ጥቂት ኦርቶዶክሳዊያን ባሉበት አከባቢዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስቀጠል በሀገራችን የሚስተዋለው የሰላም እጦት እንቅፋት እንደሆነበት ማኅበረ ቅዱሳን የዜማና የኪነ ጥበባት ማእከል አስታወቀ።
ጥር ፳፯/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን የዜማና የኪነ ጥበባት ማእከል አገልጋይ ዲያቆን ዮናስ ተስፋዬ እንደገለጹት ጥቂት ኦርቶዶክሳዊያን ባሉበት አከባቢዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስቀጠል በሀገራችን የሚስተዋለው የሰላም እጦት እንቅፋት እንደሆነባቸው ገልጸዋል።
ማኅበሩ ለበርካታ ዓመታት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማከናወኑ የሚታወቅ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የመዝሙር ክፍል ሐዋርያዊ ጉዞዎችን በተለያዩ አከባቢዎች በተለይ ጥቂት ኦርቶዶክሳዊያን በሚገኙበት ሥፍራዎች በመንቀሳቀስ በበርካታ ቋንቋዎች አገልግሎቶችን በማከናወን ተደራሽ ማድረግ ችሏል።
በዚህም አገልግሎት “ወደ 54 ቋንቋዎችን በመዝሙር ተርጉመው እየሰሩ እንደሚኙ የገለጹት ዲ/ን ዮናስ አክለውም ምዕመናን በሚሰሙት ቋንቋ ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ” በሚል ዕቅድ ይዘው እየሠሩ የነበረ እንደሆነና አሁን ላይ የሀገሪቱ የሰላም እጦት አገልግሎቱን ተደራሽ እንዳያደርጉ እንቅፋት የሆነባቸውን ለመቅረፍ ማኅበሩ የተለያየ አማራጮችን እየተጠቀመ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፍቃድ ተሰጥቷችው መንፈሳዊ ሥራዎችን እያከናወኑ የሚገኙ ማኅበራትም ወደ ገጠራማና ጠረፋማ አከባቢዎች በመሄድ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ምእመናንን የማስተማርና የማገልገል ሥራዎችን መስራት ቢችሉ በማለት ዲ/ን ዮናስ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።