"በጸጥታ ችግር"ለሁለት ወራት እርዳታ ባልደረሰበት ቡግና ወረዳ በሀገር ሽማግሌዎች ስምምነት መደረጉን ተከትሎ የእህል እርዳታ መጓጓዝ መጀመሩ ተገለጸ!
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በህጻናት መቀንጨርና በምግብ እጥረት ለተጎዱ ከ110 ሺህ በላይ ሰዎች ከሁለት ወራት በኋላ የርዳታ እህል መጓጓዝ መጀመሩን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጸ።
በተጨማሪም በላሊበላ ከተማ 34ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች 5100 ኩንታል እርዳታ ለፌደራል መንግሥት መጠየቁን ጠቅሰው እስከዚህ ሰዓት ድረስ 1200 ኩንታል መግባቱን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር አመላክተዋል፡፡
እርዳታው መጓጓዝ የጀመረው በጸጥታ ችግር ምክንያት ላለፉት ሁለት ወራት እርዳታ መድረስ ባለመቻሉ በሀገር ሽማግሌዎች ስምምነት መደረጉን ተከትሎ መሆኑንም ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እያለ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በወረዳው የተከሰተውን የምግብ እጥረት ቀውስ የሚገልጹ ሪፖርቶችን እየተከታተለ መሆኑን ትናንት ታኅሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም አመልክቷል።
Via Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa