... የስው ልጅ ፍትህ እንደ አጭር ብርድልብስ ነው... የሰው ልጅ ሃቅ ፍርሃቱ ብቻ ነው... ምናልባት ማርጀት ማለት ይህን ማመን ይሆናል... ምናልባት ተስፋ መቁረጥ መልኩ እንዲህ ነው...
በመኖር አጸድ ውስጥ
(በእውቀቱ ስዩም)
ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::
እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
-ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤
ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::
|ዘካሪያስ|
°•.• @yenie_kal •.•°
@yenie_kal
○○○○○○○