የነዳጅ ማደያዎች ፈቃድ የመስጠት ሥራ ሙሉ በሙሉ መታገዱ ተገለጸ!
በኢትዮጵያ ያሉ የነዳጅ ማደያዎች የትኞቹ የሚጠበቅባቸውን ደረጃ አሟልተዋል? የትኞቹስ አስፈላጊውን አገልግሎት እየሰጡ ነው? የሚለውን እና ተያያዥ ጉዳይዎች እስኪጣሩ ድረስ ፈቃድ የመስጠት ሥራው ለጊዜው መታገዱን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ለአሐዱ ገልጿል፡፡
የባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት እና የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ በቀለች ኩማ በዚህ ጉዳይ ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ጥናት እየተደረገ መሆኑን አንስተው፤ በአዲስ አበባ በልማት የፈረሱ መኖራቸውን አስታውሰዋል፡፡
በአዲስ አበባ በልማት የፈረሱትን ጨምሮ የትኞቹ ማደያዎች አስፈላጊ ቦታ ላይ ናቸው? የትኞቹ ደረጃ አሟልተዋል የሚሉ እና ተያያዥ ጉዳይዎችን በተመለከተ ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለመለየት ጥናት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ጥናቱ ሲጠናቅ እና ውጤቱ ሲታወቅ ፍቃድ የመስጠት ሥራው ሊጀምር እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡
ጥናቱ ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገባ ማደያ የሌለባቸው ቦታዎች ላይ ማደያዎች እንዲኖሩ ለማድረግ ያግዛልም ነው የተባለው፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘ የነዳጅ ግብይት ክልሎች ያቀረቡት ጥያቄ ሁሉም የፋይናስ ተቋማት ወደ ነዳጅ ግብይት እንዲገቡ ማስገደዱ አንስተዋል፡፡
የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን የግብይት ስርዓትን በኤሌክትሮኒክስ ካደረገ በኋላ ያሉት ሦስቱ የፋይናስ ተቋማት ብቻ ማለትም፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ እና ቴሌ ብር መሆናቸው በተገልጋዮች ላይ ቅሬታ ፈጥሮ እንደነበር ነው የተነሳው፡፡
"ክልሎች የሚገበያዩባቸው የፋይናንስ ተቋማት እና ባለስልጣኑ ግብይት እንዲፈፅሙ የፈቀደላቸው ተቋማት መጣጣም ባለመቻላቸው፤ ሁሉም የፋይናስ ተቋማት ወደ ዘርፉ እንዲገቡ ማድረግ አስፈላጊ ሆኗልም" ሲሉም ወይዘሮ በቀለች አክለዋል፡፡
"በሁሉም ክልሎች ያሉ እና የፋይናንስ ግብይቱ የሚጠይቀውን መስፈርት አሟልተው የግብይት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ ባንኮች ሁሉ መግባት እና በዘርፉ ላይ መስራት ይችላሉ" ሲሉም ገልጸዋል፡፡
"የፋይናስ ተቋማቱ መብዛት እና የግብይት ሁኔታው መስፋት ለቁጥጥር አዳጋች አይሆንም ወይ?" ሲል አሐዱ የጠየቀ ሲሆን፤ ተቋማቱ የፈቃድ ግዴታዎችን አሟልተው የሚገቡ ስለሚሆን ለቁጥጥር እና ለክትትል የሚከብድ ሁኔታን አይፈጥርም የሚል ምላሽ አግኝቷል፡፡የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ቢደረግም ነገር ግን በተደጋጋሚ ሕገ-ወጥ የነዳጅ ነጋዴዎች ምርቱን ሲያዘዋዉሩ መያዙን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እና ተባባሪ አካላት ሲገልጹ ይደመጣል፡፡
Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa