በመዲናዋ የትራፊክ ፍሰትና አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታን የሚቆጣጠር የድሮን ስምሪት ይደረጋል - የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
በቅርብ ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ፍሰትና አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም ታላላቅ ፕሮግራሞችን ቁጥጥር ማድረግ የሚችሉ የድሮኖች ስምሪት እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገለፁ፡፡
የፀጥታ ጥምር ኃይል በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ያለውን የፀጥታ ሁኔታን በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።
ግምገማውን የመሩት ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የወንጀል መከላከል ሥራችንን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ የሚችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም ከ15 ቀን በፊት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የከተማችን ሰላምና ደህንነት ዘላቂ እንዲሆን የፀጥታ ጥምር ኃይሉ ተቀናጅቶ በመሥራቱ ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡
በዚህም አሁን ላይ በአዲስ አበባ ምቹ የፀጥታ ሁኔታ ያለበትና በቀጣይ በሀገራችን የሚከበረው የጥምቀት በዓል እና የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በሰላም እንዲጠናቀቁ ከወዲሁ ይህንን የሚመጥን ዝግጅት መደረጉን ገልፀዋል፡፡
Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa