌሎችንም ነገሮች እዚህ እኛ ጋር ያገኛሉ
ቤተሰብ እንሁን
ጥያቄ አስተያየት ካላቹና Admin ማናገር ከፈለጉ
@poembot

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ደስ የሚል በአል!

@ilovvl
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ


Forward from: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
"የምሰራች"
ዮም:ፍስሀ:ኮነ:በእንተ:ልደቱ:ለክርስቶስ!! ትህትናን፣ፍቅርን የሰውን ዋጋ በበረት በመወለድ:አስተማረን!!
ወልድ:ሲወለድ:የሰው:ልጅ የሚፈልገውን: አምላክነት:በእሱ:አገኘ::
ውድ የግጥም ቃና ቤተሰቦች እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰለም አደረሰህን 🙏 መልካም በአል

@ilovvll
@ilovvll
@ilovvll 👈 ቤተሰብ ይሁኑ
አብሮነትዎም አይለየን


"ታመሀል ይለኛል ሀኪም"
Voice 😊😊😊👏👏👏
Arif gtm

@yene_gtm
@yene_gtm


"ታመሀል ይለኛል ሀኪም"
_____
ህመሜ እንደሌሎቹ መስሎት እራስ ምታት
መስሎ
ት ሙቀት መጨር ትኩሳት ነር መስሎት፤
.....
ስንቱን መድሀኒት ሲያዝ ስገዛ የታዘዝኩትን
ምንም ለውጥ ላላይበት ስወስድ የተባልኩትን፤
......
እንኳን ሊሻለኝ ይቅርና ደህን ልሆን እንደ በፊት
እየባሰብኝ መጣ ለምን እንደሆን እንጃለት፤
.....
ታመህ ነው ይለኛል ሀኪም ጤናህ አልተመለሰም
እየጨመረ ነው እንጂ ምንም ሊቀንስ አልቻለም
#ታመሀል ይለኛል ሀኪም፤
.....
መች ምልክቱን ነግሬው እንዴት እንደሚያደርገኝ
የውስጤን መች አየውና ሁሌ ታመሀል የሚለኝ፤
.....
አያተኩስም ግንባሬ ሙቀቴም ገና አልጨመረም
እራስ ምታትም የለብኝ ደም ብዛት ግፊት ስኳርም፤
.....
የራሴን ህመም የማውቀው እኔው ሆኜ ከሱ በላይ
#ታመሀል ይለኛል ሀኪም ላይረዳው የኔን ስቃይ፤
.....
ላያውቅ ፍቅር ማጣቴን ከደስታ ሀሴት መራቄን
ላያውቅልኝ ሰው ማጣቴን አንድነትን መናፈቄን፤
.....
ችግሬ ሌላ ሆነና ለየት ያለ ከሌሎቹ
ሁልጊዜ መጠየቄ በዝቶባቸው ቢሰለቹ፤
.....
አሉኝ ጭራሽ ይህ እብደት ነው ጨመር አርገው ከትኩሳት
አብሰውት ከደም ብዛት ከደም ግፊት ከራስ ምታት፤
......
ጤንነትህ ልክ አይደለም አይምሮህ ትንሽ ተነክቷል
ህመምህ ድንበር ተሻግሯል በቃ አንተ ልጅ አብደሀል
#ይለኛል ሀኪሙ ታመሀል፤
.....
#ታመሀል ይለኛል ሀኪም ጤንነትህ ልክ አይደለም
ለህመሞችህ መድሀኒት በጭራሽ እኔጋር የለም፤
.....
ይለኛል እብድ መስዬው ተለይቶበት ህመሜ
ሳይገባው የኔ በሽታ ፍቅር እንደሆን ጥሜ ፤
.....
ጥላቻ ነው የኔ ጠላት ጥላቻ ነው የኔ ህመም
ትኩሳት ሙቀት መጨመር እራስ ምታትም አይደለም፤
....
እብደትም ከቶ አይደለም የአይምሮ መሳት ችግር
በሽታዬ ጥላቻ ነው የኔ ህመም ማጣታት ፍቅር፤
....
መለያየት ነው ህመሜ መራቅ ከምወዳቸው
እስክገናኝ ከውዶቼ ወዳጅ የኔ ካልኳቸው፤
....
አይቀንስም በሽታዬ ህመሜም አይድንም ከቶ
እንዲህ አድር ባይነት በልባችን ተንሰራፍቶ፤
...
ጥላቻችን ተባብሶ አንድነታችን ደፍርሶ
መተማመን ተመናምኖ መከባበራችን ቀንሶ ፤
...
እንዴት ይሻለኛ ከቶ
ጥላቻችን ወደር አጥቶ፤
...
ልይገርህማ ሀኪሙ የኔን ህመም መድሀኒት
ፍቅር ደስታ መተሳሰብ እኩልነት አንድነት
መከባበር አብሮ መኖር ማጠናከር ወዳጅነት
የጥላቻችን ማርከሻ እኚህ ናቸው መድሀኒት፤
...
ያኔ ይሽራል በሽታው እብድ መባሌም ያበቃል
ጨለማው ፊቴ ይፈካል ዝም ያለው ጥርሴም ይስቃል፤
...
ይሽራል ያኔ በሽታው ይሄ የልቤ ህመም
እስከዛው ግን ቀን እስኪያልፍ
#ታመሀል አትበለኝ ሀኪም፤
__

@yene_gtm
@yene_gtm

✍✍fethi 🧔


Forward from: Safaricom Ethiopia
🎁Safaricom ethiopia ሽልማት🎁
በተጠቃሚዎች ዘንድ እውቅናን ለማትረፍና ደንበኞችን ለማብዛት የቴሌግራም bot ከፍተናል
በውስጡም ብዙ ሽልማቶችን አዘጋጅተናል።
🎁ያልተገደበ የአንድ ወር ኢንተርኔት
🎁smart phone( s21 ultra)
🎁Asus personal computer
ይህንን ለጓደኞችዎ በመላክ ተሸላሚ ይሁኑ

ማሳሰቢያ! ይህ ሊንክ የሚያገለግለው ለ Nardos F ብቻ ነው

https://t.me/Safaricom_ethiopia_new_bot?start=r0542771246


🎤መክሊት የ16ቷ

#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ


ምን ነካሽ ?!
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
' ጥፋቱ የማን ነው? ' ፥ ብዬ እንዳልጠይቅሽ ፣
ቃልሽን ሳልሰማ ፥ እንባ ነው ሚቀድምሽ !
ምንድነው ገላዬ? ፥ ውስጥሽን በርዞ ፣
የልብሽን ደጀን ፥ መሻከር ወዝውዞ ፤
ቂም አይሉት እልህ ፥ በነፍስሽ ተረግዞ ፣
ዜማሽ ቅኝት አጥቶ ፥ በሀዘን እንጉርጉሮ ፣
' ተወኝ ! ' የሚያስብልሽ ፥ ለአይን እንኳን አቅሮ ?

ለምን ነው አካሌ ??....
ሰውነት እርስቱን ፥ ቀን ሲገፋው ማልዶ ፣
በእምነት የካቡት ቃል ይወድቃል ተንዶ ፤
ፍቅርን ባነፁበት ፥ በቀየዱት ቀዬ ፣
እንዴት መልስ ይሆናል ፥ ለየምን እዬዬ?

ድክምክም አድርጎ ፥ ፍዝዝ ትክዝ ትክዝ ፣
አዚም ተከናንቦሽ ፥ ቀንሽን ሲበርዝ ፣
በጣት ያልጠለቀ ፥ የልባችን ኪዳን ፣
' ምን ነካት? ' ይለኛል ፥ ገፅሽ ሲደማምን።

እውነትም ምን ነካሽ ? ፥ ምን አየሽ እርግቤ
የሀሴቴ ደንገል ፥ የነብስ ረሀቤ
ምን ነካሽ? ፥ የኔ ወርቅ
የህይወት ውቧ ሰንደቅ
የናፍቆት ዶሰኛ
የቀን አመለኛ
የአይኔ ስር መሀረብ
የትዝታ ቀለብ
የሳቅሽ መስክ ላይ ፥ መከፋት ሳር ግጦ ፣
አዛኝ አንጀትሽን ያ ጭካኔሽ በልጦ ፤
በአይንሽ ስትገርፊኝ ፣
በኩርፊያሽ ስታስሪኝ ፣
በእምባሽ ልቤ ወልቆ ፥ ዝምታሽ ሲያደቀኝ ፣
' ያቺ ሴት ናት! ' ብሎ ማመኑ ጨነቀኝ።

እናልሽ ገላዬ ፥ አንቺ የነፍሴ ኩሬ
ድክምክም አድርጎ ፥ ፍዝዝ ትክዝ ትክዝ ፣
አዚም በገባሩ ፥ ቀንሽን ሲበርዝ ፤
በጣት ያልጠለቀ ፥ የልባችን ኪዳን ፣
'ምን ነካት? 'ይለኛል ፥ ገፅሽ ሲደማምን ።
ምን ነካሽ በእኔ ሞት??
.
.................... //// ....................
መስከረም ፳፻፲፫ ዓ.ም
@yene_gtm
@yene_gtm


Forward from: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
ድምቀት ማለት እኚ ህፃናት ናቸው😘

ኖሩ ወሪ መና ኖሩ


አዱሬሳኮ ማሎ....

አዱሬን ደልቴ መደቢረቲ
አዱኛን ዱፍቴ መነ ኬሰቲ

ትርጉም በስለሺም ቢሆን አስፈልጉልኝ

እወዳቹሀለው 💚መልካም💛በአል❤

#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ


Forward from: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
✍️😷ወግ ይድረሰኝ😷✍️


ሚስት ፈልጉልኝ ቀበጥ - ቅብጥ ያለች፣
ለኑሮ ለፍቅር - ፍፁም የምትመች።

ሁሌ የማስብላት - እኔ ከ "እኔ" በላይ፣
ሳቅ ደስታዋን እንጂ - ክፋቷን የማላይ።

እኔም ልክ እንደ ሠው
መቼም ወጉ ደርሶኝ፣
እንደ ገጣሚዎች...
ፍቅርሽን አፍቅሬ - ሚዛን አሳንሶኝ፣

✍️
ላንቺ ያለኝን ፍቅር
ባለችኝ ወረቀት እንድሞነጫጭር
ቶሎ ነይ ሔዋኔ....
እስቲ ወግ ይድረሰኝ - ልግጠም ስለ ፍቅር


አልአዛር
@DONAY
ኦርያሬስ ✍
፭ - ፲፪
፮:፳፪ ቀን...

@ilovvll
@ilovvll




Forward from: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
The last day of 2013😥

2014 የብርሀን ዘመን እንዲሆንልን
ችቦ በማብራት ምሽቱን አድምቀነዋል ☺

ቢለማም ቢከፋም በፈጣሪ እርዳታ ለ አዲስ ቀን እና ለአዲስ አመት ልንበቃ ሰአታት ቀርተውናል

2013 ግን ስለይክ በእንባ ነው 😘

#ግጥም_ቃና
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ


Forward from: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
The last day of 2013😥

2014 የብርሀን ዘመን እንዲሆንልን
ችቦ በማብራት ምሽቱን አድምቀነዋል ☺

ቢለማም ቢከፋም በፈጣሪ እርዳታ ለ አዲስ ቀን እና ለአዲስ አመት ልንበቃ ሰአታት ቀርተውናል

2013 ግን ስለይክ በእንባ ነው 😘

#ግጥም_ቃና
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ


Forward from: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
ሆዴን ጅብ በበላው፣
አንጀቴን ባራሰው፤
የማያገኘውን እንዴት ይመኛል ሰው?

#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ

💚ሰናይ💛ግዜ❤


Forward from: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
ንብ አትማረክም በአበቦች ፍካት፣
መአዛው ካልሳባት ነፍሷን ካላረካት፤
ድምቀቱ ቢያማልል ውበቱ ቢገዛም፦
ጣፋጭ ልቅሰም ብላ አታርፍም ከመርዛም!

#የግጥም_ቃና_በመክሊት_የ16ቷ
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ


💚ሰናይ 💛እለት ❤


ቧ ያለዉ ቀን ለት(ቡሄ)
ጀግናንኝ ከምለዉ ከነጉራዬ ነኝ ከዛ ኩሩ ደንዳና ልቤ ጋ ከንጋት ጋር አብረው ተያይዘውታል የቡሄ ጭፈራ🤷‍♀ እኛቤት ደርሰዋል በሚያጉርመርም ድምፅ🙄 ያለመደብኝን እኔዉ ለእይታ ተስፈንጥሬ ወጣው "ክፈት በለው ተነሳ የንን አንበሳ" ልቤን ሊከፈተዉ ደረቱን ነፈቶ በቁጣ 😠
ደሞ አክብሮ "ክፈት በለው በሩን የጌታዬን" 🙏 "ሆያሆዬ ጉዴ ጨዋታ ነው ልማዴ"ብሎ ከባልንጀሮቹ አባባን መርቀ አማማን ጨምሮ አሜን ብሎ ሄደ ልቤን ተቀብሎ 👳‍♂ የኔታ እርሱ ጋ ክበሩ የኔታ ቤቴ ድረስ ፈቅደው( ልከው) ልቤን ላዘረፉኝ ። መልካም በዓል።
Narii 24


Forward from: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
።።።።።። በጨዋው ልጫወት።።።።።።

"ሆያ ሆዬ" ሲሉ ሙልሙል መስጠት ትቼ፣
ከድምፅ አውጪው ጋራ ብሄድ መንገድ ስቼ፤
ይቅር!
ይቅር ብቻ በሉኝ የኔታ አይቆጡ፣
ለቀክፋት አይደለም ለ'አንድ ማታ አይምጡ።

ምን መሰሎት አባ፦

ቡሄ አልፎ ክረምት፣
ዶሮም ጮሆ ለሊት፤
ስለማይደገም ግዜም እንደ ትውፊት፤
ዝም ይበሉኝ እና በጨዋው ልጫወት፣
እርሶም አይፈሩ እኔም ልወቅ ልኬት።

✍መክሊት የ16ቷ

#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈 🙌ቤተሰቦች🙌

ለኢትዮጲያዊያን ቤተሰብዎ ያጋሩ

💚💛❤
ሰናይ ግዜ


Forward from: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
ሆያ ሆዬ ጉዴ
እሷን እሷን ይላል ሆዴ!🤷‍♂

@ilovvll
@ilovvll

እንኳን ደረሰብን መልካም በአል💚💛❤


Forward from: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
#ጊዜ_ጌታ
#ናታን_ኤርሚያስ @UniqueDy

በልኬቱ : ወርዶች : ፍቅሩን : ደርድሮ፣
ነገ : አብሮሽ : ላይዘልቀው : ዛሬሽን አፍቅሮ፣
ልብሽን : ፈልጎ : ልቡ : ውስጥ ሊከትሽ፣
በሀሰት : ምህላው : የእውነት : ሲክብሽ፣

ትላንትን : ማልቀሱ፣
ሳትቆስል : ነብሱ፣
ከላይ : ከላዩ : ላይ፣
እንባውን : ዘርግፎት : መከፋቱ : እንዲታይ፣
.
.
እዘኚልኝ : ብሎሽ፣
አጥፎ : እያሳዘነሽ፣
በፍቅር : ለማረፍ : ብዙ : ተሰቃየሽ፣
ባለፍሽበት : መንገድ : እግሮችሽ ሲጣሉ፣
ዘመን : አሽከርክሮሽ : ወደቅሽ ከመሀሉ፣
መውደቂያው ቢደላሽ አልጎዳኝም ብለሽ፣
ራሱን : ለመያዝ : እግሩ : ስር : ተገኘሽ፣

ነግሬሽ : ነበረ : ጊዜ : ጊዜ : እንዳለው፣
ስንቱን : እያነሳ : ስንቱን : እንደጣለው፣
ላትረሺው : ረስተሽ : ዛሬ ላይ : ብትፈርጪ፣
ለጊዜ : ተስለሽ : ከራስሽ : አምልጪ !


#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ

__~°\°/°💚ሰናይ💛ግዜ❤°\°/°~__


Forward from: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
#የግጥም_ቃና

የ እግዜር ስላቆች

ለፅድቅ : ፍትሀት : ሀጥያትን : ካረገ፣
መርገምን : በረከት : አርጎ : ከፈለገ፣
መሰዋዕት : አርጎ : እጣን : አሽቀንጥሮ : ቆሻሻ እያጨሰ፣
ገነትን : እያለ : ሲኦል : ከፈለሰ፣

......
በየቱስ : አምክሮ : ሞገስን : ይስባል፣
በነገር : ጎዳና : አቡዋራ : ያቦካል፣
ምሳሌውን : ንቆ : ፈጣሪው : ጋር : ቀርቦ፣
እንዲህ : ጠየቀ : አሉ : ጥጋብን : ተርቦ፣
አሳ : ስጠኝ : አለው፣
ዳቦ : ስጠኝ : አለው፣
እግዜርን : በእግዚአብሔር: ብሎ : እየለመነው፣
ፈጣሪም : ሊቀልድ : ይህን : አሰበና፣
ይሁን : ብሎ : ቸረው : ድንጋይ : እና : እባብ፣
ለንቀቱ : ክብር : ለጥጋቡ : ርሀብ፣

❗️ማሳሰቢያ የመጨረሻው አንጓ ላይ ያሉት ቃላቶች መልካም ክፉዎች ከሚለው ከሌላኛው ግጥሜ ጋር ቢመሳሰሉም። ፍፁም የተለያየ ሀሳብን ይዘዋል ።
✍ናታን ኤርምያስ
@UniqueDy

#የግጥም_ቃና
👇👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ


Forward from: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
ዘ ነገደ ፍጥረት

እንሆ ዓለም ተፈጠረ፤
ከመቅፅበት ውድያው
ሃጥያት ተጀመረ

ዲያቢሎስ በትቢት፣
የስው ልጅ በቅናት
አጋንንት በክፋት

አንድ ላይ አብረው፣
አምላክ አስቀይመው

ሞትን አስልጥነው

ከገነት ተባረው፣
እመሬት ተጥለው

መፍቀሬ ስብ አምላክ፣
እነሱን ፍለጋ

ከስማያት ወርዶ፣
ስላሙን አውርዶ

ለስው ልጆች ብሎ፣
በመስቀል ላይ ውሎ

ሁሉን ቢምሪቸው፣
ነፍሱን ቢስጣቸው
ፍቅርን ቢያሳያቸው

ዳግም ቢጠራቸው

ከዚህ ሁሉ መሀል፣
ለማንም ያልበጀው

ዘ ነገደ ፍጥረት፣
ሃጥያት ጣመቻቸው።
✍ Habtamu Mideksa
@am_habte


@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ

20 last posts shown.

132

subscribers
Channel statistics